ኅዳር ፲፫

ከውክፔዲያ
(ከኅዳር 13 የተዛወረ)

ኅዳር ፲፫ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፸፫ተኛው እና የመፀው ወቅት ፵፰ተኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፺፫ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፺፪ ቀናት ይቀራሉ።

ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት በቅርብ ነፃነቷን ክተቀዳጀችው የናይጄሪያ መንግሥት ጋር የአምባሳዶር ሏጥ እንደሚያደርጉ ይፋ አደረገ።
  • ፲፱፻፶፮ ዓ/ም - በዳላስቴክሳስ ሠላሳ አምሥተኛው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ በጠመንጃ ጥይት ተገድለው ሞቱ። በሚጓዙበት ተሽከርካሪ ውስጥ አብረዋቸው የነበሩትም የቴክሳስ ገዥ ጆን ኮናሊ በጥይት ተመተው ቆስለው ነበር። በዚህም ታሪካዊ ድርጊት የተወነጀለው ሊ ሃርቪ ኦዝዋልድ ተይዞ በቁጥጥር ሥር ሆነ። የዚያኑ ዕለት ምክትል ፕሬዚደንቱ ሊንደን ቢ ጆንሰን ሠላሳ ስድስተኛው ፕሬዚደንት ሆነው የመሀላ ሥርዐታቸውን በመፈጸም ስልጣኑን ተቀበሉ።
  • ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የቀድሞው የማዕድን ሚኒስትር አቶ ተሾመ ገብረ ማርያም በኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት (ደርግ) ታሰሩ።
  • ፲፱፻፺፭ ዓ/ም - በናይጄሪያ በወቅቱ ሊካሄድ በታቀደው ከ”ወይዘሪት ዓለም” የቁንጅና ውድድር ጋር በተያያዘ ጉርምርምታ መነሻነት “ThisDay” በተባለ የናይጄሪያ ጋዜጣ ላይ የወጣው ‘ሐይማኖት ነክ’ አንቀጽ ባስከተለው ሽብር ከሁለት መቶ በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። ውድድሩም በዚሁ ሽብር ምክንያት ወደ ለንደን ተዛወረ።[1]
  • ፲፱፻፺፯ ዓ/ም - በዩክራይን የተካሄደውን የፕሬዚደንታዊ ምርጫ ሕዝቡ ትልቅ ጭብርብርነት ተፈጽሟል በሚል መነሻነት፣ በብዙ አሥራት ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች፣ የዕጩዋቸውን፣ የቪክቶር ዩሽቼንኮን ስም እየጠሩ የኪዬቭን ከተማ አጥለቀለቋት። ይሄውም የተቃውሞ ሰልፍ “የብርቱካን አብዮት” (Orange Revolution) ተብሎ የተሰየመውን ቅስቀሳ የተጀመረበት ዕለት ነው።

ልደት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዕለተ ሞት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዋቢ ምንጮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • (እንግሊዝኛ) P.R.O., FO 371/154836 - Annual Report from Ethiopia for 1960
  • {{en]] P.R.O., FCO 371/1829 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1974
  1. ^ http://news.bbc.co.uk/1/hi/world/africa/2518977.stm