ሚያዝያ ፳

ከውክፔዲያ
(ከሚያዝያ 20 የተዛወረ)

ሚያዝያ ፳፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፴ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፳፭ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፴፮ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፴፭ ቀናት ይቀራሉ።


ታሪካዊ ማስታወሻዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • ፲፱፻፴፯ ዓ/ም - የኢጣልያ የፋሺስት መሪ የነበረው ቤኒቶ ሙሶሊኒ ከነውሽማው ክላራ ፔታቺ ጋር በቀበሌ ታጣቂዎች ተይዞ በኮሎኔል ካሌሪዶ ከተረሸነ በኋላ አደባባይ ላይ ቁልቁል ተሰቀለ።
  • ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - የሆለታ ጦር ትምሕርት ቤት ብዙ የውጭ እንግዶች በተገኙበት የሃያ አምስተኛ የልደት በዓሉ ተከበረ።
  • ፲፱፻፶፱ ዓ/ም - ጥቁር አሜሪካዊው ቡጢኛ ሙሐመድ አሊ ወደአገሪቱ ጦር ሠራዊት ገብቶ የማገልገል ግዴታውን እንዲወጣ ቢጠየቅም አሻፈረኝ አለ። የዚያኑ ዕለት የዓለም ቻምፒዮናነቱን ማዕረግ በኒው ዮርክ የአትሌቲክ ባለ ሥልጣን ተገፈፈ።
  • ፲፱፻፸፰ ዓ/ም - በስዊድንፊንላንድ እና ኖርዌይ የሚገኙ የኑክሊዬር ምርመራ ማዕከላት ያልተለመደ የራዲዮ-አክቲቭ በከላ በምድር ጠፈር ላይ እንዳገኙ ባስታወቁ በሁለተኛው ቀን የሶቪዬት ኅብረት ባለ ሥልጣናት ቸርኖቢል የሚባለው የኑክሊዬር የመብራት ኃይል ማምረቻ አደጋ እንደደረሰበት ይፋ አደረጉ።

ልደት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዕለተ ሞት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዋቢ ምንጮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • (እንግሊዝኛ) P.R.O., FO 371/154836 Annual Report from Ethiopia for 1960


የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