ሶሀባ (sahabah)

ከውክፔዲያ


🔸አብደላህ ኢብን መስዑድ

ረዲየላሁ ዐንሁ🔹

<<ቁርኣንን በወረደበት ዓይነት ለ መቅራት የፈለገ ሰዉ እንደ ኡም አብድ ይቅራ!>>

         (ነብዩ ሙሐመድ ሰለላሁ 
         ዐለይሂ ወሰለም)


✍ገና ወጣት እያለ የጉርምስና ዕ ድሜዉን ሳይጨርስ ዑቅባ ኢብን ሙዐይጥ የተባለዉን የቁረይሽ ሹ ም የከብት መንጋዎች በመጠበቅ በመካ የተራራ ሰርጦች ላይ ብቻ ዉን መመላለስ ልማዱ ነበር።ሰዎ ች <<ኢብን ዑም አብድ>>-የባሪያ እናት ልጅ-ብለዉ ይጠሩት ነበር።እ ዉነተኛ ስሙ አብደላህ ሲሆን የአባ ቱ ስም መስዑድ ነበር።

✍ወጣቱ በወገኖቹ መካከል ስለ ታዩት ነብይ ወሬዎችን ሰምቶ የነበ ረ ቢሆንም በዕድሜዉና ከመካ ኀ ብረተሰብ በመራቁ ምክንየት አንዳ ችም ችኩረት አልሰጣቸዉም ነበር ።የዑቅባህን የከብት መንጋ ይዞ ገ ና ማለዳዉ ላይ መዉጣት ልማዱ የነበረ ሲሆን ካልመሸ ደግሞ አይመለስም።

✍አንድ ቀን መንጋዎቹን እየጠበቀ ሳለ፥ሁለት መካከለኛ ዕድሜና ግር ማ ሞገስ የተላበሱ ሰዎች ወደ እ ሱ ሲመጡ ከርቀት አየ።እንደ ደከ ማቸዉ ያስታዉቁ ነበር።ከመጠማ ታቸዉም የተነሳ ከንፈሮቻቸዉ ክዉ ብለዉ ደርቀዋል።

✍ወደእሱ ቀርበዉ ሰላምታ ከሰ ጡት በኃላ <<አንተ ወጣት፥የዉኃ ጥማችንን ለመቁረጥና ጉልበት ለ ማግኘት ብንችል እስኪ እባክልህ ከነዚህ በጎች መካከል አንዷን እለ ብልን?>>አሉት።

✍ወጣቱም <<አልችልም!በጎቹ የ ኔ አይደሉም።የኔ ስራ መጠበቅ ብ ቻ ነዉ።>>ሲል መለሰላቸዉ።

✍ሁለቱ ሰዎች አልተከራከሩትም ።ምንም እንኳ በዉሃ ጥም እጅግ ተሰቃይተዉ የነበሩ ቢሆንም ቀና በ ሆነ መልሱ እጅግ ተደሰቱ።ደስታቸ ዉ በፊታቸዉ ላይ ይታይ ነበር።

✍በእርግጥ ሁለቱ ሰዎች የተባረ ኩት ነቢይና ጓደኛቸዉ አቡበክር ሰ ዲቅ ነበሩ።የዚያን ቀን ወደ መካ ተ ራራዎች የወጡት ከቁረይሽ ግፍና መከራ ለማምለጥ ነበር።

✍ወጣቱም በተራዉ በነብዩና ሰለ ላሁ ዐለይሂ ወሰለም በጓደኛቸዉ ተደንቆ ወዲያዉኑ ከእነሱ ጋር ተወ ዳጀ።አብደላህ ኢብን መስዑድ ረ ዲየላሁ ዐንሁ ሙስሊም ሆኖ ለነብ ዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ግልጋ ሎት ለመስጠት ፈቃደኝነቱን ሲገል ፅ ብዙም አልቆም።ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በነገሩ ተስማሙ በትና ከዚያ ቀን ወዲህ እድለኛዉ አብደላህ ኢብን መስዑድ የበግ እ ረኝነቱን ተወ።በምትኩም የተባረኩ ት ነብይ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የቅርብ አገልጋይነት ዋና ሥራዉ ሆነ።

