Jump to content

መጽሕፍ ቅዱስ

ከውክፔዲያ

ትምህርት አንድ

የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ እና የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ መካከል ያለው ልዩነትና አንድነት

በዚህ አጭር ጽሑፍ ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታና የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ ውስጥ የሁለቱም ልዩነታቸውንንና አስፈላጊነቱን አንዲሁም ምን ማለት እንደሆነ እናጠናለን፡፡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች አማካይነት የሚፈጠሩ ችግሮች ምን ምን እንደሆነና ችግሮችን እንዴት መፍታት እንዳለብን መመልከት ይቻላል፡፡ በመጨረሻም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተወሰኑ ሰዎች ብቻ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች እንዳላቸው በማሰብ ክርስቲያኖች በተቀበሉት በመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስያገለግሉ አይታይም፡፡ ከዚህ የተነሳ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አገልግሎት የሚደረገው በተከፋው ባለሙያ እየሆነ መምጣቱ፤ ሞያተኛ አገልጋይ በመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ምዕመናን ማገልገል ያለባቸውን አገልግሎቶችን ያስቀራል፡፡ ይህ በሚሆን

በት ጊዜ  ምዕመናን በመክልታቸው ማትረፍ አይችሉም፡፡ በዚህ አጭር ትምሀርት ውስጥ ስለመንስ ቅዱስ ስጦታዎች በዝርዝር አንማርም ምክንያቱም ትኩረታችን በሁለቱ መካከል ባለው ልዩነትና አስፈላጊነት ላይ ስለሆነ ነው፡፡


የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ብለን ስንል በመጽሕፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ የሚከተሉትን መንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ያካትታል፡፡ 1ኛ ቆሮ 12፡4-11፤ ሮሜ 12፡6-8፤ 1ኛ ጴጥ 4፡10-11፡፡

§  የመነጻት ስጦታዎች

ትንቢትን መናገር

በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር

በልሳኖች የተነገረውን መተርጎም

§  የመገለጥ ስጦታዎች

ጥበብን መናገር

እውቀትን መናገር

መናፍስትን መለየት

§  የኃይል ስጦታዎች

የመፈወስ ስጦታ

የታአምራት ስጦታ

እምነት

ከዚህ ከተጠቀሱት በተጨማሪም

§  የማስተማር ስጦታ

§  የማስተዳደር/የእረኝነት/ ስጦታ

§  የመስጠት ስጦታ

§  የማገልገል ስጦታ

§  ወንጌል የመስበክ ስጦታ

§  የመጋብነት ስጦታን ያካትታል፡፡

የፀጋ ስጦታዎች ቢሮዎች ደግሞ ከዚህ ይለያል፡፡ እነሱም

1.  የሐዋሪያነት ቢሮ

2.  የነቢይነት ቢሮ

3.  የመጋቢነት ቢሮ

4.  የወንጌላዊነት ቢሮ እና

5.  የአስተማሪነት ቢሮዎች ተብለው ይታወቃሉ፡፡


መግቢያ ላይ እንደተገለጸው በዚህ ትምህርት የምንዳስሰው ስለመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ዝርዝርና አጠቃቀማቸው ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ ስጦታ ምንድነው፤ መንፈስ ቅዱስ ፍሬ ምንድነው፤ የሁለቱም አስፈላጊነት፤ ልዩነት እንዲሁም በሁለቱ አማካይነት በቤተ ክርስቲያን ውስጥም በሆነ በአገልግጋዮች ዘንድ የሚፈጠሩ ክፍተቶችን ማየት ነው፡፡

ሁላችን መገንዘብ ያለብን ነገር ቢኖር በሁለቱም መካከል ያለውን ልዩነት ነው፡፡

ሀ) የመንፈስ ቅዱስ  ስጦታ እና የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ በክርስቲያን ህይወት ውስጥ እንዴት ይጀምራል?

መንፈስ ቅዱስ ስጦታ የክርስቶስ አካል የሆነችውን ቤተ ክርስቲያን ለማነጽ ወይም ለመገንባት ይሆን ዘንድ ለቅዱሳን ያለምንም ቅደመ ሁኔታ የተሰጠ ነው፡፡ ይህንን የሚያደርገው የሰው ትጋት ወይም ቅዱስ በመሆን ሳይሆን የእግዚአብሔር መንፈስ እንደወደደ የሚሰጥ ስጦታ ነው፡፡ ሰዎች በእግዚአብሔር ቤተ ስቆዩ ወይም ብዙ ዓመት ስያገለግሉ የሚሰጥ ስጦታ አይደለም፡፡ አንድ ሰው የትንቢትን  ወይም መናፍስትን የመለየትን ስጦታ ለመቀበል  ረዥም ዓመት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ማገልገል አይጠበቅበትም ወይም ከፍተኛ የተምህርት ደረጃ መማሪ አይጠበቅበትም፡፡ ይህ ማለት ረዥም ዘመን ወይም ከፍተኛ ትምህርቶችን በቤተ ክርስቲያው ውስጥ መማር አያስፈልግም እያልኩኝ አይደለም፡፡ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ረዥም ዓመት በአገልግሎት መቆየት ወይም ትምህርት መማረ በአገልግሎት ዘርፍ ውስጥ የራሱ የሆነ ጥቅም አለው፡፡ ሳሙኤል ገና ብላቴና ነው፡፡ ነገር ግን ካህኑ ኤል ግን በቤተ መቅደስ ውስጥ ረዥም ዕድሜን አስቆጥሮአል፡፡ አንድ ቀን የእግዚአብሔር ድምፅ ወደ ሳሙኤል ስመጣ አለወቀውም፤ ነገር ግን ኤልን ሄዶ በጠየቀ ጊዜ ስለ ደምፁ ባህሪይ ነገርው፡፡ በሌላ አገላለጽ መንፈስ ቅዱስ ስጦታ የሚሰጠው ረዥም ዕድሜ በእግዚአብሔር ቤተ ውስጥ በመቆየት አይደለም፡፡ መንፈስ ቅዱስ ስጦታ መንፈስ ራሱ እንደወደ ይሰጣል እንጅ!

