Jump to content

ናኒና ሚካኤል

ከውክፔዲያ

ናኒና ሚካኤል ማለት በጎጃም ክፍለ ሃገር የሚገኝ ሲሆን ከመርዓዊ ከተማ በ58 ኪሎሜትር ርቀት የሚገኝና የጀማ ወንዝሰቀላ ወረዳ ጋር የሚካ0ል ገጠራማ ቀበሌ ነው፡፡ ዋና ከተማው፡ ቅዳሚት ( አብራዲ ገበያ) ትምህርት ቤት ፡ ናኒና አንደኛ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ት/ቤት (1974 ተሠራ) በስፋራው የናኒና ሚካኤል ገዳም፡ የሸባይታ ሚካኤል ንዑስ ደብር የሚገኝ ሲሆን አሞራ ገደል የሚባል ትልቅ ተራራ ባለፀጋ ነው፡፡

ናኒና የቦታውን ስያሜ ያገኘው ናና ከሚባል ፈረሰኛ እንደሆነ በአፈታሪክ ይነገራል፡፡

በአገረኛ አጠራሩ ቁልጭ እቦሌ፡ ወይም እቦሌ በመባል ይታወቃል፡፡

ደርግ ስርዓት የጭነት መኪና ይደርስ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት ምንም አይነት ዘመናዊ የመጓጓዣ ዘዴ ተጠቃሚ አይደለም፡፡

በቦታው በግምት ከ2- 3 ሺህ አባ ወራዎች እንደሚኖሩ የሚገመት ሲሆን በነፍስ ወከፍ ኗሪ ቁጥር 8-10ሺህ ህዝብ እንደሚኖር ይገመታል፡፡

ናኒና በ6 ደሽ/ጎጥ የተከፋፈለ በአንድ ሰበካ ጉባኤ የሚመራ ነው፡፡ ዳንቡርታ፡ ቆለላ፡ ገርባይታ፡ አባይ፡ ደብር፡ ሰላይታ ይባላሉ፡፡

በቦታው አችፊ :ጀማ፡ ህዝብዳር፡ አረፈአይኔ፡ ላይደብር የሚባሉ ወንዞች ሲኖሩ በርካታ ምንጮች ባለፀጋ የሆነ ደጋማ ስፍራ ነው፡፡

ድንችገብስባቄላአተርአጃስንዴበቆሎተልባኑግጎመንጤፍዳጉሳ ሰብሎች በማብቀል ይታወቃል፡፡ ህዝቡ ኑሮው ባህላዊ የኑሮ ዘዴን የተከተለ ሲሆን ሙሉ በሙሉ 100% ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ ህዝብ ነው።

ናኒና ተምረው ለወግ የበቁ ምሁራኖች ሲኖሩ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በተለያየ ሙያ ዘርፍ በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡ ለመጥቀስ ያክል፡

  • ዶ/ር ጋሹ ክንዱ የቡሬ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር
  • ዘመነ ታረቀኝ ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህር
  • ግርማው አሸብር በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ የስነፅሁፍ መምህር
  • ብርሃኑ ሽፈራው መምህር
  • አውደው ታደለ መምህር
  • መንግስቱ አሸብር የመንግስት ሰራተኛ
  • አመረ መስፍን
  • ደርበው ማሞ
  • ምትኩ መስፍን
  • ገነት መስፍን
  • ሰራዊት አበራ

✈ሙላት ታደለ፡ ኢንስፔክተር ✈ዘመኑ ተፈሪ ✈አመረ ገነት ✈አንለይ አናጋው ✈ቡቃያው እውነቱ ሙጨ ኢንጅነር ✈ቀረብህ አለሙ ✈ሙሃባው የሽዋስ ✈አመረ ገነት ✈ይታክቱ አሸብር የጤና ባለሙያ ✈ዉብስራ አለምነህ ✈ሙሉቀን በቃሉ ሙሉ ✈ዳኝነት ታደለ ✈ይሔነው አሸብር ✈ሃይማኖት ተሰራ ✈አደላ አያና ✈ካሳሁን አስማማው ✈አዲሹ መንገሻ......እና ሌሎችም ተጠቃሽ ሲሆኑ በርካታ ተተኪ ወጣቶች የከፍተኛ ትምህርታቸውን የሚገኙከታተሉ ይገኛሉ፡፡ በአጠቃላይ ናኒና በወፍ በረር ለመግለፅ ያክል ይህን ይመስላል፡፡