ስዕል:General Hailu Kebede Sekota.jpg

ከውክፔዲያ

General_Hailu_Kebede_Sekota.jpg(445 × 551 ፒክስል፤ መጠን፦ 72 KB፤ የMIME ዓይነት፦ image/jpeg)

ሌተናል ጀኔራል ሃይሉ ከበደ ዋግ ሹም ጓንጉል የንግስና ዘመናቸዉ 1894-1905 ነበር፡ እርሳቸዉ በተሸሙበት ወቅት የአድዋ ጦርነት በመካሄዱ ጀግናዉን የዋግን ህዝብ ጦር በመምራት ታላቅ ጀብድ ፈፅመዋል ፡፡ዋግ ሹም ጓንጉል ብሩ ይመሩት የነበረዉ የዋግ ጦርም በአድዋዉ ጦርነት ጊዜ ከ 400 የሚበልጡ ጣሊያኖችን እንደማረከ ታሪክ ይናገራል፡፡ዋግ ሹም ጓንጉል ብሩ የጦር ሜዳ ጀግና መሆናቸዉ ከመታወቁም ሌላ በአስተዳደርም ዝነኛ ፍርድ አዋቂ እንደነበሩ ይነገርላቸዋል፡፡የእራስቸዉን ታሪክ የሚያዉቁ አባቶች እንደሚሉት (አንድ ግዜ ለዋግ ሹሞች ከየገበሬዉ እየተመለመለ የሚወሰደዉን ከ 10 አንድ ፍየል ሙክት ለመመልመል ተልከዉ የሄዱ መልክተኞች መምጣታቸዉን አስቀድሞ የሰማ ሃብታም ገበሬ‹ የሰቡ ሙክቶችን መርጦዋሻ ዉስጥ በመደበቅ የከሱትን ብቻ አቅርቦ አሳየ፡፡ በዚህም ግዜ ጠቋሚ በዋሻ የደበቃቸዉን አንድ ሺ ያህል ሙክቶች ስለ አስያዘበት በሙሉ እንዲወረስ ተደረገ፡፡ ይሁን እንጅ ገበሬዉ ለዋግ ሹም ጓንጉል አቤት ለማለት ቤጊዜዉ ቢመላለስ እሳቸዉ ለፍርድ ካልተቀመጡ በስተቀር በመንገድ ላይ አቤቱታ ስለማይቀበሉ በጣም ተጉላላ እና ስለተናደደ ከፊታቸዉ ቁሞ ሰደባቸዉ ፡፡ በዚህ ግዜ ጉዳዩ ምን እንደሆነ እንዲያስረዳ ተጠይቆ በዝርዝር ስለተናገረ የተወረሱት ሙክቶችእንዲመለሱለት እና ሁለተኛም በሳቸዉ ዘመን ምልምል እንዳይመለመልበት ስለተደረገለት መልማዮቹ ወደሱ ሲሄዱ ጓንጉል ይብቃ የሚለዉን ነፃ ያደረገዉን የፍርድ ቃል በመጥቀስ ሳይመለመልበት ኖሯል፡፡ ከዋግ ሹም ጓንጉል ሞት ቡሃላ ዋግ ሹም ከበደ ተሹመዋል፡፡ እሳቸዉም ደግና ሃይማኖተኛ መሪ እንደነበሩ ይነገርላቸዋል፡፡ እንደ አባቶች አገላለፅ ዋግ ሹም ከበደ ለድሃ አዛኝ እና ፍርድ እንዳይጓደል የሚጥሩ ነበሩ፡፡ሹመት የሚሰጡት ለዋግ ዘሮች ብቻ ሳይሆን የማስተዳደር ችሎታ እና እዉቀት ላላቸዉ ሰዎች ጭምር ነበር፡፡ጉቦንም በከፍተኛ ደረጃ ይቃወሙ ስለነበር በአንድ ወቅት አንዲት ድሃ ሴት ለጉዳይ መታያ ጉቦ ባዶ ሞሰብ ይዛ በመሄዷ እንጀራ ተቀባዩ ጉቦ መቀበል እንዳለበት ይገነዘባል፡ ባዶ መሆኑን