ቲታኖማኪያ

ከውክፔዲያ
(ከቲታኖማኬ የተዛወረ)

ቲታኖማኪያ (ግሪክ፦ Τιτανομαχία) ወይም «የቲታኖች ጦርነት» በጥንታዊ ግሪክ አፈ ታሪክ የ10 ዓመት የአማልክት ጦርነት ነበር። በአንዱ ወገን ክሮኖስቲታኖች ነበሩ፤ በሌላውም ዚውስና የኦሊምፑስ ወገን ነበረ።

ጦርነቱ የመጣበት ጠንቅ እንዲህ ይተረካል። ክሮኖስ አባቱን ኡራኑስ ሰለበውና ገድሎት ከንጉሥነት ገለበጠው። ኡራኑስ እየሞተ፣ ክሮኖስ በፈንታው በራሱ ልጆች እንዲገለበጥ የሚል ትንቢት ተናገረ። ከኡራኑስም ደም ጊጋንቴስ (ታላላቅ ወይም ረጃጅም ሰዎች) ተወለዱ።

የቲታኖች አለቃ ክሮኖስ አሁን ንጉሥ ሆኖ እኅቱን ሬያን ሚስት አደረጋት፤ ትንቢቱንም ለማምለጥ እያንዳንዱን ልጅ ስትወልዳቸው ክሮኖስ ቀጥታ በላቸው። ዚውስ ሲወለድ ግን እናቱ ሬያ ከክሮኖስ ሠወረችው አልተበላም። ሬያ ሕጻኑን ዚውስን ወደ ቀርጤስአማልጤያ አሳዳጊነት ላከችው። በኋላ ዚውስ ተመልሶ አባቱ ወንድሞቹን እንዲያስታውክ ልዩ መድኃኒት ይሠጣል። ከዚያ በኋላ ዚውስና ወንድሞቹ በቲታኖች ላይ በአመጽ ተነሡ።