ስዕል:AmharicTeretinaMisale.pdf

ከውክፔዲያ
ወደ ገጽ# ለመሄድ
የሚቀጥለው ገጽ →
የሚቀጥለው ገጽ →
የሚቀጥለው ገጽ →

ዋና ፋይል(1,275 × 1,650 pixels, file size: 368 KB, MIME type: application/pdf, 106 pages)

ተረትና፡ምሳሌ

(ከልዩ፡ልዩ፡ምንጮች፡የተቀዳ....



   አበቢላ፥የመስከረም፡ጠላ።
   አቡጊዳ፥የተማሪ፡ዕዳ።
   አባ፥ልብሱ፡ዳባ፤ውስጡ፡ደባ።
   አባያ፡ቢቀና፥ቤት፡ያቀና።
   አባይ፡ማደሪያ፡የለው፥ግንድ፡ይዞ፡ይዞራል።
   አባይን፡ያላየ፡ምንጭ፡ያመሰግናል።
   አባት፡ያበጀው፡ለልጅ፡ይበጀው።
   አባት፡ሳለ፡አጊጥ፥ጀንበር፡ሳለ፡ሩጥ።
   አገባሻለኹ፡ያለሽ፡ላያገባሽ፥ከባልሽ፡ሆድ፡አትባባሽ።
   አጓቱን፡ሲያዩት፥ዐይቡን፡ጨለጡት።
   አደባባይ፥አይወድም፡ዐባይ።
   አደንጓሬ፥የኽል፡አውሬ።
   አህያ፡የለኝም፤ከዥብ፡አልጣላም።
   አወን፡ባይ፡ዕዳ፡ከፋይ።
   አዘዞ፥አንድም፡ተናዞ፥አንድም፡ሥንቅ፡ይዞ።
   አጥብቆ፡ጠያቂ፡እናቱን፡ይረ፟ዳ፟ል።
   አያድርስ፡የባል፡ቢስ።
   አይበሉት፡እኽል፡ካፈር፡አንድ፡ነው።
   አይጠቅም፡ጠላ፥ባልና፡ሚስት፡ያጣላ።
   አይጥፍ፡ደብተራ፤ክንፍ፡የለው፡አሞራ።
   አለባለቤቱ፡አይነድም፡እሳቱ።
   አለዳኛ፡ሙግት፤አለገመድ፡እክት።
   አለዋዛው፡ዋዛ፥ቅቤም፡አያወዛ።
   አለው፡አለውና፥ሳይመታው፡ቀረ።
   አላባት፥ጐመን፡ባጓት።
   አላባት፥ዦሮ፡በጡጫ።
   አላዋቂ፡ቤት፡እንግዳ፡ናኘበት።
   አላዋቂ፡ሳሚ፡ንፍጥ፡ይለቀልቃል።
   አላቻ፡ጋብቻ፥ቈይ፡ብቻ፥ቈይ፡ብቻ።
   አሞራውም፡በረረ፥ቅሉም፡ተሰበረ።
   አንበሳ፡ምን፡ይበላል፧ተበድሮ፤ምን፡ሊከፍል፧ማን፡ተናግሮ።
   አንበሳ፡ሲያረጅ፡የዝንብ፡መጫወቻ፡ይኾናል።
   አንዱ፡ባንዱ፡ሲሥቅ፥ጀንበር፡ጥልቅ።
   አንዱን፡ጥሎ፥አንዱን፡አንጠልጥሎ።
   አንድ፡አይነድ፤አንድ፡አይፈርድ።
   አንድ፡በሬ፡ስቦ፥አንድ፡ሰው፡አሳቦ።
   አንድ፡ያላት፡እንቅልፍ፡የላት።
   አንድ፥ከደግ፡ተወለድ፤አንድ፥ከደግ፡ተጠጋ።
   አንድ፡ዓመት፡በወዝ፥አንድ፡ዓመት፡በደመ፡ወዝ።
   አንጣሪያ፡ላንጣሪያ፡ቢደጋገፍ፥ተያይዞ፡እዘፍ።
   አንቃ፡ላንቃ፡ቢደጋገፍ፥ተያይዞ፡እዘፍ።
   አንቃ፥ለራሱ፡አይበቃ።
   አትኵራ፡ገብስ፥ጐመን፡ባወጣው፡ነፍስ።
   እባብ፡ግደል፤ከነበትሩ፡ገደል።
   እኽል፡የያዘ፥ፈርዛዛ፤ወርቅ፡የያዘ፡ቀበዝባዛ።
   እኽል፡ከበዩ፤ሰው፡ከገዳዩ።
   እናት፡ለልጇ፡ጠንቋይ፡ናት።
   እንዳየን፡ጤፍ፡አጋየን።
   እንስራዋን፡ትታ፥ውሃ፡ወረደች።
   አንቱ፡ትተረጕሙ፤አንቱ፡ትደረግሙ።
   አንቱም፣አንቱም፡አትዋሹ፥ወደ፡ጓሮ፡ልትሸሹ።
   አፍ፡ቢሳሳት፥ዕዳ፤እግር፡ቢሳሳት፡አንጋዳ።
   አፍ፡ያለው፡ጤፍ፡ይቈላል።
   አፍ፡ሲከዳ፡ከሎሌ፡ይብሳል።
   አፍኣው፡ሰንሰለት፥ውስጡ፡ዐውደ፡ነገሥት።
   አፍጣኝና፡አቅጣኝ፥እመዳሮ፡እንገናኝ።
   አራሪ፡ለማራሪ፤ማራሪ፡ለበራሪ፡ይተው።
   አሰድ፥የያዘውን፡አይሰድ።
   እባብ፡ግደል፥ከነበትሩ፡ገደል።
   እባብ፡ያየ፥በልጥ፡በረየ።
   እባብን፥ልቡን፡አይቶ፡እግር፡ነሣው።
   እብድ፡የያዘው፡መልክ፡አይበረክትም።
   እብድና፡ዘመናይ፡የልቡን፡ይናገራል።
