ሳት

ከውክፔዲያ
(ከ የተዛወረ)

ሰ ሱ ሲ ሳ ሴ ስ ሶ ሷ



አቡጊዳ ታሪክ

ሳት (ወይም ሰዓት) በጥንታዊ አቡጊዳ ተራ 15ኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓንአራማያዕብራይስጥ ፊደሎች 15ኛው ፊደል "ሳሜክ" በሶርያም ፊደል "ሲምኬት" ይባላል። በዓረብኛ ግን ተመሳሳይ ፊደል የለም፣ ለዚሁ ድምፅ ከ"ሺን" የተወሰደ ፊደል በሱ ፈንታ አለ።

አማርኛ አጻጻፍ ብዙ ጊዜ "ሳት" ከ"ሠውት" (ሠ) ጋራ ሊለዋውጥ ይችላል። ቀድሞ ግን በግዕዝ የ"ሠውት" ድምጽ "ሸ" ለማመልከት ይጠቅም ነበር። በዛሬው አማርኛ "ሸ ሹ ሺ ሻ ሼ ሽ ሾ" ከ"ሰ..." ትንሽ ተቀይሯል።

ታሪክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ተመሳሳይ ግብፃዊ ስዕል ሣባ ግዕዝ
R11


የሳት መነሻ ግልጽ አይደለም። ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ቢታስብም እስካሁን አልተገኝም። ለዚህም ምናልባት ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር። አንዳንድ ሊቃውንት የ"ዓምድ" ("ጀድ") ስዕል እንደ ነበር ይገምታል።

ከነዓን አራማያ ዕብራይስጥ ሶርያ ዓረብኛ
ሳሜክ ሳሜክ ס ሳሜክ


የከነዓን "ሳሜክ" እንዲሁም ከዚህ ምልክት ተወስዶ በዚያ መንገድ የዕብራይስጥና የአራማያም "ሳሜክ" ወለደ። ከዚህ በላይ የግሪክ አልፋቤት "ክሲ" (Ξ, ξ) ምናልባትም የ"ክሒ" (Χ, χ) አባት ሆነ። "ክሒ" የላቲን አልፋቤት (X x) ወላጅ ሆነ። ስለዚህ እነዚህ ሁሉ የ"ሳት" ሩቅ ዘመዶች ሊባሉ ይቻላል። በተጨማሪ የግዕዝ ቁጥር (ስልሳ) ከግሪኩ Ξ በመወሰዱ እሱም የ"ሰ" ዘመድ ነው።