✍አብደላህ ኢብን መስዑድ ረዲየ ላሁ ዐንሁ ከነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጋር የቅርብ ወዳጃቸዉ እ ንደሆነ ቆዩ።በቤታቸዉ ዉስጥና ዉ ጭ የሚያስፈልጋቸዉን ነገር ሁሉ ያሟላ ነበር።መንገድ ሲሄዱና ዘመ ቻ ሲወጡ ያጅባቸዋል።ሲተኙ ይቀ ሰቅሳቸዋል።ሲታጠቡ ግርዶሽ ይ ሠራላቸዋል።ዕቃቸዉንና የጥርስ መፋቂያቸዉን ይይዝ ነበር።ሌሎች በግል የሚያስፈልጉዋቸዉን ነገሮ ችም ያቀርብ ነበር።

✍አብደላህ ኢብን መስዑድ ረዲ የላሁ ዐንሁ በነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቤተሰብ ዉስጥ ልዩ ስል ጠና (ተርቢያ )ተቀበለ።በነብዩ ሰለ ላሁ ዐለይሂ ወሰለም አመራር ሥር ነበር። <<በፀባይ ነብዩን ሰለላሁ ዐ ለይሂ ወሰለም እጅግ በጣም የሚ መስል ነበር>> እስከሚባል ድረስ እያንዳንዱን የእሳቸዉን ባህርይ ተላበሰ።

✍አብደላህ ረዲየላሁ ዐንሁ በነብ ዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም <<ትም ህርት ቤት>>ዉስጥ ነበር የተማረ ው።ከሶሃባዎች መካከል ቁርኣንን በመሸምደድ በላጩ እሱ ነበር።ከ ሁሉም በተሻለ ሁኔታ ተረድቶትም ነበር።ስለዚህ በኢስላማዊ ሕገ-መ ንግስት (ሸሪዓ)ላይ ከሁሉም የላቀ ከፍተኛ እዉቀት ነበረዉ።ይህንን ዑ መር ኢብን አልኸጠጧብ ረዲየላሁ ዐንሁ በአረፋ ሜዳ ላይ ቆመዉ ሳ ሉ ወደ እሳቸዉ ከመጣዉና እንደ ሚከተለዉ ለነገራቸዉ ሰዉ ታሪክ የ ተሻለ የሚያብራራ የለም፦

<<የምእመናን መሪ ሆይ! በኩፋ ነ ዉ የመጣሁት።የቁርኣኑን ቅጅዎች ከአምሮዉ እያፈለቀ የሚሞላ ሰዉ አጋጥሞኛል>>አላቸዉ።ዑመር ረ ዲየላሁ ዐንሁ እጅግ በጣም ተናድ ደዉ በግመላቸዉ አጠገብ ይንጎባ ለሉ ጀመር።<<እሱ ማነዉ?>>ሲሉ ጠየቁት።<<አብደላህ ኢብን መስ ዑድ ረዲየላሁ ዐንሁ>>ሲል መለሰ ።የዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ ቁጣ ወ ዲያዉ በረደ።ተረጋጉ።<<በአላህ ስ ም እምላለሁ! በዚህ ጉዳይ ላይ ከ እሱ የበለጠ አዋቂ ሌላ ሰዉ መኖ ሩን አላዉቅም።ስለዚሁ አንድ ነገር ላጫዉትህ>>አሉ።ቀጠሉና <<አን ድ ቀን ማታ የአላህ መልእክተኛ፥ሰ ለላሁ ዐለይሂ ወሰለም፥ከአቡበክር ጋር ሆነዉ ስለሙስሊሞች ይነጋገ ሩ ነበር።እኔም ከእነሱ ጋር ነበርኩ ።ከጨረስን በኃላ ነብዩ ሰለላሁ ዐ ለይሂ ወሰለም ሄዱ።እኛም ተከትለ ናቸዉ መስጊዱን አቋርጠን ስንሄድ እኛ ከሩቅ ያልለየነዉ በስግደት ላይ የቆመ ሰዉ ነበር።ነብዩ ሰለላሁ ዐ ለይሂ ወሰለም ቆመዉ ሰዉየዉ የ ሚለዉን ከሰሙ በኃላ ወደእኛ ዞረ ዉ <<ቁርኣንን በወረደበት ዓይነት ለማንበብ የፈለገ ሰዉ እንደ ኢብን ኡም አብድ ያንብብ አሉ።

