ሚያዝያ ፳፪
Appearance
ሚያዝያ ፳፪'፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፴፪ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፳፯ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፴፬ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፴፫ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - በጄኔራል መንግሥቱ ንዋይ የሚመራው የክብር ዘበኛ ሠራዊት በሱሉልታ አካባቢ የጦር ታክቲክ ልምምድ አካሄደ። ይሄንን ልምምድ ብዙዎች የታኅሣሥ ግርግር ዝግጅት እና ትልቅ የማስጠንቀቂያ ደውል መሆኑን ይገምታሉ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ አብዮታዊ እንቅስቃሴ የ፪ተኛ ክፍለ ጦር ሰራዊት የአስመራ ከተማን በቁጥጥሩ ስር አዋለ። የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት የፖስታ እና ቴሌኮሙኒኬሽን ሚኒስትሩ ሌተና ጄኔራል አሰፋ አየነ በአብዮታዊ ወታደሮች በዚህ ዕለት እስር ላይ ሲውሉ፤ የመከላከያ ሚኒስቴር ደግሞ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበርን ሕገ-ወጥ አድማ ማካሄዱን ካላቆመ እንደሚዘጋ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።
- (እንግሊዝኛ) FCO 371/1829 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1974
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |