ሮቦት

ከውክፔዲያ
የሰው ሴት እንድትመስል ተደርጋ የተሰራች የጃፓን ሮቦት። በርግጥም መራመድና አንድ አንድ ቃላትንም መናገር ትችላለች።

ሮቦት ማለት በምናባዊው አለም ሆነ በተጨባጭ ያለ ሰው ሰራሽ ስራ ፈጻሚ ነው። ይህ አጠቃላይ ትርጉሙ ሲሆን በውኑ አለም ግን ሲተገበር የምናየው በተንቀሳቃሽ የኤሌክትሪክ መሳሪያወች ነው። ሮቦቶች ብዙ ጊዜ በኮምፒውተር የሚታዘዙ ይሁኑ እንጂ በኤሌክትሪክ ትዛዝም ቀልጥፈው እንዲሰሩ የሚደረግበት ጊዜ አለ። ሮቦትን ከሌሎች አይነት የሰው ልጅ መሳሪያወች የሚለየው አንድን ስራ የሚሰራው በራሱ መሆኑ ነው።