ከ«ሀዲስ ዓለማየሁ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

ከውክፔዲያ
No edit summary
«ሃዲስ አለማየሁ» ወደ «ሐዲስ ዓለማየሁ (ዶ/ር)» አዛወረ: correct alphabets
(No difference)

እትም በ17:03, 26 ማርች 2008

ደራሲ ሃዲስ ዓለማየሁ ከአባታቸው ከቄስ ዓለማየሁ ሰለሞን እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ደስታ ዓለሙ በደብረ ማርቆስ ወረዳ በእንዶር ኪዳነ ምኅረት ቀበሌ በጥቅምት 5 ቀን 1903 ዓ.ም. ተወለዱ። ገና በጨቅላ እድሜያቸው በቤተ ክርስቲያን የሚሰጠውን ትምህርት መከታተል ጀመሩ። የቤተክርስቲያን ስርዐታትንና መንፈሳዊ ትምህርትን በጎጃም ገዳማት በደብረ ኤልያስ፣ በደብረ ወርቅና በዲማ ከቀሰሙ በኋላ ወደ አዲስ አበባ በመሄድ በስዊድን ሚሽነሪ ትምህርት ቤት በኋላም በራስ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ተከታተሉ። ለትንሽ ግዜ በአስተማሪነት ሥራ ተሰማርተው እንዳገለገሉ የፋሽስት ጣሊያን ወረራ ተከሰተ።

በጦር ሜዳ ዘምተው ሲዋጉ ቆይተው በአርበኝነት ሲንቀሳቀሱ በመያዛቸው ጣሊያን ከራስ እምሩ ኃይለ ሥላሴ ጋር ተልከው ለሰባት ዓመት በፖንዞ ደሴትና በሊፓሪ ደሴት ታስረው ቆይተዋል።

ከዚያም የተባባሪ ኃያላት ወታደሮች በ1935 ዓ.ም. ሲያመልጧቸው በተመለሱበት ጊዜ በትምህርታቸው እንደገና በኦክስፎርድ ከገፉ በኋላ በተለያዩ የመንግስት ተቋማት በተለይም በትምህርት ሚኒስቴር ለረጅም ግዜ አገልግለዋል።

ሃዲስ ዓለማየሁ በርካታ የስነጽሑፍ ሥራዋችን አበርክተዋል። ከነዚህም ውስጥ ታላቅ አድናቆትንና እውቅናን ያተረፈው ሥራቸው ፍቅር እስከ መቃብር (1958) በሁለት የተለያዩ መደቦች ውስጥ የሚገኙ የሁለት ሰዎች የፍቅር ታሪክ ላይ ያተኩራል። እንዲሁም በ1970 ወንጀለኛው ዳኛ በ 1980 ደግሞ ስለ ማህበራዊ ጉዳዮችና ስለ ጣሊያን ውርስ የሚዳስሰውን የልም እዣት የተሰኙትን ልብ ወለድ ታሪኮች ለንባብ አቅርባዋል።

ከዚህ ባሻገር:

የተሰኙት ጽሁፎችና የሌሎች በርካታ ሥራዎች ባለቤት ናቸው።

ሃዲስ ዓለማየሁ በኅዳር 26 ቀን 1996 ዓ.ም. በ94 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ዋቢ መጻሕፍት

Historical Dictionary of Ethiopia