መጋቢት ፲፰
Appearance
መጋቢት ፲፰፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፺፰ ኛው ዕለት ሲሆን፤ የበጋ ወቅት ፹፫ ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፷፰ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና በዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፷፯ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፰፻፸ ዓ/ም - ዓፄ ዮሐንስ እና የሸዋው ንጉሥ ምኒልክ ወሎ ቦሩ ሜዳ ላይ ተገናኝተው ንጉሥ ምኒልክ የንጉሠ ነገሥቱን የበላይነት መቀበላቸውን እና ዓፄ ዮሐንስ ደግሞ የምኒልክን በሸዋ ላይ ንጉሥነታቸውን በመቀበል በመሐላ ታረቁ። ንጉሠ ነገሥቱ ለንጉሥ ምኒልክም ዘውድ ጫኑላቸው።
- ፲፱፻፷፱ ዓ/ም - የሆላንድ 'ኬ.ኤል.ኤም' 'ቦይንግ ፯መቶ፵፮' ጥያራ እና የ'ፓን-አም' ቦይንግ ፯መቶ፵፮' ጥያራ በ'ካናሪ ደሴቶች፤ ቴኔሪፍ ጥያራ ጣቢያ ማኮብኮቢያ ላይ በጉም ምክንያት ተጋጭተው፣ የ'ኬ.ኤል.ኤሙ' ፪መቶ፵፰ ተሣፋሪዎች በሙሉ ሲሞቱ ከ'ፓን-አሙ' ተሣፋሪዎች መኻል ፫መቶ፴፭ ሞተው ፷፩ ሰዎች ተርፈዋል። ይኼ አደጋ በታሪክ ከተከሰቱት የጥያራ አደጋዎች በሙሉ እጅግ የባሰ አደጋ በመሆን ይታወቃል።
- መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፣ ዕለታዊ የታሪክ ድርጊት - የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ፓትረያርክ (፲፱፻፶፩ ዓ/ም)
- http://www.ethiopianreporter.com Archived ጃንዩዌሪ 24, 2005 at the Wayback Machine ኪንና ባህል፡ ሳምንቱ በታሪክ
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |