አል-ገኒይ (በራሱ የተብቃቃ)

ከውክፔዲያ

በአቡ ሀይደር በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሓ 2) ፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡

ሀ. ትርጉም፡-

"አል-ገኒይ" የሚለው መለኮታዊ ስም ትርጉሙ፡- በራሱ የተብቃቃ ሐብታም ማለት ነው፡፡ ጌታ አላህ በራሱ የተብቃቃ የምሉእ ባሕሪያት ባለቤት በመሆኑ "አል-ገኒይ" ይባላል፡፡ ጌታ አላህ ከፍጡራኑ ምንም ነገር የማይፈልግና የማያስፈልገው አምላክ በመሆኑ "አል-ገኒይ" ይባላል፡፡ ጌታ አላህ ባሪያዎቹን ከችሮታው በመለገስ የሚያብቃቃ (ሐብታም የሚያደርግ) በመሆኑ "አል-ገኒይ" ይባላል፡፡ ጌታ አላህ የለመኑትን ሁሉ እንደ-ፍላጎታቸው ቢሰጥ ምንም የማይጎድልበት አምላክ በመሆኑ "አል-ገኒይ" ተብሎ ይጠራል፡፡ 

ለ. አመጣጡ፡-

"አል-ገኒይ" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ አስራ ስምንት ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ ከነዚህም ውስጥ፡- 
"قَوْلٌ مَعْرُوفٌ وَمَغْفِرَةٌ خَيْرٌ مِنْ صَدَقَةٍ يَتْبَعُهَا أَذًى وَاللَّهُ غَنِيٌّ حَلِيمٌ " سورة البقرة 263 

"መልካም ንግግርና ምሕረት ማድረግ ማስከፋት ከሚከተላት ምጽዋት በላጭ ነው፡፡ አላህም #ተብቃቂ ታጋሽ ነው፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 263)፡፡

"وَرَبُّكَ الْغَنِيُّ ذُو الرَّحْمَةِ إِنْ يَشَأْ يُذْهِبْكُمْ وَيَسْتَخْلِفْ مِنْ بَعْدِكُمْ مَا يَشَاءُ كَمَا أَنْشَأَكُمْ مِنْ ذُرِّيَّةِ قَوْمٍ آخَرِينَ " سورة الأنعام 133 

"ጌታህም #ተብቃቂ የእዝነት ባለቤት ነው፡፡ ቢሻ ያስወግዳችኋል፤ (ያጠፋችኋል)፡፡ ከሌሎች ሕዝቦችም ዘሮች እንዳስገኛችሁ ከበኋላችሁ የሚሻውን ይተካል፡፡" (ሱረቱል አንዓም 133)፡፡

"يَا أَيُّهَا النَّاسُ أَنْتُمُ الْفُقَرَاءُ إِلَى اللَّهِ وَاللَّهُ هُوَ الْغَنِيُّ الْحَمِيدُ " سورة فاطر 15 

"እናንተ ሰዎች ሆይ! እናንተ (ሁልጊዜ) ወደ አላህ ከጃዮች ናችሁ፤ አላህም እርሱ ተብቃቂው ምስጉኑ ነው።" (ሱረቱ ፋጢር 15)፡፡ ሐ. የምንወስደው ትምሕርት፡- 1. አላህ ከኛ የተብቃቃ መሆኑን፡- የኛ አምልኮና ታዛዥነት ጠቀሜታው ለኛው እንጂ ለአላህ አይደለም፡፡ አላህ ስላመለክነው የሚጠቀመው ስለከዳነው የሚቀርበት ነገር የለም፡፡ ጥቅምና ጉዳቱ ለኛው ነውና፡-

"فِيهِ آيَاتٌ بَيِّنَاتٌ مَقَامُ إِبْرَاهِيمَ وَمَنْ دَخَلَهُ كَانَ آمِنًا وَلِلَّهِ عَلَى النَّاسِ حِجُّ الْبَيْتِ مَنِ اسْتَطَاعَ إِلَيْهِ سَبِيلًا وَمَنْ كَفَرَ فَإِنَّ اللَّهَ غَنِيٌّ عَنِ الْعَالَمِينَ " سورة آل عمران 97 