   እገድል፡ያለ፡መጋኛ፤እበላ፡ያለ፡ዳኛ።
   እግዜር፡ሳይደግስ፡አይጣላም።
   እግር፡ይብሳል፤ያበሰብሳል።
   እጅግ፡ስለት፡ይቀዳል፡አፎት፤እጅግ፡ብልኀት፡ያደርሳል፡እሞት።
   እያየዃት፡የምታሥቀኝ፡ሚስት፡አገባኹ።
   እካስ፡ያለ፡ታግሦ፥እጸድቅ፡ያለ፡መንኵሶ።
   እኽል፡አላምጦ፤ነገር፡አዳምጦ።
   እምዬ፥ጣጣሽ፡በዛዬ።
   እናቱ፡ውሃ፡የኼደችበትና፡የሞተችበት፡እኩል፡ያለቅሳሉ።
   እኔ፡ዐውቃለኹ፡የቆቅን፡መላ፤ወይ፡በራለች፥ወይ፡ደፍጣለች።
   እንግዴህ፡ለርጥ፥አምሮቴ፡ቍርጥ።
   እንደ፡እንግዳ፡ደራሽ፤እንደ፡ውሃ፡ፈሳሽ።
   እንደ፡የቦ፡ሰልቶ፥እንደ፡ቈንዦ፡ደርቶ።
   እንዲያውም፡በመላ፥ፈስ፡ዳልቻ፡ነው።
   እንዳገሩ፡ይኖሩ፤እንደ፡ወንዙ፡ይሻ፟ገ፟ሩ።
   እንዳያማኽ፡ጥራው፤እንዳይበላ፡ግፋው።
   እንዳንድ፡ቃል፡ተናጋሪ፤እንዳንድ፡ሰው፡መስካሪ።
   እንዶድን፡በገርነቷ፡ውሃ፡ወሰዳት።
   እንጀራን፡ከባዕድ፥መከራን፡ከዘመድ።
   እንጃ፥ባፍኽ፡ሙሉ፡ዥብ፡ይንጃጃ።
   እንቅልፍ፡ታበዢ፥ከነብር፡ትፋዘዢ።
   እንትኑን፡በንትን፡አደረገው፡ብትንትን።
   እንትን፡አልንበት፡እንትን፡ገባበት፤እንትን፡አምጪልኝ፥እንትን፡እልበት፤አንቺም፡ነዪ ልኝ፡እንትን፡ትዪልኝ።
   እኛ፡ባገራችን፥ዳቦ፡ፍሪዳችን።
   እጸድቅ፡ብዬ፡ባዝላት፥ተንጠልጥላ፡ቀረች።
   እራትና፡እሳት፥ዐማትና፡ምራት፤ሳይስማሙ፡መሬት።
   እርጅና፥ብቻኽን፡ና።
   እሰር፡በፍንጅ፤ጣል፡በደጅ።
   እሳት፡ቢዳፈን፡የጠፋ፡ይመስላል።
   እሳት፡ለፈጀው፡ምን፡ይብጀው፧
   እታዘዝክበት፡አውለኻቸው፥ሽፍታ፡በወሰዳቸው።
   በ
   በበላኽ፡ገብር፤በሰማኽ፡መስክር።
   በባዳ፡ቢቈጡ፤በጨለማ፡ቢያፈጡ።
   በገዛ፡ዳቦዬ፡ልብ፡ልቡን፡ዐጣኹት።
   በደንባሪ፡በቅሎ፥ቃጭል፡ተጨምሮ።
   በድንገት፥አህያ፡ገባ፡እዥብ፡ቤት።
   በጠረጠሩ፥ጠጠር፡ይጥሉ።
   በጨው፡ደንደስ፥በርበሬ፡ተወደስ።
   በኔ፡ሲያዩብኝ፡፥ባንቺ፡ይዩብሽ።
   በምድር፡አይቀር፡ብድር።
   በዕውር፡ይጠቃቀሱበታል፤በደንቈሮ፡ይሾካሾኩበታል።
   በዓል፡ሽሮ፡የከበረ፥ጦም፡ገድፎ፡የወፈረ፡የለም።
   በራት፡ዋዛ፥መሳ፡ይመስል።
   በቅሎ፥አባትኽ፡ማን፡ነው፡ቢሉት፥እናቴ፡ፈረስ፡ነች፡አለ።
   በቈማጣ፡ቤት፡አንድ፡ጣት፡ብርቅ፡ነው።
   በሬ፡ሆይ፥ሣሩን፡አየኽና፡ገደሉን፡ሳታይ።
   በሰው፡ቍስል፡ዕንጨት፡ስደድበት።
   ቢተኙ፥ነገር፡ያገኙ፤ቢነሡ፥ነገር፡ይረሱ።
   ባይገባቡ፥በደጃፍ፡ይገቡ።
   ባለቤት፡ቢያፍር፥እንግዳ፡ይጋብዝ።
   ባለቤት፡ካልጮኸ፥ጎረ፡ቤት፡አይረዳም።
   ባለጌ፡የጠገበ፡ዕለት፡ይርበው፡አይመስለውም።
   ባለጌን፥ካሳደገው፡የገደለው፡ይጸድቃል።
   ባላዋቂ፡ቤት፡እንግዳ፡ናኘበት።
   ባልንጀራዬ፡ሲበልጠኝ፥ቍንጣን፡ይፍለጠኝ።
   ባልነቃ፡ሠንጥቆ፤ባልደመነ፡በርቆ።
   ባልና፡ሚስት፥ሎሚ፡ከኹለት።
   ባልንጀራዬ፡ሲበልጠኝ፥ቍንጣን፡ይፍለጠኝ።
   ባንድ፡አጕራ፡ኹለት፡አውራ።
   ባፍ፡ይጠፉ፥በለፈለፉ።
   ባቄላ፥የራብ፡ዱላ።
   ባሪያ፥አጋዥ፡ብታገኝ፥መጅ፡ደበቀች።
   በረት፡ካልፈላ፥አይላላ።
   ብርሌ፡ተነቃ፥አይኾንም፡ዕቃ።
   ብርቅና፡ድንቅ፥አላንድ፡ቀን፡አይደምቅ። / ጕድና፡ድንቅ፥አላንድ፡ሰሞን፡አይደምቅ።
   ቦይ፡ለውሃ፥ጐመን፡ለድኻ።


