ተባሕትዎ
ተባሕትዎ ራስን መግዛት፣ በራስ ማስገዛት ድህነት እና በቀላል ኑሮ አማካኝነት ከዓለማዊ ደስታዎች በመራቅ የሚገለጽ የአኗኗር ዘይቤ ሲሆን [1] ብዙውን ጊዜ መንፈሳዊ ግቦችን ለማሳካት ይውላል። [2] ባሕታውያን ከዓለም ተለይተው ሊኖሩ ወይም የማኅበረሰቡ አካል ሆነው ሊቀጥሉ ይችላሉ፤ ነገር ግን በተለምዶ ቁጠባ ያለው የአኗኗር ዘይቤን ሊከተሉ ይችላሉ፣ [3] ይህም ቁሳዊ ንብረቶችን እና አካላዊ ደስታዎችን በመተው የሚታወቅ ሲሆን፣ እንዲሁም በሃይማኖት ፣ በጸሎት ወይም በማሰላሰል ላይ እያተኮሩ ጾምን ያሳልፋሉ። [4] አንዳንድ ግለሰቦች እንደ አልኮል ፣ ማጨስ ፣ አደንዛዥ ዕፅ ፣ ወሲብ ፣ የወሲብ ፊልሞች ፣ የቅንጦት ምግብ እና መዝናኛ ካሉ ሱሶች ራሳቸውን ለማላቀቅ የባሕታዊ የአኗኗር ዘይቤን ሞክረዋል። [5]
[6] በተለየግሪክ የፍልስፍና ትምህርት ቤቶች [3] ( ኤፒኩራዊ ፣ ጂምኖሶፊያዊ ፣ ስቶይሲዝም እና ፓይታጎሪያኒዝም )፣ [3] የህንድ ሃይማኖቶች ( ቡድሂዝም ፣ ሂንዱይዝም ፣ ጃይኒዝም )፣ [6] የአብርሃም ሃይማኖቶች [6] ( ክርስትና ፣ አይሁድነት ፣ እስልምና )፣ [6] እና ዘመናዊ ልማዶች ውስጥ በስፋት ይገኛል። ይህም መንፈሳዊ ልምምድ እስከ ዘመናችን ድረስ በተለያዩ የእምነቱ ተከታዮች ዘንድ በተግባር እየዋለ ይገኛል። [5] ተለማማጆቹ (ባሕታውያኑ) ለነፍስ ቤዛን ፣ [7] መዳን ፣ [4] ወይም መንፈሳዊነትን በመከታተል [3] የተከለከሉ የአኗኗር ዘይቤዎችን ይመራሉ። [8] ብዙ ባሕታውያን አካልን የማንጻት ተግባር፣ ነፍስን ለማንጻት ይረዳል ብለው ያምናሉ፤ እንዲህ በማድረግም ከፈጣሪ (መለኮታዊ ኃይል) ጋር የጠበቀ ግንኙነት ለመፍጠር ወይም ውስጣዊ ሰላምን ለማግኘት ይጥራሉ። [3] ይህ የአምልኮ ሥርዓቶችን፣ ሀብትንና ሥጋዊ ደስታን መተውን፣ [3] ወይም መንፈሳዊ ግቦችን ለማሳካት ራስን መገሰጽን ሊያመለክት ይችላል። [6]
ይሁን እንጂ፣ ባሕታውያን በራሳቸው ላይ የሚጥሏቸው ገደቦች በብዙ የሕይወታቸው ዘርፎች ላይ የላቀ ነፃነትን እንደሚያመጡላቸው ያምናሉ። ይህም እንደ አእምሮ ጥራት እና አውዳሚ የሆኑ ፈተናዎችን የመቋቋም አቅም መጨመርን ያካትታል። በአንዳንድ ጥንታዊ ሥነ-መለኮታዊ አስተምህሮዎች ውስጥ፣ ተባሕትዎ ወደ መንፈሳዊ መታደስ የሚደረግ ጉዞ ተደርጎ ይታያል። በዚህም ጉዞ ውስጥ 'ቀላሉ ነገር በቂ ነው'፣ 'እውነተኛ ሐሴት የሚገኘው በውስጥ ማንነት ነው'፣ እንዲሁም 'ቁጥብነት ትልቅ ሀብት ነው' ተብሎ ይታመናል። [4] በተቃራኒው፣ እንደ ዞሮአስትራዊ ፣ የጥንታዊ ግብፅ ሃይማኖት ፣ የዲዮኒሲያን ሚስጥሮች እና ቫማካራ (ግራ እጅ ያለው የሂንዱ ታንትራዊ ) ያሉ በርካታ ጥንታዊ ሃይማኖታዊ ወጎች ከተባሕትዎ ተግባራት ይቆጠባሉ። ይልቁንም ትኩረታቸውን በዓለም ላይ በሚደረጉ የተለያዩ በጎ ተግባራት እና ለቤተሰብ ሕይወት በሚሰጥ ትልቅ ዋጋ ላይ ያደርጋሉ።
- ↑ Randall Collins (2000), The sociology of philosophies: a global theory of intellectual change, Harvard University Press, ISBN 978-0674001879, p. 204.
- ↑ You must specify title = and url = when using {{cite web}}. "".
- 1 2 3 4 5 6 "Pagan asceticism: cultic and contemplative purity". Asceticism in the Graeco-Roman World. Cambridge and New York: Cambridge University Press. 2009. pp. 9–33. ISBN 978-1-139-48066-6. https://books.google.com/books?id=0EAgAwAAQBAJ&pg=PA9.
- 1 2 3 "Christian asceticism before Origen". Asceticism in the Graeco-Roman World. Cambridge and New York: Cambridge University Press. 2009. pp. 94–99. ISBN 978-1-139-48066-6. https://books.google.com/books?id=0EAgAwAAQBAJ&pg=PA94. Cite error: Invalid
<ref>tag; name "Finn2009p94" defined multiple times with different content - 1 2 "IAFOR Journal of Ethics, Religion & Philosophy". Asceticism: A Match Towards the Absolute 3 (2): 14. Autumn 2017. http://iafor.org/archives/journals/iafor-journal-of-ethics-religion-and-philosophy/10.22492.ijerp.3.2.06.pdf በ10 January 2021 የተቃኘ. Cite error: Invalid
<ref>tag; name "volume" defined multiple times with different content - 1 2 3 4 5 Body, Society, and Subjectivity in Religious Studies. Oxford and New York: Oxford University Press on behalf of the American Academy of Religion. pp. 7–33.
- ↑ Asceticism. Oxford and New York: Oxford University Press. 2002. pp. 247, 351. ISBN 978-0-19-803451-3. https://books.google.com/books?id=EIqym5Pw_O8C&pg=PA247.
- ↑ Roles and Rituals for Hindu Women. Delhi and London: Motilal Banarsidass. 1992. pp. 212–219. ISBN 978-81-208-1036-5. https://books.google.com/books?id=sKDm8EH2L3kC&pg=PA212.