አንድ አማኝ ውደ እግዚአብሔር መንግስት ከመጣ በኃላ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ያስፈልጋል፡፡ይህ ባልሆነበት ግን አንድ አማኝ ከመንፈስ ቅዱስ  ስጦታን ይቀበላል ማለት አይቻልም፡፡ ምክንያቱም የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ለአንድ አማኝ አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡ አማኝ መጸለይ የሚችለው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል መረዳት የሚችለው መንፈስ ቅዱስ ርዳታ ነው፡፡ መዋጋት የሚችለው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ብቻ ነው፡፡

አማኝ ህይወት ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ወዲያውኑ ከድነት ጋር በመፈጸም በአማኝ ውስጥ ያድራል እንዲሁም የዋስትና/ማህተም/ ምልክት ነው፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ወደ አዲስ ግኑኝነት የመግባታችን እውነት ነው፡፡ አንድ አማኝ በመንፈስ ጥምቀት ውስጥ የክርስቶስ አካል ይሆናል፡፡ 1ኛ ቆሮ 12፡13፡፡ ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ ሙላት ውስጥ ክርስቲያኖች የመንፈስ ቅዱስ  ስጦታን ይለማመዳሉ፤ በአገልግሎት ኃይል ይገለጣል፡፡ ድነት ካገኘ አጭር ጊዜ የሆነው አማኝ በመንፈስ ቅዱስ ሊመላና የመንፈስ ቅዱስ  ኃይል በህይወት ሊገለጥ ይችላል፡፡ በመንፈስ ቅዱስ በተለያየ ጊዜ እንዲንሞላ በተለያየ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ የተጠቀሰ ሲሆን የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ግን ከድነታችን ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምክንያቱም በመንፈስ ቅዱስ ሙላት ኃይል ይገለጣል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰዎች በተለያየ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተዋል፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት እንደቅደመ ሁኔታ የግለሰቡን ዝግጅት ይፈልጋል፡፡ ማጠቃለያ፤- በመንፈስ ቅዱስ ሙላት ውስጥ ክርስቲያኖች በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የመመላለስና የማደግ ጉልበትን ያገኛሉ፡፡ እንዲሁም የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን ይለማመዳሉ/ይገለጣል/፡፡

ወደ ተነሳንበት ርዕሰ ጉዳይ ስንመለስ፡- የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ በራሱ መንፈስ ቅዱስ አማካይነት የሚሰጥ እንደሆነ ተነጋግረናል፡፡ ነገር ግን የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ ከመንፈስ ቅዱስ የሚናገኝ ስጦታ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት የምናድግበት ነው፡፡ በክርስቲያን ህይወት ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ እንዲታይ፤ ክርስቲያኖች ከመንስ ቅዱስ ጋር የጠበቀ ህብረት ያስፈልጋል፡፡ በተለይም ትኩረት መስጠት ያለብን ጉዳይ ቢኖር፤

1.   መንፈስ ቅዱስን አላማሳዘን፤ ኤፌ 4፡30

መንፈስ ቅዱስ ለምን ያዝናል? መንፈስ ቅዱስ የምናሰዝነው እንዴት ነው? መንፈስ ቅዱስን የሚናሰዝን ከሆነ በተቃራኒው መንፈስ ቅዱስን ማስደሰት ይቻላል ማለት ነው፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ባልተደሰተባቸው ሁኔታ ሁሉ ያዝናል ማለት ነው፡፡

2.  መንፈስ ቅዱስን አለማጥፋት 1ኛ ተሰ 5፡19

ሌላኛው አስፈላጊ ነገር፤ መንፈስ ቅዱስን አለማጥፋት ነው፡፡ በሌላ አባባል ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ዘወትር መሆን ማለት ነው፡፡ በእርሱ መገኘት ውስጥ መሆን ለአንድ ክርስቲያን የመንፈስ ፍሬ ወሳኝነት አለው፡፡

3.  መንፈስ ቅዱስ መመላለስ ገላ 5፡16

ከላይ የተጠቀሱትን ጉዮች በመዝላል፤ የመንፈስ ቅዱስ ርዳታ ብንጠብቅ ምንም ዓይነት ዕገዛ አይኖረንም፡፡ ያለመንፈስ ቅዱስ ኃይል የመንፈስ ቅዱስ ፍሬን ማፍራት አንችልም፡፡ ሌላኛው የመንፈስ ቅዱስ ተግባር ሰዎችን ስለኃጢአት የሚወቅስ እና ወደ እውነት የሚመራ ነው፡፡ ሰው በኃጢኣት ውስጥ ሆኖ ወይም በእውነት መንገድ ላይ ሳይሆን የመንፈስ ቅዱስ  ፍሬን ማፍራት አይችልም፡፡

ከላይ የተመለከትነው የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ እና የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ በክርስቲያን ህይወት ውስጥ እንዴት እንደምጀምር ነው፡፡

ለ) በሰው ወይም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስገለጥ

ሐ) በሰው ዘንድ ሲተዩ

መ) በእግዚአብሔር ዘንድ ሲታዩ