   ገ
   ገበጣ፥ገበጥባጣ፥ከኢየሩሳሌም፡የመጣ።
   ገቢኽን፡ሳታውቅ፡ይሉኝ፡አትበል።
   ገባርና፡ድግር፥ሲተካከል፡ያምር። / ድግርና፡ገባር፡ሲተካከል፡ያምር።
   ገብስ፥የኽል፡ንጉሥ።
   ገዳይ፡በበለሱ፤ድኻ፡በንጉሡ።
   ገንዘብ፡የተውሶ፥ጠፋ፡ተጨርሶ።
   ገንዘብ፡ካለ፥በሰማይ፡መንገድ፡አለ።
   ገንፎ፥እፍፍ፡ቢሉኽ፥ሊውጡኽ።
   ጌታ፡ያዛል፤ውሃ፡ይነ፟ዛ፟ል።
   ጐኑ፡የኔ፤ቀኑ፡ሠኔ።
   ጕድና፡ድንቅ፥አላንድ፡ሰሞን፡አይደምቅ።


   ደ
   ደግ፡አድራጊ፡አበደረ፤ክፉ፡አድራጊ፡ተገደረ።
   ደግ፡ጎረ፡ቤት፡ውሻ፡ያሳድጋል፤ክፉ፡ጎረ፡ቤት፡ግን፡ዶሮ፡ያረባል።
   ደብተራ፥የዘኬ፡ጐተራ።
   ደግ፡ብሠራ፡የጠሉኝ፤ክፉ፡ባደርግ፡ምን፡ይሉኝ።
   ደግ፡ዐማጭን፡መጦር፤ክፉ፡ዐማጭን፡በጦር።
   ደጃፍ፡የመለሰው፤ማጀት፡የጐረሰው።
   ደፋር፡ወጥ፡ያውቃል።
   ደፋርና፡ጭስ፡መውጫ፡አያጣም።
   ዳቦ፡ሲያይ፥ልብ፡ልቡን፤ዳገት፡ሲያይ፥ጥግ፡ጥጉን።
   ዳገት፡ዕርሙ፤ሜዳ፡ወንድሙ።
   ዳኛ፡ሲገኝ፥ተናገር፤ውሃ፡ሲጠራ፥ተሻገር።
   ድኻ፡በቤቱ፡ንጉሥ፡ነው።
   ድኻ፡ቢናገር፡አያደምቅ፤ቢጨብጥ፡አያጠብቅ።
   ድኻ፥ይበላው፡እንጂ፥ይከፍለው፡አያጣም።
   ድኻ፡ተበድሎ፥ማሩኝ፡ይላል፡ቶሎ።
   ድመትን፡በቈሎ፡መጠርጠር።
   ድንቢጥ፡እንዳቅሟ፡በብር፡ትታገማለች።
   ድር፡ቢያብር፥አንበሳ፡ያስር።
   ዶሮ፥ሲሉ፡ሰምታ፥ሞተች፡እጪስ፡ገብታ።


