ስዕል:Fitawurari Ayele Tessema Aba Gudie.jpeg

ከውክፔዲያ

ዋና ፋይል(529 × 680 ፒክስል፤ መጠን፦ 68 KB፤ የMIME ዓይነት፦ image/jpeg)

የፋሽስት ጣሊያን መንግስት ሃገራችን በግፍ በወረረበት ወቅት ሃገራችን ብዙ ስመጥር ጅግኖችን አፍርታለት፡፡ በዚህ ወረራ ወቅት በጎንደር ከጓንግ ወንዝ እስከ መተማ ድረስ በጀግንነት ሃገሩን ከወረራ ነፃ ካደረጉት መካከል ጀግናዉ አርበኛ ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ አባ ጓዴ አንዱ ነበሩ፡፡ በአንድ ወቅት ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ ሰባስጌ በተባለ የፋሽስት የጦር ካምፕ ቦታ ላይ ከትንሽ ተከታዩቻቸዉ ጋር ጥቃት ፈፅመዉ 3 ወታደር ገድለዉና ብዛት ያለቸዉን በማቁሰላቸዉ፤ የፋሽስት ጣሊያን ባለስልጣናት በፊት አዉራሪ አየለ ላይ የተጠናከረ ዘመቻ በማድረግ አሳድደዉ ለመግደል ያላደረጉት ጥረት አልነበረም፡፡ነገር ግን እሱን መያዝ ቢቸግራቸዉ ቤተሰቦቹን አባቱን ቀኝ አዝማች ተሰማን ፤ ወንድሞቹን ልጅ ታደሰ እና ረዳን በመያዝ በጎንደር አርበኞች በሚታጎሩበት እስር ቤት አሰሯቸዉ፡፡ ነገር ግን በወቅቱ በእስር ቤቱ በተነሳዉ የታይፎይድ በሽታ ብዙ አርበኞች ሲሞቱ ልጅ ታደሰ የገፈቱ ተቃማሽ ነበር፡፡ ይሁን እንጅ የቀሪዎች ህይዎት ለማትረፍ በተደረገዉ ጥረት ወ/ሮ አቻሽማን ተሰማ ሽማግሌዉ አባቷን ቀኝ አዝማች ተሰማ እና ወንድሟን ረዳን ለማስፈታት ባደረገችዉ ጥረትና በዚህ ወቅትም ብዙ የጎንደር አርበኞች በጣሊያን ባለስልጣናት ምህረት ተደርጎላቸዉ ከስር ተፈተዋል፡፡ ይሁን እንጅ ቀኝ አዝማች ተሰማ በወቅቱ በታመሙት የታይፎይድ በሽታ በተፈቱ በሳምንታት ዉስጥ ለሞት አበቃቸዉ፡፡ ታዲያ ለዚህ ሁሉ የቤተሰብ ችግር አምጭ ተደርጎ የታየዉ ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ ነበር፡፡ ለፊት አዉራሪ ግን የእነሱ ሞት ለነፃነታቸዉ እንደ መሰዋዕትነት አድረጎ ነዉ የቆጠረዉ፡፡ በዚህ ልዩ የቁጭት አርበኝነትና ሃገር ወዳድነት ስሜት ጀግናዉ አርበኛ ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ አባ ጓዴ ከወንድሙ ከግራዝማች ረዳና ከልጅ አበራ ጋር በመሆን በሜጀር ባንቲ ቸኮ ሴንታታ የሚመራዉን የጣሊያንን ጦር በመተማ አካባቢ ነጋዴ ባህር አማኒት ተብሎ በሚጠራዉ ቦታ በሰኔ 29 1938 ዓ.ም በመሄድ አስደናቂ ጀብድ በመስራት የፋሽስትን ጦር በመደምሰስ አኩሪ ታሪክ ሰሩ፡፡ ይህ ጀብዳቸዉም እስከ ስደተኛዉ ንጉስ ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ ድረስ በመሰማቱ ጃንሆይም የአድንቆት ደብዳቤና በግራዝማች ራዳ አማካኝት 300 ጠበንጃ፤3000 ጥይትና 1000 ብር ልከዋል፡፡ በአባባ ገሪማ ታፈረ "ጎንደሬ በጋሻዉ" እና በሕይዎት ህዳሩ የቀ.ኃ.ስ መልክተኛ "ያች ቀን ተረሳች" መፃህፎች ስለጀግናዉ አርበኛ ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ እና ወንድማቸዉ ግራዝማች ረዳ ተገልፆል፡፡ በዚህ የአማኒት ጦርነት ድል መሰረት ለጀግናዉ አርበኛ ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ በህዝብ እንዲህ በፉከራና በቀረርቶ ተገጠላቸዉ፡፡ አባት አስገዳይ ወንደም አስገዳይ ብለዉ ሲያሙት ነጭ ሰዉ ገዳይ ወርዶ አማኒት ገዳይ አማኒት እንደ አራስ ነብር ተጉዞ ሌሊት ገዳይ ኩመር በር በለዉ እያለ ከቀስቅስ ጋር፡፡ የአባቱን ጠላት የተሰማን የታዴን ጠላት የወንድሙን በቁሙ ጠጣዉ በሳንጃ አልቢን አርዶ በካር ጠጣዉ ደሙን፡፡ የማር ቤቶች ልጀ የእነ አብዶ በላ ሲቸግር በእርሳስ ሲመች በዱላ፡፡ የአባ ሙላት ልጅ የባለ ሱሪ የቀስቅስ ወንድም የፊት አዉራሪ ከአዳራሻቸዉ አይበላም ፈሪ እራስ የሚሄድ ምንሽር ገሪ ከጥይት ጥይት መርጦ ቀርቃሪ ንብ የመሰለ ባንዳ አባራሪ የተጠመደ መድፍ አዛዋሪ የአበዛል እንጅ አይባል ፈሪ፡፡ ዘላለማዊ ክብርና ሞገስ ለምንግዜም ሃገር ወዳድ የነፃነት ጀግኖች አባቶቻችና እናቶቻችን!! አሹ ዋሴ

የፋይሉ ታሪክ

የቀድሞው ዕትም ካለ ቀን/ሰዓቱን በመጫን መመልከት ይቻላል።

ቀን /ሰዓትናሙናክልሉ (በpixel)አቅራቢውማጠቃለያ
ያሁኑኑ14:10, 7 ኤፕሪል 2014በ14:10, 7 ኤፕሪል 2014 የነበረው ዕትም ናሙና529 × 680 (68 KB)Ashu wasie (ውይይት | አስተዋጽኦ)የፋሽስት ጣሊያን መንግስት ሃገራችን በግፍ በወረረበት ወቅት ሃገራችን ብዙ ስመጥር ጅግኖችን አፍርታለት፡፡ በዚህ ወረራ ወቅት በጎንደር ከጓንግ ወንዝ እስ...

ወዲህ ፋይል የተያያዘ ገጽ የለም።