አበበ ገላው

ከውክፔዲያ

አበበ ገላውኢሳት (የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሌቭዥን) ጋዜጠኛ ሲሆን በአሜሪካን በሮናልድ ሬገን ሕንጻ የምግብ ዋስትናን አስምልክቶ ግንቦት ፰ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. በተካሄደው የቡድን ፰ (Group 8) ስብስባ ላይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ንግግር ለማድርግ በጀመሩ ጊዜ በከፍተኛ ድምጽ በመጮህ ጠቅላይ ሚኒስተሩ አምባገነን እንደሆኑና፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የመብት ረገጣ ወንጀል እንዳካሄዱ፣ የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ እና «ምግብ ያለ ነፃነት ዋጋ ቢስ ነው... ነፃነት.. ነፃነት... ነፃነት...» በማለት (በእንግሊዝኛ) ድምፁን አሰማ። ብዙ ኢትዮጵያውያን ሲያደንቁት ጥቂት የመንግሥት ደጋፊዎች ደግሞ ዝተውበታል።