   ሀ
   ሆድ፡ባዶ፡ይጥላል።
   ሆድ፡ያባውን፡ብቅል፡ያወጣዋል።
   ሆድ፡ሲያውቅ፡ዶሮ፡ማታ።
   ሆድ፡ሲያር፡ጥርስ፡ይሥቃል።


   ወ
   ወዶ፡ገባ፥ልብሱ፡ዳባ።
   ወይ፡ጣጣ፤በዚህም፡አያስወጣ።
   ወር፡አይጸድቅ፥አቦን፡አይጠምቅ፡የለም።
   ወርቅ፡ላበደረ፡ዐፈር።
   ውሃ፡ቢወቅጡ፥እንቦጭ።
   ውሻን፡በርግጫ፡ማለት፦ዕንካ፡ሥጋ፥ማለት፡ነው።
   ዋና፡ከቤት፤ጠበቃ፡ከዱለት።


   ዘ
   ዘማት፡ለባልንጀራው፦እኔ፡የገደልኹት፡ደም፡አልወጣውም፡ቢለው፦ቤት፡ሠሪውን፡ገድለኽ፡ ይኾናል፡አለው፡ይባላል።
   ዘሩ፡የጣቴ፤ምድሩ፡ያባቴ።
   ዘር፡ከልጓም፡ይጠቅሳል።


   ዠ
   ዥብን፡ሊወጉ፡ባህያ፡ይጠጉ።
   ጠ
   ጠጅ፡በብርሌ፤ዜማ፡በሃሌ። / ጠጅ፡በብርሌ፤ነገር፡በምሳሌ።
   ጠላት፡ይቀባ፟ል፡ጥላት።
   ጠንቋይ፡ለራሱ፡አያውቅም።
   ጠፍር፡በሊታ፡ብትኼድ፥ልጓም፡በሊታ፡መጣች።
   ጣዝማ፡ይሰረስራል፤ዳኛ፡ይመረምራል።
   ጣመኝ፤ድገመኝ።
   ጥምድ፡እንደ፡በሬ፤ቅንት፡እንደ፡ገበሬ።
   ጥፌ፥ለጭፌ።
   ጥርስና፡ከንፈር፥ሲደጋገፍ፡ያምር።
   ጦጣ፥ባለቤትን፡ታስወጣ።


