አስኩና
Appearance
አስኩና በጉዋጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ከወረዳው ርእሰ ከተማ ከቲሊሊ በስተምስራቅ ይገኛል።አስኩና በተፈጥሮ ፀጋ የተዋበ እና ብዙ አይነት የእፅዋት ዝርያዎች ይገኙበታል።ይህ ቀበሌ ብዙ አመታትን ያስቆጠረ የሰው ልጅ የሰራው ማይመስል ግን በሰው ልጆች ድንቅ ጥበብ ከጭቃ የተሰራ እፁብ ድንቅ የሆነ ቤተ ክርስቲያንን አቅፎ ይዟል።ይህ ቤተ ክርስቲያን በውስጡ ብዙ ቅዱስ መፃህፋትን ይዟል።አስኩና በቆዳ ስፋቱ በጣም ብዙ ስፍራዎችን አጠቃሎ ይዟል።በተጨማሪም በውስጡ ብዙ ወንዞች በጣም ጣፋጭ የሆኑ ምንጮች ይገኛሉ።እንዲሁም ለመድሀኒትነት የሚጠቀሙበት የአምቦ ውሀ ይገኛል።በቀበሌው በጣም ብዙ የሆኑ ምርቶች ይበቅላሉ።በጣም በስፋት ከሚመረቱ ምርቶች ሰፊውን ስፍራ የሚይዘው የድንች ምርት ነው፣የድንች ምርት በአመት ሁለት ጊዜ ይመረታል፣ሰው ሁሌም አመት እስከ አመት ከድንች ተለይቶ አያውቅም።ከዚህ በተጨማሪም ጤፍ፣ስንዴ፣በቆሎ፣ገብስ፣ባቄላ እና አተር በስፋት ይመረታል።አስኩና ለኑሮ አመቺ በጣም አሪፍ አካባቢ ነው።በውስጡ ብዙ እፅዋቶችም ይገኛሉ።ከነዚህም መካከል ቀርከሃ፣ሾላ፣ቀጋ፣ውልክፋ፣አሽኩዋር፣እንጆሪ፣ኮርች፤ሆማ፣ቁልቋል፣ግራር፣ባህርዛፍ፣ስሚዛ፣ግራዋ፣ጨባ፣እና ሌሎች በርካታ እፅዋት ይገኙበታል።