"በዉስጡ ግልጽ የሆኑ ታምራቶች፥ የኢብራሂም መቆሚያ አለ የገባዉም ሰዉ ጸጥተኛ ይሆናል፤ ለአላህም በሰዎች ላይ ወደርሱ መኼድን በቻለ ሁሉ ላይ ቤቱን መጐብኘት ግዴታ አለባቸዉ፤ የካደም ሰዉ አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነዉ።" (ሱረቱ አለ-ዒምራን 97)፡፡

"وَلِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ وَلَقَدْ وَصَّيْنَا الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ مِنْ قَبْلِكُمْ وَإِيَّاكُمْ أَنِ اتَّقُوا اللَّهَ وَإِنْ تَكْفُرُوا فَإِنَّ لِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ وَكَانَ اللَّهُ غَنِيًّا حَمِيدًا " سورة النساء 131 

"በሰማያት ያለውና በምድርም ያለው ሁሉ የአላህ ነው። እነዚያንም ከበፊታችሁ መጽሐፍን የተሰጡትን፣ እናንተንም አላህን ፍሩ፣ በማለት በእርግጥ አዘዝን፤ ብትክዱም በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው፤ (አትጎዱትም)፤ አላህ ተብቃቂ ምስጉን ነው።" (ሱረቱ-ኒሳእ 131)፡፡

"وَقَالَ مُوسَى إِنْ تَكْفُرُوا أَنْتُمْ وَمَنْ فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا فَإِنَّ اللَّهَ لَغَنِيٌّ حَمِيدٌ " سورة إبراهيم 8 

"ሙሳም አለ፦ እናንተም በምድር ላይ ያለውም ሁሉ በመላ ብትክዱ፤ አላህ በርግጥ ተብቃቂ ምስጉን ነው።" (ሱረቱ ኢብራሂም 8)፡፡

"وَمَنْ جَاهَدَ فَإِنَّمَا يُجَاهِدُ لِنَفْسِهِ إِنَّ اللَّهَ لَغَنِيٌّ عَنِ الْعَالَمِينَ " سورة العنكبوت 6 

"የታገለ ሰውም የሚታገለው ለነፍሱ ነው፤ አላህ ከዓለማት በእርግጥ ተብቃቂ ነውና።" (ሱረቱል ዐንከቡት 6)፡፡ 2. ልጅ እንደማያስፈልገው፡- አላህ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የሱ ንብረት ነው፡፡ ዘላለማዊ ሕያው ጌታ በመሆኑም የተብቃቃ ነው፡፡ የማይሞት በመሆኑም ወራሽ ልጅ አያስፈልገውም፡፡ ሁሉን ቻይ አምላክ በመሆኑም ይደክማልና ጉልበት የሚሆነው ልጅ ይኑረው አይባልም (ተዓለላሁ ዐን-ዛሊከ ዑሉወን ከቢራ)፡-

"قَالُوا اتَّخَذَ اللَّهُ وَلَدًا سُبْحَانَهُ هُوَ الْغَنِيُّ لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ إِنْ عِنْدَكُمْ مِنْ سُلْطَانٍ بِهَذَا أَتَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ " سورة يونس 68 

"«አላህ ልጅን ያዘ (ወለደ)» አሉ፡፡ (ከሚሉት) ጥራት ተገባው፡፡ እርሱ ተብቃቂ ነው፡፡ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የርሱ ነው፡፡ እናንተ ዘንድ በዚህ (በምትሉት) ምንም አስረጅ የላችሁም፡፡ በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን" (ሱረቱ ዩኑስ 68)፡፡

"لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ وَإِنَّ اللَّهَ لَهُوَ الْغَنِيُّ الْحَمِيدُ " سورة الحج 64 

"በሰማያት ውስጥ ያለውና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው፤ አላህም እርሱ ተብቃቂው ምስጉኑ ነው።" (ሱረቱል ሐጅ 64)፡፡

"لِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْغَنِيُّ الْحَمِيدُ " سورة لقمان 26 

"በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው፤ አላህ እርሱ ተብቃቂ ምስጉን ነው።" (ሱረቱ ሉቅማን 26)፡፡ 3. ሐብትን እንደሚሰጥ፡- ጌታ አላህ በራሱ የተብቃቃ "አል-ገኒይ" እንደመሆኑ ባሮቹንም ከለመኑትና ከጸጋው ከተማጸኑት እንደሚያብቃቃቸው መረዳት ይቻላል፡-