   የ
   የእብድ፡አሞራ፥ሲላ፡ደንገጥሯ።
   የበላ፡በለጠ፤የሮጠ፡አመለጠ።
   የበላን፡ያብላላዋል፤የለበሰን፡ይበርደዋል።
   የበሬ፡ዶሰኛ፥የሴት፡ምላሰኛ፥አታምጣ፡ወደኛ።
   የበሬን፡ውለታ፡አህያ፡ወሰደች።
   የባል፡ደግነቱ፥ባትናገር፡ሚስቱ።
   የደላው፡ሙቅ፡ያኝካል።
   የዘሬን፡ብተው፡ያንዘርዝረኝ።
   የኅት፡ልጅ፥ባይወልዱትም፡ልጅ።
   የኽል፡ክፉ፥ዐጃ፤የሣር፡ክፉ፥ሙጃ፤የነገር፡ክፉ፥እንጃ።
   የጅ፡ብልኀት፥ባርነት፤ያፍ፡ብልኀት፥ጌትነት።
   የኃጥኡ፡ዳፋ፥ጻድቁን፡አዳፋ።
   የጠበኛ፡ፈስ፡ዐይን፡ፋስ።
   የካባን፡ራብ፥የዳባን፡ጥጋብ፡የሚያውቅ፡የለም።
   የላሜ፡ልጅ፥ያውራዬ፡ውላጅ።
   የሌባ፡ዐይነ፡ደረቅ፥መልሶ፡ልብ፡ያደርቅ።
   የሌባን፡ጠበቃ፥አደባልቀኽ፡ውቃ።
   የልጅ፡ጥፉ፥በስም፡ይደግፉ።
   የሚያድግ፡ልጅ፡አይጥላኽ፤የሚሞት፡ሽማግሌ፡አይርገምኽ።
   የማይፈወስ፡ድውይ፤የማይመለስ፡ጊጉይ።
   የምጣዱ፡ሳለ፥የዕንቅቡ፡ተንጣጣ።
   የሞተውን፡አያ፡ይለዋል።
   የነገር፡ጣም፡በዦሮ፤የኽል፡ጣም፡በጕረሮ።
   የጠገራ፡ላም፥ባደረችበት፡በረት፡እበት፡አይገኝም።
   የጠረጠረ፥ቤቱን፡ዐጠረ።
   የመዝሙር፡መዠመሪያ፡ሃሌታ፤የዘፈን፡መዠመሪያ፡እስክስታ።
   የነገር፡ወጡ፥ማዳመጡ።
   የፈሪ፡በትር፥ዐሥር።
   የፉክክር፡በር፡ሳይዘጋ፡ዐደረ።
   የረዘመውን፡በጦር፥ያጠረውን፡በድግር።
   የራሷን፡አበሳ፡በሰው፡አብሳ።
   የሰው፡ገንዘብ፡አይጠገብም።
   የሰው፡ወርቅ፡አያደምቅ።
   የስንዴ፡ዐራራ፥የቈንዦ፡መራራ።
   የሹሮ፡ድንፋታ፥እንጀራ፡እስኪመጣ።
   የሺ፡ፍልጥ፥ማሰሪያው፡ልጥ።
   የተጠማ፡ከፈሳሽ፤የተበደለ፡ከነጋሽ።
   የተከፋ፡ተደፋ።
   የተናገሩት፡ከሚጠፋ፥የወለዱት፡ይጥፋ።
   የታዘለ፡በለምድ፥የተረገዘ፡በሆድ።
   የታጠበ፡እጅ፥ያልባለቀ፡ልጅ።
   የቸገረው፡ዱቄት፡ከነፋስ፡ይጠጋ።
   የት፡ነው፡አገርኽ፧አህያ፡ፈጅ።ከማዞር፡ከመጠምጠም፡እንዲያው፡ዥብ፡ነኝ፡አትልምን፧
   የትም፡ፍጪው፥ዱቄቱን፡አምጪው።
   የትም፡ተወለድ፤አንኮበር፡እደግ።
   ያቡን፣የጨጌ፡ከብት፥በየወገኑ፡ይከተት።
   ያባያ፡ልጅ፡ወዳቂ፥ያራኝ፡ልጅ፡አጥባቂ።
   ያባት፡ወዳጅ፤የደንጊያ፡ገድጋጅ።
   ያህያ፡ባል፡ከዥብ፡አያስጥል።
   ያወቀ፥ተጠነቀቀ፤የዘነጋ፥ተወጋ።
   ያውሬ፡ሥጋ፥ለወሬ።
   ያኵራፊ፡ምሳ፡ራት፡ይኾናል።
   ያለኽ፡ምዘዝ፥የሌለኽ፡ፍዘዝ።
   ያልገደለ፡ዘማች፤ያልወለደ፡ዐማች።
   ያልወለድኹት፡ልጅ፡አባባ፡ቢለኝ፤አፌን፡ዳባ፡ዳባ፡አለኝ።
   ያልጠረጠረ፡ተመነጠረ።
   ያልተሾመ፡አያዝ፤ያልቀሰሰ፡አይናዝዝ።
   ያመኑት፡ፈረስ፥በደንደስ።
   ያምራል፡ብሎ፡ከመናገር፥አያምርም፡ብሎ፡መተው።
   ያምሯል፤ይታደሏል።
   ያፍ፡ዘመድ፥በገበያም፡አይገድ።
   ያረገዘች፡ታስታውቅ፥ከደረቷ፡ትታጠቅ።
   ያረረበት፡ያማስላል።
   ያራኝ፡ልጅ፥አጥባቂ፤ያባያ፡ልጅ፥ወዳቂ።
   ያስቡት፡አይገድ።
   ያተር፡ክምር፥የጪሰኛ፡ክብር።
   ይሉኝታ፥የራስ፡ዐሊን፡ቤት፡የፈታ።
   ይሉኝታና፡መጠቀም፡ባንድነት፡አይገኝም።
   ይመስል፥አይመስል፤የጠይብ፡እጁ፡ተከሰል።


