መለጠፊያ:የኢኮኖሚ ምርጥ ጽሑፍ

ከውክፔዲያ

ገንዘብ

ሳንቲም እና ብር – በብዛት በስራ ላይ በተጨባጩ አለም ውስጥ የተሰማሩ የገንዘብ አይነቶች ናቸው። ገንዘብ ከነዚህ ውጭ ሊሆን ይቻላል።

በአንድ አገር ወይም ማህበረሰብ ውስጥ ለሸቀጥ (አሰፈላጊ እቃ) ና አገልግሎት መግዢያ እንዲሁም እዳ መክፈያ የሚያገለግ ማንኛውም ነገር ሁሉ ገንዘብ ይባላል።

የጥንቱ ገንዘብ ዋጋ ይመነጭ የነበረው ከራሱ ከተሰራበት እቃ ዋጋ ነበር (ለምሳሌ፡ ከወርቅ የተሰራ ሳንቲም) ። በዚህ ምክንያት እንዲህ አይነቱ ገንዘብ የኮሞዲቲ ገንዘብ ይባላል። በአሁኑ በአለማችን የሚሰራባቸው ገንዘቦች በራሳቸው የራሳቸው የሆነ ዋጋ የላቸውም (ለምሳሌ ከተልባ እግር የተሰራው ዶላር በራሱ ዋጋ የለውም) ። ይህ አይነት ገንዘብ ፊያት ገንዘብ ሲባል ዋጋው የሚመነጨው የአንድ አገር መንግስት ህጋዊ መገበባያ ብሎ ስላወጀው ብቻ ነው። ህጋዊ መገበባያ ሲባል ለማንኛውም በዚያ አገር ውስጥ ላለ እዳ ይህ የታወጀው ገንዘብ እንደ ክፍያ ሲቀርብ "አይ! አልቀበልም" ማለት ክልክል ነው። በዚህ ምክንይት የፊያት ገንዘብ ዋጋ ከመንግስት ሃይል ጋር ከፍተኛ ግንኙነት አለው።

ያንድ ዘመናዊ ሃገር የገንዘብ አቅርቦት በሁለት ይከፈላል፣ ይኸውም ተጨባጭ የሆነው የታተመው ብርና በማይጨበጥ መልኩ በባንክ ቤት ተጠራቅሞ ያለው በቼኪንግ እና ሴቪንግ የሚከፈለው የባንክ ሒሳብ ነው። ባብዛኛው ጊዜ እኒህ የ ባንክ ሒሳቦች ታትሞ ከቀረበው ብር በላይ ናቸው። በምናባዊ አለም ውስጥ የተቀመጡት እነዚህ የቁጥር ሰነዶች ምንም እንኳ የማይታዩና የማይዳሰሱ ቢሆንም ልክ እንደ ጥሬ ብር እኩል ለመሸጥና ለመለወጥ ያገለግላሉ። ...