መሰቃ

ከውክፔዲያ

መሰቃ ማለቱ አንድ የጠበቅነው ነገር ተቃራኒ ሆኖ ሲገኝ ነው። ብዙ ጊዜ አስቂኝ አልፎ አልፎ ደግሞ አሳዛኝ ሊሆን ይችላል። ብዙ አይነት መሰቃዎች አሉ፦

  • የድራማ መሰቃ ፦ የአንድ ድራማ ታዳሚዎች ሊሆን የሚጠብቅን ነገር ሲያውቁ፣ ነገር ግን መድረኩ ላይ ያሉ ተዋንያን ሳያውቁ ሲቀሩ።
  • የቃላት መሰቃ ፦ ለምሳሌ ምፀት
  • ዕድላዊ መሰቃ ፦ የዕድል እጣ ፈንታ መጥፎ መሆን
  • ሶቅራጥሳዊ መሰቃ፦ አንድ ሰው ሆን ብሎ እራሱን የማያውቅ በማስመሰል የሌሎችን አለማወቅ ሲያሳይ (ተመልካች ወይንም ታዛቢ የሁኔታውን ምስጢር እንዲያውቅ ሆኖ ተነግሮታል)