መካ
Appearance
መካ የሙስሊሞች ቅድስት ከተማ ስትሆን ካዕባ በመባል የሚታውቅ የአላህ ቤት ያለባትና በእስላም ልማድ «የዱአለም እምብርት» የተባለች ነች።
«የአለም እምብርት» በትክክለኛው ይህ ካዕባ የሚባለው መስጅድ አለሃረም ያለበት ቦታ ነው። በዚህ ክልል ማንኛውም አይነት ወንጀል መስራቱ ቅጣቱ ድርብ ነው። አደን ማደን እና ነፍስ መግደል ዛፍ መቁረትም ቢሆን ፈጽሞ የተከለከለ ነው።
በመካ በሚገኘው መስጊድ መስገድ ሌሎች መስጊዶች ከሚደረግ ሰላት በአንድ መቶሽ ጊዜ ይበልጣል። የወደቀ ገንዘብ አገኘሁ ተብሎ አይወሰድም ፡ለመስጊዱ አስተዳደር ማስረከብ ይገባል እንጅ!
ሰዎች በአለም ዙሪያ ለሃጅ እና ኡምራ ወደዚህ ከተማ ይጎርፋሉ፤ ምክንያቱም ካዕበቱል ሙሸረፋ ወይም ሃረም በመባል የሚታወቅ የአላህ ቤት መሆኑን ያምናሉ። በቁርዓን ዘንድ፣ ይህ የአላህ ቤት በኢብራሂምና በልጃቸው እስማኤል የተገነባ ነው።