መስቀል አደባባይ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search
የመስቀል ክብረ በዓል በመስቀል አደባባይ

መስቀል አደባባይኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ የሚገኝ አደባባይ ነው።‹‹መስቀል አደባባይ ለክብረ በዓል፣ ለአምልኮት፣ ለተቃውሞ፣ ለሩጫ፣ ለውድድር፣ ለእግር ኳስ፣ ለማረፊያ፣ ለስብሰባ፣ ለዳንስ፣ ለፓርኪንግ፣ ለማስታወቂያ፣ ወዘተ የሚውል የአዲስ አበባ ሕዝባዊ አደባባይ (Open Space) ነው፤››[1]

ስያሜውን ያገኘው በኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በየዓመቱ በሚከበረው የመስቀል በዓል ምክንያት ነው።ይህ ቦታ በደርግ አገዛዝ ዘመን በኦፊሴል "አብዮት አደባባይ" ተብሎ ይጠራ የነበረና በየዓመቱ የአብዮቱ ክብረ በዓል ይከናወንበት ነበር።የጥናት ድርሳናት እንደሚያሳዩት መስቀል አደባባይ በ1950ዎቹ መጀመርያ ስያሜው ከማግኘቱ በፊት በእስጢፋኖስ[2] አደባባይነት እንደሚታወቅ፣ ከ1967 ዓ.ም. መገባደጃ ጀምሮ በዘመነ ደርግ ‹‹አብዮት አደባባይ›› ይባል ነበር፡፡ኢሕአዴግ መንበረ ሥልጣኑን ከያዘ በኋላ ከ1984 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ቀድሞው መጠሪያ መስቀል አደባባይ መመለሱ ይታወቃል፡፡

ይህ ቦታ ሌሎች ሕዝባዊ ስብሰባዎች የፖለቲካ ሰልፎች(ታሪካዊውን የቅንጅት ሰልፍ ጨምሮ) እንዲሁም የስፖርት ፌስቲቫሎች እና ሌሎች ሰልፎች ይካሄዱበታል።

  1. ^ [1]
  2. ^ [2][3]