   ከ
   ከበሮ፥በሰው፡እጅ፡ያምር፤ሲይዙት፡ያደናግር።
   ከጌታ፡ግልምጫ፥ከዳገት፡ሩጫ፥ከባለጌ፡ጡጫ፥(ሰውረኝ)።
   ከዳቦ፡የተገኘ፡ወጥ፥ዐብረኽ፡ግመጥ።
   ከገንዘብ፡ርስት፥ከከብት፡እንስት።
   ከባለቤት፡ያወቀ፡ቡዳ፡ነው።
   ከወገብ፡በታች፡ጣዖት፤ከወገብ፡በላይ፡ታቦት።
   ከወገኑ፡የተለየ፡አንበጣ፡ይኾናል፡ፌንጣ።
   ከጥላ፡ያረፉ፤ከሞት፡የተረፉ።
   ከይሉኝ፡አይል፡ዐይብ፡አትብላ፤አይመረው፥አይተኵሰው፤ውጦ፥ውጦ፡ይጨርሰው።
   ከክፉ፡ባለዕዳ፡ጐመን፡ዘር፡ተቀበል።
   ከልጅ፡አትጫወት፤ያወጣኻል፡በንጨት።
   ከልጅ፡ክፉ፥ዲቃላ፤ከኽል፡ክፉ፥ባቄላ፤ከልብስ፡ክፉ፥ነጠላ።ጠላት፡ይገፋል፡ዲቃላ፤ራብ ፡ይከላል፡ባቄላ፤ቀን፡ያሳልፋል፡ነጠላ።
   ከመደብደብ፡ይሻላል፡ማደብ።
   ከመጠምጠም፥መማር፡ይቅደም።
   ከመልካም፡ጠላ፥ክፉ፡ጠጅ፤ከመልካም፡ጎረ፡ቤት፥ክፉ፡ልጅ።
   ከመምሩ፥ደቀ፡መዝሙሩ።
   ከመረቁ፡አውጡልኝ፤ከሥጋው፡ጦመኛ፡ነኝ።
   ከመቶ፡ዐምሳ፡ዳዊት፥የልብ፡ቅንነት።
   ከሜዳ፡ወዲያ፡ፈረስ፥ካርባ፡ወዲያ፡ቄስ።
   ከምድር፡አደላድሎ፡ካህያ፤ከቡላድ፡አደላድሎ፡ከቋያ።
   ከነገረኛ፡ሰው፡ሥንቅ፡አይደባልቁም።
   ከነገሩ፥ጦም፡ዕደሩ።
   ከኛ፡ወዲያ፡ጐራሽ፥እኽል፡አበላሽ።
   ከናት፡ወዲያ፡ዘመድ፥ከቃጫ፡ወዲያ፡ገመድ።
   ከሩቅ፡ዘመድ፥የቅርብ፡ጎረ፡ቤት።
   ከሰው፡ክፉ፥ደባል፤ከጭነት፡ክፉ፥አላል።
   ከሰው፡ክፉ፥ደብተራ፤ካውሬ፡ክፉ፥ዳሞትራ።
   ከሰው፡ቀለብላባ፥ከመሬት፡ገብጋባ።
   ከሺ፡ደብተራ፥የቄስ፡ደንካራ።
   ከሺ፡ምስክር፡የታቦት፡እግር።
   ከተሟጋች፡ታራቂ፤ካጣቢ፡አድራቂ።
   ካገር፡ደጋ፤ከመኝታ፡ዐልጋ። / ካገር፡ወይና፡ደጋ፤ከመኝታ፡አልጋ።
   ካጕል፡ጥንቈላ፥የሰው፡ልጅ፡መላ።
   ካላ፟ህ፡አልኾንኹ፥ከነቢ።
   ካልጠገቡ፡አይዘሉ፤ካልዘለሉ፡አይሰበሩ።
   ካልሠሩ፡በጣም፥ገንዘብ፡አይመጣም።
   ካንዠት፡ካለቀሱ፡እንባ፡አይገድም።
   ካፍ፡የወጣ፡አፋፍ፡(ነው)።
   ክስ፡በክሱ፤ሥጋን፡በኵበት፡ጠበሱ።