✍አብደላህ ረዲየላሁ ዐንሁ ስግ ደቱን ጨርሶ ተቀምጦ ዱዓ እያደረ ገ ሳለ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለ ም <<ጠይቅ!ይሰጥሀል፥ጠይቅ!ይ ሰጥሀል>>አሉ።ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ ንግግራቸዉን ቀጠሉ...<<ወ ደ አብደላህ ኢብን መስዑድ ረዲየ ላሁ ዐንሁ በቀጥታ ሄጄ ፀሎቶቹ ሁሉ ተቀባይነት ስለማግኘታቸዉ ነ ብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የተና ገሩትን የምስራች እነግረዋለሁ ብ ዬ ወሰንኩ።ነገርኩትም።ነገር ግን ከእኔ በፊት አቡበክር ሄዶ የምስራ ቹን ነግሮት እንደነበር ተረዳሁ።በአ ላህ ስም እምላለሁ!አቡበክርን ጥ ሩ ነገር በመሥራት ፈፅሞ ቀድሜ ዉ አላዉቅም።>>

✍አብደላህ ኢብን መስዑድ ረዲየ ላሁ ዐንሁ እንዲህ ዓይነት ከፍተኛ የቁርኣን ዕዉቀት ከማግኘቱ የተነሳ <<ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌ ለ በሆነዉ እምላለሁ!እያንዳንዱ የ ቁርኣን አንቀፅ የት እንደወረደና የአ ወራረዱን ሁኔታ (ታሪካዊ አመጣ ጡን)እኔ ሳላዉቅ አንዲትም የቁርኣ ን አንቀፅ አልወረደም።በአላህ ስም እምላለሁ!የአላህን መፅሐፍ የበለ ጠ የሚያዉቅ ሰዉ መኖሩን ካወቅ ሁ ከእሱ ጋር ለመሆን የምችለዉን ሁሉ አደርጋለሁ>>ይል ነበር።

✍አብደላህ ረዲየላሁ ዐንሁ ስለራ ሱ የተናገረዉ እያጋነነ አልነበረም። ዑመር ኢብን አልኸጧብ ረዲደላሁ ዐንሁ ኸሊፋ በነበሩበት ወቅት ካደ ረጉዋቸዉ ረጅም ጉዞዎች መካከል በአንደኛዉ አንድ (ካራቫን) (ሲራራ ነጋዴ) ያጋጥማቸዋል።ጥቅጥቅ ያ ለ ጨለማ ስለነበረ የንግድ ቅፍለቱ በወጉ አይታይም ነበር።ዑመር ረ ዲየላሁ ዐንሁ አንድ ሰዉ ቅፍለቱን እንዲያናግር አዘዙ።

  1. <<ከየት ነዉ የምትመጡት?>>

ሲሉ ዐመር ረዲየላሁ ዐንሁ ጠየቁ፤

•<<ከፈጀል-ዐሚቅ>> (ከጥልቅ ሸ ለቆ)የሚል መልስ ተሰማ።(ፈጀል-ዐሚቅ የሚለዉ አገላለፅ ቁርኣናዊ ነዉ።)

  1. <<እና ወዴት እየሄዳችሁ ነዉ?>

>ሲሉ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ ጠደ ቁ፤

• <<ወደ አል-በይተል-ዓቲቅ (ወደ ጥንታዊዉ ቤት)የሚል መልስ ሐ ጣ።(አል-በይት አልአቲቅ የሚለዉ አገላለፅም ቁርኣናዊ ነዉ።)

