መስጴጦምያ (ከግሪክኛ፦ Μεσοποταμία /መሶፖታሚያ/፣ «ከወንዞች መካከል ያለችው አገር») ከጤግሮስ ወንዝ እና ከኤፍራጥስ ወንዝ መካከል ያሉት አገሮች ሁሉ ማለት ነው። አሁን ይህ አቅራቢያ በኢራቅ፣ ሶርያና ቱርክ ይከፋፈላል። በጥንት ሱመር፣ አካድ፣ ባቢሎን፣ አሦር፣ አራምና ሌሎችም ልዩ ልዩ መንግሥታት በነዚህ ወንዞች መካከል ይገዙ ነበር።