መለጠፊያ:የእለቱ ምርጥ የአማርኛ ጽሑፍ

ከውክፔዲያ

አማርኛ ፦ ሥርዓተ ነጥቦች


በወረቀት ላይ የሰፈረ ሐሳብ (ቋንቋ) መልእክቱ ግልጽ ሆኖ እንዲተላለፍ ሥርዓተ - ነጥቦች የጎላ ድርሻ አላቸው። በጽሑፍ ላይ ነጥቦችን አስተካክሎ ካለመጠቀም የተነሳ ዐረፍተ ነገሮችን ያሻማሉ፤ መልእክቶች ይዛባሉ፤ ሐሳቦች ይድበሰበሳሉ። ስለዚህ ሐሳቦችን ግልጽ በሆነ መልኩ በጽሑፍ ለማስተላለፍም ሆነ የተጻፈውን መልእክት በትክክል አንብቦ ለመረዳት ሥርዓተ - ነጥቦችን እና አገልግሎታቸውን በሚገባ ማወቅ ተገቢ ይሆናል።

ብዙዎቻችን ከሁለት ነጥብና ከአራት ነጥብ በስተቀር ሌሎቹን ሥርዓተ - ነጥቦች በሚገባ አንጠቀምም። ለምሣሌ አንዱ ድርብ ሠረዝ (፤) የሚጠቀምበትን ቦታ ሌላው ነጠላ ሠረዝ (፣)/(፥) ይጠቀማል፤ እንዲሁም አንዱ ትእምርተ - ጥያቄ (?) የሚጠቀምበትን ቦታ ሌላው ትእምርተ - አንቅሮን ይጠቀማል። ወጥ የሆነ የአጠቃቀም ስርዓት አይታይም። በርግጥ አንዳንዴ ድርብ ሠረዝን መጠቀም አለመጠቀም የምርጫ ጉዳይ ሊሆን ይችላል። ሐሳቦች ተደራርበው ወይም ተጣምረው እንዲቀርቡ የፈለገ ሰው ድርብ ሠረዝን ተጠቅሞ ሐሳቦቹን በአንድ ዐረፍተ ነገር ሊያጠቃልል ይችላል። በአንጻሩ ደግሞ ሐሳቦቹን ቆራርጦ የተለያዩ ዐረፍተ ነገሮች በማድረግ ለየብቻቸው ሊያቀርብ የፈለገ ሰው አራት ነጥብን መጠቀም ይችላል። ዞሮ ዞሮ የሥርዓተ - ነጥቦችን አጠቃቀም ማወቅ ተገቢ ነው።

በአሁኑ ጊዜ በአማርኛ ቋንቋ ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙት ሥርዓተ - ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው።

አንድ ነጥብ (.)[ኮድ አርም]

አንድ ነጥብ (.) በግእዝ ነቁጥ ይባላላል። በአማርኛ ደግሞ <<ይዘት>> ተብሎ የሚጠራ ሲሆን በሦስት የተለየ መልክ ያገለግላል።

  • ቃላትን በምህፃረ - ቃል አሳጥሮ ለመጻፍ የሚያገለግል ሲሆን ሁለት የተለያዩ ሥርዓቶችን ይከተላል።

ሀ. የቃላትን መነሻ ፊደል ብቻ በመውሰድ ምሳሌ፡ ተ. መ. ድ. = የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት

ለ. የአንድን ቃል መነሻና መድረሻ ሆሄ ብቻ በመውሰድ ምሳሌ፡ ወር. = ወታደር


ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