ካረጋገጠ ቡሃላ ሊያሲዛት ቢሞክርም ቢቸግራት ነዉ ብለዉ መለሱዋት እና ጉዳይዋን ፈፅመዉ ላኳት ይባላል፡፡ ዋግ ሹም ከበደ በላስታ እና በጎንደር ባላባት የሆኑትን የደጃዝማች ንጉሴ ፋሪስን ልጅ ወይዘሮ ሂሩትን አግብተዉ ሌተናል ጀኔራል ሃይሉን፡እንዲሁም ደጃዝማች በላይን፡ ፊት አዉራሪ ገሰሰን፡ደጃዝማች በላቸዉን፡‹ጣሊያን ጋር ሲዋጉ የተገደሉ› ፡ደጃዝማች እጅጉን እና ግራ አዝማች በዛብህን ወልደዋል፡፡ ከዋግ ሹም ከበደወዲህም የዋግን የቆየ ጀግንነት እንዲታደስ ያደረጉት ልጃቸዉ ደጃዝማች ቡሃላ ሌተናል ጀኑራል ሃይሉ ከበደ ናቸዉ፡፡ ጀኔራል ሃይሉ ከ1927-1933 ኢትዮጵያን የወረረዉን የፋሽስት ጦር በማርበድበድ ጀግናዉን የዋግን ህዝብ አሰልፈዉ በቆራጥነት ሲዋጉ ፡ ወለህ በተባለዉና የሰቆጣ ከተማ አቅራቢ በሆነዉ የጦር አዉድማ ላይ አንገታቸዉ በጠላት ተቆርጦ ወደ ጣሊያን ሮም ሲወሰድ፡ ተራፊዉ አካላቸዉ ደግሞ ከሰቆጣ ከተማ በታች በሚገኘዉ እና ጉድጉዳ በተባለዉ ገደል እንዲጣል ተደርጉዋል፡፡ ሆኖም የአከባቢዉ ገበሬዎች አስከሬናቸዉን ወድቆ በማግኘታቸዉና የእራሳቸዉ መሆኑን በመገንዘባቸዉ ከአንድ የተወሰነ ቦታ ላይ ቀብረዉት ቆይተዋል፡፡ ፋሽስት ጣሊያን ተሸንፎ የኢትዮጵያ ነፃነትሲመለስ ግን አፅማቸዉ ከተቀበረበት ቦታ ተቆፍሮ ከወጣ ቡሃላ የአያታቸዉ የዋግ ሹም ተፈሪ ፡የአባታቸዉ የዋግ ሹም ከበደ አፅም ካረፈበት በሰቆጣ ደብረ ገነት መድሃኒአለም በክብር አርፉዋል፡፡ ይህን ጀግንነታቸዉን በመገንዘብም የኢትዮጵያ መንግስት ከሞቱ ቡሃላ ሌተናል ጀኔራል በሚለዉ ማእረግ እንዲጠሩ አድርጓል፡፡ማእረጉም በኢትዮጵያ ቤተ መንግስት ለክብራቸዉ ሲባል ከንጉሱ በስተቀር የመጀመሪዉ እንደነበር አበዉ ይናገራሉ፡፡ Dr. Ayalew Sisay የአገዉ ህዝብ ታሪክ

የፋይሉ ታሪክ

የቀድሞው ዕትም ካለ ቀን/ሰዓቱን በመጫን መመልከት ይቻላል።

ቀን /ሰዓትናሙናክልሉ (በpixel)አቅራቢውማጠቃለያ
ያሁኑኑ14:01, 7 ኤፕሪል 2014በ14:01, 7 ኤፕሪል 2014 የነበረው ዕትም ናሙና445 × 551 (72 KB)Ashu wasie (ውይይት | አስተዋጽኦ)ሌተናል ጀኔራል ሃይሉ ከበደ ዋግ ሹም ጓንጉል የንግስና ዘመናቸዉ 1894-1905 ነበር፡ እርሳቸዉ በተሸሙበት ወቅት የአድዋ ጦርነት በመካሄዱ ጀግናዉን የዋግን ህዝ�...

ወዲህ ፋይል የተያያዘ ገጽ የለም።

ተጨማሪ መረጃ