ሲድና ማርቲ ክሮፍት

ከውክፔዲያ
ማርቲ ክሮፍት በ1954 ዓም

ሲድ ክሮፍት (1921 ዓም- ፣ የልደት ስም /ኪዶስ ዮላስ/) እና ማርቲ ክሮፍት (1929 ዓም- ፣ የልደት ስም ሞሾፖፑሎስ ዮላስ) ዝነኛ የቴሌቪዥን ትርዒት ፕሮዲውሴሮችና ጸሐፊዎች የሆኑ ሁለት ግሪካዊ-ካናዳዊ ወንድሞች ናቸው። በተለይ በ1970ዎቹ እ.ኤ.አ. ያህል ላደጉት አሜሪካዊ ልጆች ላይ በየቅዳሜ ጧቱ ይታዩ በነበሩት ትርኢቶቻቸው በኩል ከፍተኛ ተጽእኖ አሳድረዋል።

1940ዎቹ እ.ኤ.አ. ጀምሮ አንጋፋ የአሻንጉሊት አጫዋቾች በመሆናቸው ታውቀው ነበር። የልጆችና ሕፃናት ቅዳሜ ጧት ትርዒቶች መሥራት የጀመሩ በ1968 እ.ኤ.አ. ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ብዙ ደስ የሚሉ ልቦለዳዊ ትይንቶቻቸው እስካሁን ድረስ ይታወሳሉ።

ዝነኛ ትርኢቶች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ከዚህም አንጋፋ ዘመን በኋላ እስካሁን ድረስ በአንዳንድ ሌሎች ትርዒቶች ላይ ተሳትፈዋል። ትርዒቶቹም አሁንም በኢንተርኔት ሊታዩ ስለሚቻል አዳዲስ ወዳጆች አገኝተዋል።