   ኸ
   ኹለት፡ጥፉ፥ካገር፡ይጠፉ።
   ኹለት፡ቍና፡ሰጥቼ፥አንድ፡ጥንቅል።


   ለ
   ለዳኛ፡አመልክት፥እንዲኾን፡መሠረት።
   ለወጡ፡ዕዘኑለት፥ከንጀራውም፡ጕረሡለት።
   ለወሬ፡የለው፡ፍሬ፤ላበባ፡የለው፡ገለባ።
   ለጥምቀት፡ያልኾነ፡ቀሚስ፥ይበጣጠስ።
   ለጦም፡ግድፈት፤ለበዓል፡ሽረት።
   ለይቶት፡አባ፡ንጉሧ።
   ለሙት፡የለው፡መብት።
   ለራሱ፡አያውቅ፡ነዳይ፥ቅቤ፡ለመነ፡ላዋይ።
   ለሰው፡ብሎ፡ሲያማ፥ለኔ፡ብለኽ፡ስማ።
   ለሰው፡ልጅ፡ሲያበሉ፥ለውሻ፡ልጅ፡ያብሉ።
   ላገሩ፡እንግዳ፥ለሰዉ፡ባዳ።
   ላህያ፡ማር፡አይጥማት።
   ላይሞቱ፡መናዘዝ፤ላይመቱ፡መጋበዝ።
   ላይን፡አምላክ፡አለው።
   ላይንና፡ለወዳጅ፡ጥቂት፡ይበቃዋል።
   ላም፡ሲበዘበዝ፥ጭራውን፡ያዝ።
   ላምጪ፡ይግደደው።
   ላንድ፡ብርቱ፥ኹለት፡መድኀኒቱ።
   ላፍ፡ግም፥አፍንጫ፡ድፍን፡ያዝለታል።
   ላሳር፡የጣፈው፡ቢነግድ፡አይተርፈው።
   ሌባን፡ሌባ፡ቢሰርቀው፥ምን፡ይደንቀው።
   ሌሊት፡ላራዊት፥ቀን፡ለሰራዊት።
   ልጅ፡ያለልጅ፡አከለ።
   ልጅና፡ጦጣ፥ውሃ፡ይጠጣ።
   ልፋት፡ቢያምርኽ፥መሬት፡ግዛ፤ችግር፡ቢያምርኽ፥ልጅ፡አብዛ።
   መ
   መጓጓት፡ያከሳል።
   መሶብ፡ሰፍቼ፥ላጤ፡አበርክቼ።
   ማቅ፡ይሞቃል፤ጋቢ፡ይደምቃል፤ገቢውን፡ባለቤት፡ያውቃል።
   ሜ፡ባልኩ፥ፍየል፡ከፈልኩ።
   ምን፡ብታፈገፍጊ፥ተግድግዳ፡አታልፊም።
   ምን፡ያመጣል፡ሠኔ፤ምን፡ይሠራል፡ቦዘኔ።
   ምን፡ቢያርሱ፥እንደ፡ጐመን፡አይጐርሡ።
   ምን፡ቢነግሡ፥በገዛ፡እጅ፡አይካሱ።
   ምንም፡በሙቱ፥ዐራድማ፡ሸምቱ።
   ምንም፡ብጠላው፥በወንድሜ፡ግንባር፡ደም፡አልይበት።
   ሞኝ፡የያዘው፡ፈሊጥ፥ውሻ፡የያዘው፡ሊጥ።
   ሞኝ፡የለቱን፥ብልኽ፡ያመቱን።
   ሞት፡ሲደርስ፥ቄስ፤ጦር፡ሲደርስ፡ፈረስ።


   ነ
   ነገሩ፡ነገር፡ነው፤ውስጡ፡ጥቅንጥቅ፡ነው።
   ነገር፡ቢበዛ፡ባህያ፡አይጫንም።
   ነገር፡ባዋቂ፥ብረት፡በጠራቂ።
   ነገር፡ከግቡ፤ጋሻ፡ከንግቡ።
   ንጉሥ፡ከሠየመው፡ማረሻ፡የሾመው።
   ንግርና፡ግግር፥ሳይደርስ፡አይቀር።


   ሠ
   ሠላሳ፡ቢታለብ፥እኔ፡በገሌ፡አለች፡ድመት።
   ሥጋ፡ቍጠር፡ቢሉት፦ጣፊያ፡አንድ፥አለ።


   ዐ
   ዐባይ፡ጠንቋይ፡ቤት፡ያፈርሳል።
   ዐብሮ፡ማደግ፡ያናንቃል።
   ዐደራ፡ቢሏቸው፥ይብሳሉ፡እሳቸው።
   ዐደራ፡ጥብቅ፤ሰማይ፡ሩቅ።
   ዐውድማ፡ላመለጥ፤ምስክር፡ላበለጥ።
   ዐጤን፡ይበልጡ፡ቀላጤ፥ሙክትን፡ይሻል፡ወጠጤ።
   ዐጤን፡መደብ፤ይቴጌን፡ገደብ።
   ዐይጥ፡በበላ፥ዳዋ፡ተመታ።
   ዐይጥ፡ለሞቷ፡የድመት፡አፍንጫን፡ታሸታለች።
   ዐሮ፟ም፡መሮም፥ማበሬን፡ከፈልኹ።
   ዐሎ፡ብሎ፡የተረታ፥መኻል፡አገዳውን፡የተመታ።
   ዓለም፡ዐላፊ፥መልክ፡ረጋፊ።
   ዓሣ፡ያለበት፡ባሕር፥ዕውር፡ያለበት፡ደብር፥ሳይበጠበጥ፡አያድር።
   ዕዳ፡በድግጣ።
   ዕዳው፡ዶሮ፥መጋቢያው፡ዳወሮ።
   ዕድሜ፡ለንስሓ፥ዘመን፡ለፍሥሓ።
   ዕድሜና፡ጨርቅ፥እንደ፡ምንም፡ያልቅ።
   ዕውቀትና፡ፍጥረት፡አንድ፡ቀን፡ነው።
   ዕውር፡ቢወበራ፥ከመሪው፡ይጣላ።
   ዕውር፡ያለበት፡ደብር፥ዓሣ፡ያለበት፡ባሕር፥ሳይበጠበጥ፡አያድር።
   ዕንጨት፡ኹኖ፡የማይጨስ፥ሰው፡ኹኖ፡የማይበድል፡የለም።


