ሰኸቀንሬ

ከውክፔዲያ
ሰኸቀንሬ ሳንኽፕታሂ
ሰኸቀንሬ ዘይት ለጣኦት ሲያቅርብ
ሰኸቀንሬ ዘይት ለጣኦት ሲያቅርብ
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1646 ዓክልበ. ግ. ?
ቀዳሚ መርኸፐሬ ?
ተከታይ ሰኸምሬ ጀሁቲ ?
ሥርወ-መንግሥት 13ኛው ሥርወ መንግሥት


ሰኸቀንሬ ሳንኽፕታሂላይኛ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ምናልባት 1646 ዓክልበ. አካባቢ የገዛ ፈርዖን ነበረ።

የሰኸቀንሬ ጽላት በሙሉ

ዘመኑ በሂክሶስ ጦርነት ዘመን ውስጥ እንደ ነበር ይመስላል። ከመርካውሬ 7 ሶበክሆተፕ ቀጥሎ እነማን በጤቤስ እንደ ገዙ ግልጽ አይደለም፤ ብዙ ስሞች ከቶሪኖ ቀኖና እንደ ጠፉ ይመስላል። ከሥነ ቅርስ የተረጋገጡት ግን መርኸፐሬ እና ሰኸቀንሬ ብቻ ናቸው። በቶሪኖ ዝርዝር ላይ «-ቀንሬ» የሚል ብቻ ሊነብብ ይቻላል። ከዚህ ውጭ ስሙ ሰኸቀንሬ ሳንኽፕታሂ ይታወቀው ከአንድ ጽላት ብቻ ነው። ጽላቱ ከመጀመርያው ዓመት ሲሆን ለጣኦቱ ዘይት በአረመኔ ሥነ ስርዓት ሲያቀርብ ያሳያል።

ከ13ኛ ሥርወ መንግሥት በኋላ ሂክሶስ የጤቤስን ሃያላት እንዳሸነፉት ይመስላል። እንደገና ከወጡ በኋላ በፈንታው የ16ኛ ሥርወ መንግሥት ፈርዖን ሰኸምሬ ጀሁቲ እንደ ተነሣ ይታስባል። በአቢዶስም አንድ ነጻ ሥርወ መንግሥት (የአቢዶስ ሥርወ መንግሥት) እንደ ተነሣ ይታስባል።

ቀዳሚው
መርኸፐሬ ?
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን
1646 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሰኸምሬ ጀሁቲ ?