✍በዚህ ጊዜ ዑመር ረዲየላሁ ዐ ንሁ <<ከነሱ መካከል የተማረ ሰዉ (ዓሊም)አለ።>>ካሉ በኃላ ተጨማ ሪ ጥያቄ እንዲጠየቅ አዘዙ።

<<ከቁርኣን ዉስጥ ታላቁ ክፍል የ ቱ ነዉ?>>የሚከተለዉን አነበበላቸ ዉ፦

  1. <<አላህ ከእርሱ በቀር ሌላ አም

ላክ የለም፤ሕያዉ፥ራሱን ቻይ ነዉ፤ ማንገላጀትም፥አንቅልፍም፥አትይዘዉም፤በሰማያት ዉስጥና በምድር ዉስጥ ያለዉ ሁሉ የርሱ ብቻ ነዉ፤ ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነዉ?(ከፍጡሮች) በፊታቸዉ ያለዉንና ከኃላቸዉ ያለዉ ን ሁሉ ያዉቃል፤በሻዉም ነገር እን ጂ ከዕዉቀቱ በምንም ነገር አያካ ብ ቡም፥(አያዉቁም)፤መንበሩ ሰማ ያትንና ምድርን ሰፋ፤ጥበቃቸዉም አያቅተዉም፤እርሱም የሁሉ የበላ ይ ታላቅ ነዉ።>>(አል-በቀራህ፥ 255)

<<ስለፍትህ እጅግ በጣም ግልጽ የሆነ ማብራሪያ የሚሰጠዉ የቁር ኣን ክፍል የትኛዉ ነዉ?>>

  1. <<አላህ በማስተካከል፥በማሳመ

ር፥ለዝምድና ባለ ቤት በመስጠት ም ያዛል፤>>(አል-ነሕል፥90)

<<ከቁርኣን ዉስጥ እጅግ አሳሳቢ አንቀጽ የትኛዉ ነዉ?>>

  1. የብናኝ ክብደት ያክልም መልካም

ን የሠራ ሰዉ፥ያገኘዋል።የብናኝ ክ ብደት ያክልም ክፉን የሠራ ሰዉ ያ ገኘዋል።>>(አል-ዘልዘላህ፥7-8)

<<ከቁርኣን ዉስጥ የትኛዉ አንቀጽ ከፍተኛ ተስፋ ይሰጣል?>>

  1. በላቸዉ፦እናንተ በነፍሶቻችሁ ላ

ይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ!ከአ ላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፤አላህ ኃጢአቶችን በመላ ይምራልና እነሆ እርሱ መሓሪዉ፥አዛኙ ነዉና።>>(አ ል-ዙሙር፥53)

✍ከዚያም ዐለመር ረዲየላሁ ዐን ሁ እንዲሁ ሲሉ ጠየቁ፦ <<አብደ ላህ ኢብን መስዑድ ረዲየላሁ ዐን ሁ ከናንተ ጋር ነዉን?>>


• <<በአላህ ይሁንብን እሱ ከኛ ጋር ነዉ>>በማለት መለሱላቸዉ።

✍አብደላህ ኢብን መስዑድ ረዲየ ላሁ ዐንሁ ቁርኣንን በአምሮዉ የተ ቀረጸ ምሁር የአላህ ተገዢ (ዓቢድ )ብቻ አልነበረም።ሁኔታዉ በሚጠ ይቅበት ጊዜ ደግሞ ሃሞተ ኮስታ ራ፣ጠንካራና ደፋር ተዋጊም ነበር።

☔️በአንድ ወቅት የነብዩ ሶሐቦች መካ ዉስጥ አንድ ላይ ተሰባሰቡ። ብዛታቸዉ ትንሽ ከመሆኑ ሌላ ኃይ ል አልባና ተጨቋኞች ነበሩ።<<ቁ ርኣን ከፍ ባለ ድምፅ በይፋ ሲነበብ የቁረይሽ ወገኖች ሰምተዉ አያዉቁ ምና ሊያነብላቸዉ የሚችል ሰዉ ማነዉ?>>ተባባሉ።