   ፈ
   ፈጥኖ፡መስጠት፤ዃላ፡ለመፀፀት።
   ፊት፡ወዳጅኽን፡በምን፡ቀበርከው፧በሻሽ፤የዃለኛው፡እንዳይሸሽ።
   ፊት፡የደረሰን፡ወፍ፡ይበላው፤ፊት፡የተናገረን፡ሰው፡ይጠላው።
   ፌንጣ፡ብትቈጣ፥እግሯን፡ጥላ፡ኼደች።
   ፍየል፡ከመድረሷ፥ቅጠል፡መበጠሷ።


   ጸ
   ጺም፡የሌለው፡መምር፤ዐጸድ፡የሌለው፡ደብር።
   ቀ
   ቀይ፡እንደ፡በርበሬ፤ጠሩ፡እንደ፡ብርሌ።
   ቀን፥በበቅሎ፤ማታ፡በቈሎ።
   ቀን፡ከጣለው፥ዅሉ፡የጠላው።
   ቀን፡ለተባባሰው፥ማጭድ፡አታውሰው።
   ቅቤ፡መዛኝ፡ድርቅ፡ያወራል።
   ቍንጫ፡የተጠረገ፡ዕለት፥ባለጌ፡የተመከረ፡ዕለት።


   ሰ
   ሰባት፡ዓመት፡ባይማሩ፥ሰባ፡ዓመት፡ይደነቍሩ።
   ሰዶ፡ማሳደድ፡ቢያምርኽ፥ዶሮኽን፡ለቆቅ፡ለውጥ።
   ሰው፡እንግዳ፡ቢኾን፥እግዜር፡ባላገር፡ነው።
   ሰው፡ከሞት፡ወዲያ፥ከወረደ፡አንጋዳ፥ወዳጁን፡አይጠቅም፥ጠላቱን፡አይጐዳ።
   ሰውን፡ማመን፡ቀብሮ፡ነው።
   ሰይጣን፡ጦመኛ፡ሲኾን፥ዘላለም፡ሰይጣን፡ነው።
   ሰይጣን፡ለወዳጁ፡ደርብ፡ነው።
   ሰነፍ፡እረኛ፡ከሩቅ፡ይመልሳል።
   ሲገደገድ፡ያልበጀው፥ሲዋቀር፡እሳት፡ፈጀው።
   ሲወጡ፡እንደ፡ጦጣ፤ሲወርዱ፡ዐሳር፡መጣ።
   ሲጠባ፡ያደገ፡ጥጃ፥ቢይዙት፡ይጓጕራል።
   ሲያረጁ፡አይበጁ።
   ሲያረጁ፡አንባር፡ይዋጁ።
   ሲታጠቡ፡ከክንድ፥ሲታረቁ፡ከሆድ።
   ሳይጠሩት፡ወይ፡ባይ፥ሳይሰጡት፡ተቀባይ።
   ሳይጣሉት፡የተጣላ፥ሲርብ፡ያበላ።
   ሳይቸግር፡ጤፍ፡ብድር።
   ሳትወልድ፡ብላ።
   ሴት፡ሲበዛ፥ጐመን፡ጠነዛ።
   ሴት፡ታውቅ፤በወንድ፡ያልቅ።
   ስለት፡ድጕሱን፥ደባ፡ራሱን።
   ስምኽ፡ማን፡ነው፧ላገር፡አይመች።ማን፡አወጣልኽ፧አሮጋግቶች።
   ስምኽ፡ማን፡ነው፧ላገር፡አይመች።ማን፡አወጣልኽ፧ጎረባብቶች።
   ስምንተኛው፡ሺ፥ሰው፡አበላሺ።


   ሸ
   ሸዋ፡ባላመጠ፥ባመቱ፡ይውጣል።
   ሹመት፡በተርታ፤ሥጋ፡በገበታ።


   ተ
   ተግደርዳሪ፤ጦም፡ዐዳሪ።
   ተጠማኝ፡ሲሰነብት፡ባለርስት፡ይኾናል።
   ተጥዶ፡የማይፈላ፤ተሹሞ፡የማይበላ።
   ተፈጥሮን፡ተመክሮ፡አይመልሰውም።
   ተረቴን፡መልስ፥አፌን፡በጨው፡አብስ።
   ትልቁ፡ዳቦ፡ሊጥ፡ኾነ።


   ቸ
   ቸርን፡ቢያጠብቁት፡ቢስ፡ይኾናል።
   ጰ
   ጳጉሜ፡ቢወልስ፥ጐተራኽን፡አብስ።

የፋይሉ ታሪክ

የቀድሞው ዕትም ካለ ቀን/ሰዓቱን በመጫን መመልከት ይቻላል።

ቀን /ሰዓትናሙናክልሉ (በpixel)አቅራቢውማጠቃለያ
ያሁኑኑ23:19, 30 ሜይ 2011በ23:19, 30 ሜይ 2011 የነበረው ዕትም ናሙና1,275 በ1,650፣ 106 ገጾች (368 KB)Hgetnet (ውይይት | አስተዋጽኦ)

የሚከተለው ገጽ ወደዚሁ ፋይል ተያይዟል፦

ተጨማሪ መረጃ