ቦሩ ሜዳ
Appearance
ቦሩ ሜዳ በቀድሞ ወሎ የሆነ ትልቅ ገበያ ከተማ ነው።
በመጋቢት 18 ቀን 1870 ዓ.ም. በቦሩ ሜዳ ላይ የሸዋ ንጉሥ (ምኒልክ) ለንጉሠ-ነግስት ዮሐንስ አራተኛ ተገዥ እንደሆኑ ቃላቸውን ገቡ። በምላሽም ዮሐንስ በሸዋ ላይ የምኒልክን ንጉሥነት ተቀበሉ።
ዮሐንስ በቦሩ ሜዳ ቤተክርስቲያንን ሠርተው በግንቦት 1870 አንድ ታላቅ የተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስብሰባ ተፈጸመበት። በዚህ ስብሰባ «የጸጋ ልጅ» ወይም «ሦስት ልደት» የተባለ ትምህርት ተከታዮች ከእንግዲህ እንደ ሃራ ጤቃ ይቆጠራሉ የሚል አዋጅ ወጣ። ከዚህ በላይ በአጼ ዮሐንስ ትእዛዝ ዘንድ የእስላም ሃይማኖት ለወሎ መኳንንት በግድ ተከለከለ። ይህ ከባድ ቃል ግን በሚከተለው ንጉሠ ነገሥት በ2 ምኒልክ አዋጅ ተሠረዘ።
ስመ ጥሩ መምህር የሆኑት አለቃ አካለ ወልድ በወሎ ያለውን በተክርስቲያን በማጽናት እንዲረዱ ተመረጡ። በቦሩ ሜዳ ላይ የትምህርት ማእከል መሠረቱ። ቦሩ ሜዳ ሥላሴ የቤተክርስቲያን ከፍተኛ ትምህርት ማእከል ሲሆን ታውቆ ተማሪዎች ከአገሩ ሁሉ ወደዚያ ይመጡ ነበር።