ሜትር

ከውክፔዲያ

ሜትር አለም አቀፍ መሰረታዊ የርዝመት መለኪያ አሀድ ነው። የተፈጠረው በፈረንሳይ የሳይንስ ትምህርት በፕላቲኒየም ላይ ባሉ ሁለት ነጥቦች መካከል ያለ ርቀት በማለት ነበር። ይህም ርቀት ይወክላል የሚባለው ከምድር ወገብ እስከ የመሬት ሰሜናዊ ጫፍ ድረስ ያለውን ርቀት አንድ አስር ሚሊዮንኛ ( 0.0000001 መቶኛ)ን ነው። ይህም በፓሪስ ሜሪዲያን ላይ ስንጓዝ ማለት ነው። በ1983 እ.ኤ.አ. አንድ ሜትር ብርሃን በ 1/299,792,458 ሰከንድ የሚጓዘው ርቀት ተደርጎ ተሰልቷል። ከሌሎች የርዝመት መለኪያ አሀዶች ጋር ለማነጻጸር 1 ሜትር ከ1000 ሚሊ ሜትር፣ 39.370 ኢንች ጋር እኩል ነው።