💫<<እኔ አነብላቸዋለሁ>>ሲል አ ብደላህ ኢብን መስዑድ ረዲየላሁ ዐንሁ ፈቃደኛነቱን ገለጸ።ሰዎቹ ግ ን <<አንተንስ እንፈራልሃለን።እኛ የ ምንሻዉ ከነሱ ጥቃት ሊጠብቀዉ የሚችል ጎሳ ያለዉ ሰዉ ነዉ>> አሉ።

💥<<ለእኔ ፍቀዱልኝ፣ከእነሱ ተንኮ ልና መጥፎ ድርጊት አላህ ይጠብ ቀኛል፤ያርቀኛልም።>>ሲል አብደላ ህ ኢብን መስዑድ ረዲየላሁ ዐንሁ ሽንጡን ይዞ ተሟገተ።ስለዚህ ከካ ዕባ ጥቂት ሜትሮች ብቻ ርቆ ከሚ ገኘዉ <<መቃም ኢብራሂም>>(የ ኢብራሂም መስገጃ ቦታ)እስከሚደ ርስ ወደ መስጊዱ ጉዞ ቀጠለ።ወ ቅቱ ጎህ እየቀደደ ነቀር።ቁረይሾች ከካዕባ ዙሪያ ተቀምጠዉ ነበር።አ ብደላህ ረዲየላሁ ዐንሁ በቦታዉ ቆ ሞ እንዲህ ሲል ማንበብ ጀመረ፦

  1. አል-ረሕማን፤ቁርኣንን አስተማረ፥

ፈጠረ።>>(አል-ረሕማን፥1-3)

💐ማንበቡን ቀጠለ።በዚህ ጊዜ ቁ ረይሾች አትኩረዉ ተመለከቱት።አን ዳንዶቹ ደግሞ <<ኢብን ኡሙ አብ ድ ምን እያለ ነዉ?>> <<ይሄ የተረ ገመ (ሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ካመጣዉ መካከል አንዳን ዶቹን እየደገመ ነዉ)>>ሲሉ አረጋገጡ።

🌿እሱ ግን ማንበቡን አላቋረጠም ።ይደበድቡት ጀመር...ወደ ሶሃባዎ ች በተመለሰ ጊዜ ከፊቱ ላይ ደም ይጎርፍ ነበር።

🌼እነሱም እንዳዩት <<ይህን ነበር የፈራንልህ?>>አሉት።በዚህ ጊዜ አ ብደላህ ረዲየላሁ ዐንሁ <<በአሁኑ ወቅት የአላህ ጠላቶች ከእኔ የበለ ጠ ደህንነት አይሰማቸዉም።ከፈለ ጋቸዉ በነገዉም ዕለት ሄጄ ይህንኑ አደርጋለሁ>> አለ። <<የሚበቃህን ያህል አድርገሃል።የሚጠሉትን እን ዲሰሙ አድርገሃቸዋል>>አሉት።

• <<ኃጢያቶቼ!>>

🍃<<ታዲያ ምን ይሻልሃል?>>

•<<የጌታዬ ምህረት!>>

🍃<<ለብዙ ዓመት ዉሰድ ስትባል እምቢ ያልከዉ የመምህርነት ደመ ወዝህን አሁንስ አትቀበልም?!>>

•<<አልፈልገዉም!>>

🍁<<ከሞትክ በኃላ ለሴቶቹ ልጆ ችህ እንዲሆን ፍቀድ።>>

•<<ልጆቼ ድህነት ያገኛቸዋል ብለ ህ ትፈራለህን?ነብዩ ሰለላሁ ዐለይ ሂ ወሰለም <<ሱራ -አል-ዋቂዓህ> >ን በየምሽቱ የሚያነብ ሰዉ ድህነ ት ፈፅሞ አይነካዉም)ሲሉ ስለሰማ ሁ ይህንኑ ምዕራፍ በየምሽቱ እን ዲያነቡ አዝዣቸዋለሁ።>>

💐የዚያን ቀን ምሽት አብደላህ ረ ዲየላሁ ዐንሁ ምላሱ አላህን በማ ዉሳትና የቁርኣንን አንቀጾች በመድ ገም እንደራሰች አለፈ።

☪ተጠናቀቀ💟