"وَلْيَسْتَعْفِفِ الَّذِينَ لَا يَجِدُونَ نِكَاحًا حَتَّى يُغْنِيَهُمُ اللَّهُ مِنْ فَضْلِهِ... " سورة النور 33 

"እነዚያም የማግቢያን ጣጣ የማያገኙ አላህ ከችሮታው እስከሚያከብራቸው ድረስ ይጠበቁ…" (ሱረቱ-ኑር 33)፡፡

"وَأَنَّهُ خَلَقَ الزَّوْجَيْنِ الذَّكَرَ وَالْأُنْثَى * مِنْ نُطْفَةٍ إِذَا تُمْنَى * وَأَنَّ عَلَيْهِ النَّشْأَةَ الْأُخْرَى * وَأَنَّهُ هُوَ أَغْنَى وَأَقْنَى " سورة النجم 48-45 

"እርሱም ሁለቱን ዓይነቶች ወንድና ሴትን ፈጠረ። ከፍትወት ጠብታ (በማኅፀን ውስጥ) በምትፈስስ ጊዜ፤ የኋለኛይቱም ማስነሳት በርሱ ላይ ነው። እነሆ እርሱም አከበረ፤ ጥሪተኛም አደረገ።" (ሱረቱ-ነጅም 45-48)፡፡

"أَلَمْ يَجِدْكَ يَتِيمًا فَآوَى * وَوَجَدَكَ ضَالًّا فَهَدَى * وَوَجَدَكَ عَائِلًا فَأَغْنَى " سورة الضحى 8-6 

"የቲም ሆነህ አላገኘህምና አላስጠጋህምን? (አስጠግቶሃል)።የሳትክም ሆነህ አገኘህ፤ መራህም። ድኻም ሆነህ አገኘህ፤ አከበረህም።" (ሱረቱ-ዱሓ 6-8)፡፡ 4. ከሱ ውጭ ያለው ሁሉ ድኃ መሆኑን፡- እውነተኛ ሐብታም አላህ ብቻ ነው፡፡ በራሱ የተብቃቃ ጌታ በመሆኑ፡፡ የሌላው ግን አንጻራዊ ነው፡፡ የአንዱ የሐብት መጠን ከሌላው አንጻር በሚለው መስፈሪያ ነው ሐብታምና ድኃ ተብለው የሚከፋፈሉት፡፡ ሁሉም ግን አላህ ዘንድ ድኃዎች ናቸው፡፡ ከአላህ መብቃቃትና ሌላውንም ማብቃቃት ስለማይችሉ፡-

"وَاذْكُرْ فِي الْكِتَابِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّهُ كَانَ صِدِّيقًا نَبِيًّا * إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ يَا أَبَتِ لِمَ تَعْبُدُ مَا لَا يَسْمَعُ وَلَا يُبْصِرُ وَلَا يُغْنِي عَنْكَ شَيْئًا " سورة إبراهيم 42-41 

" እኛ ምድርን፣ በርሷም ላይ ያለውን ሁሉ እኛ እንወርሳለን፤ ወደኛም ይመለሳሉ። በመጽሐፉ ውስጥ ኢብራሂምንም አዉሳ፤ እርሱ በጣም እውነተኛ ነቢይ ነበርና። " (ሱረቱ መርየም 41-42)፡፡

"يَا أَيُّهَا النَّاسُ أَنْتُمُ الْفُقَرَاءُ إِلَى اللَّهِ وَاللَّهُ هُوَ الْغَنِيُّ الْحَمِيدُ " سورة فاطر 15 

"እላንተ ሰዎች ሆይ! እናንተ (ሁልጊዜ) ወደ አላህ ከጃዮች ናችሁ፤ አላህም እርሱ ተብቃቂው ምስጉኑ ነው።" (ሱረቱ ፋጢር 15)፡፡

አምላካችን አላህ ሆይ! አንተ በችሮታህ ካንተ ውጭ ካለው ነገር ሁሉ አብቃቃን፡፡ የሰው ፊት ከመጠበቅም አድነን አሚን፡፡ ይቀጥላል፡፡