ምድረ ከብድ

ከውክፔዲያ

ምድረ  ከብድ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም  

በጉራጌ ዞን ውስጥ የሚገኝ ቀደምትና ታሪካዊ ገዳም ሲሆን የተመሰረተው በ12ኛው ክፍለ ዘመን በአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ ገዳሙ ከአዲስ አበባ ወደ ቡታጅራ ከተማ በሚወስደው መንገድ ከወረዳው ዋና ከተማ ቡኢ በስተምስራቅ በኩል 19 ኪ/ሜ ላይ ያገኙታል፡፡

ገዳሙ ህንፃ ቤተክርስቲያን በዳግማዊ አፄ ሚሊኒክ ዘመነ መንግስት በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንደተሠራና በኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣንና በጎ አድራጊ ግለሰቦች ታሪካዊ ይዘቱ ሳይለቅ በ2002 ዓ/ም እድሳት ተደርጓል፡፡ በገዳሙ ጥንታዊ የነገስታት ዘውድ፣ መስቀሎችና የብራና መጽሀፍት፣ ስዕላት … ወዘተ መዛግብቶች ይገኛሉ፡፡ እንዲሁም የተለያየ አገልግሎት የሚሰጡ ዕድሜ ጠገብና ዘመናዊ የእንግዳ መቀበያና ማረፊያ ቤቶች ተገንብተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገናሉ፡፡ እንዲሁም እጅግ በጣም ዘመናዊ የሆነ ሙዝየም ተገንብቶ በ2008 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡      

በገዳሙ መናንያን መነኮሳት የተሠሩ የእደ ጥበብ ውጤቶችና ቅርፃ ቅርጾች በስፍራው ማየትና መገበያየት ይቻላል፡፡ በክርስትና እምነት ተከታዮችና በታሪክ ተመራማሪዎች እየተጎበኘ ሲገኝ ከተለያየ የሀገሪቱ ክፍሎችና ከአካባቢው የሚመጡ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ጎብኚዎች በየዓመቱ ጥቅምት 5 እና መጋቢት 5 በስፍራው ይታደማሉ፡፡