ሚያዝያ ፲፱
Appearance
(ከሚያዝያ 19 የተዛወረ)
ሚያዝያ ፲፱፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፳፱ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፳፬ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፴፯ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፴፮ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፱፻፲፯ ዓ/ም - በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት አልጋ ወራሽ እና ባለሙሉ ሥልጣን እንደራሴ 'የግል ገንዘብ' የተሠራውና በስማቸው የተሠየመው የተፈሪ መኰንን ትምሕርት ቤት ተከፈተ።
- ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - በኢትዮጵያ የካቶሊክ ዕምነት ተከታዮች ሃይማኖታዊ በዓላትን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር መሠረት ለማክበር መወሰናቸው ተገለጠ።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በእስፓኝ የሁለት ቀን ጉብኝታቸውን ጀመሩ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በብሪታኒያ በሚገኘው የሊቢያ ቋሚ ልዑካን መሥሪያ ቤት ደጅ ላይ አንዲት እንግላዚዊት የፖሊስ ባልደረባ በመገደሏ ምክንያት የብሪታኒያ መንግሥት ከሊቢያ ጋር የዲፕሎማቲክ ግንኙነቱን ከማቋረጡም ባሻገር፣ በዛሬው ዕለት የሊቢያን ልዑካን ካገር አስወጡ።
- ፲፱፻፷፬ ዓ/ም - የጋና የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር እና የመጀመሪያው ፕረዚደንት ዶክቶር ክዋሜ ንክሩማ በዚህ ዕለት በቡካሬስት፣ ሩማንያ የቆዳ ነቀርሳ ህክምና በመከታተል ላይ እንደነበሩ አረፉ። አስከሬናቸው ወደ ትውልድ አገራቸው ተመልሶ
በመዲናዋ በአክራ ተቀብሯል።
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FO 371/190144 Annual Review of 1965
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 31/1118፣ ETHIOPIA: ANNUAL REVIEW FOR 1971
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1829 ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1974
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |