አባል:ባሕረ ሐሳብ

ከውክፔዲያ

የመስከረም መባቻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ  አሕዱ አምላክ አሜን✝

ገፅ ፩

ሰላም ለእናንተ ይሁን ውድ የዚህ ብሎግ ተከታታዮች ቃል በገባሁት መሰረት ዛሬ

የመስከረም መባቻ ፣ዮሐንስ፣መስከረም አንድ፣ርእሰ አውደ አመት የሚውልበትን ዕለት እንዴት አንደሚወጣ እናያለን፡፡

🖍በኢትዮጵያና በግብፅ የዘመን አቆጣጥር መሰረት መስከረም አንድ የአመቱ የመጀመሪያው ወር የመጀመሪያው ቀን ነው፡፡ሁሉም አንደሚያውቀው ማንኛውም ወር የሚጀምረው አንድ ብሎ ነው፡፡ ነገር ግን ይህች አንድ ቀን ከሰባቱ አለታት በሄትኛው ዕለት ትውላለች የሚለውን  አውቆ መመለስ ተገቢ ነው፡፡

🖍የመስከረምን መባቻ ማወቅ በዚያ አመት  ከምንፈልገውን ወር ውስጥ ያለን ቀን ዕለቱን ለማወቅ ይረዳል፣መሠረትም ነው፡፡

ስለዚህ ዛሬ የመጀመሪያው መንገድ ከማየታችን በፊት ለመንገድ አንድ መሰረት የሆኑትን ነገሮች እናያለን፡፡

                  🔑ጥንተ ቀመር🔑

📜ጥንት ማለት መነሻ(መዠመሪያ) ማለት ነው፡፡ሲበዛ ጥንታት ይባላል፡፡

-ጥንተ ቀመር👉 ማለት ቀመር የተዠመረበት ማለት ነው(ዘመን ቆጠራ የተዠመረበት) ማለት ነው፡፡ ያም ቀን ማግሰኞ ነው፡፡

          ሶስቱ  የፀሐይ ጥንታት

-የፀሐይ ጥንታት ሶስት ናቸው እነሱም፡-

1⃣አለም የተፈጠረበት እሁድ ጥንተ እለት

2⃣እፅዋት ፣አዝርዕት ፣አትክልት የተፈጠሩበት ማግሰኞ ጥንተ ቀመር

3⃣ፀሐይ ጨረቃ የተፈጠሩበት ዕሮቡ ጥንተዮን ናቸው፡፡

🔑ዘመን ሲቆጠር የሚዠመረው አለም ከተፈጠረበት ከእሁድ ሳይሆን እፅዋት አዝርዕትና አትክልት በተፈጠሩበት ከማግሰኞ ነው፡፡

❓ሌሊትን ከመዓልት የሚለዩ ፀሐይና ጨረቃ የተፈጠሩበት ረቡዕ ሲሆን ለምንድን ነው ማግሰኞ የቀመር መጀመሪያ የሆነው፡፡❓

ይህ የሆነበት ምክንያት

    በመጀመሪያ👉ከፍሬና ከአበባ ጋር ዛፎች ሁሉ የበቀሉበት የብስ የታየበት ማያት(ውሃ)የተከፈሉበት የመዠመሪያ ወር የባቱበት ዕለት መግሰኞ ስለሆነ

   በሁለተኛ👉መፅውንና ፀደይን(በለግ) ክረምትንና ሐጋይን(በጋ) የምትለይ ማዕከላዊት፣ኮኮባዊት የሆነች አንዲት ቀን ከንቱ ሁና እንዳትቀር ቀመራቸውን በማግሰኞ ጀምረዋል፡፡(ዘፍ 1:14-19)

  በሶስተኛ👉ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በ5500 ዓመት በዕለተ እሁድ በዘመነ ዮሐንስ ተፀንሶ በ5501 ዓመት በዕለተ ስሉስ(ማግሰኞ) በዘመነ ማቴዎስ ሰለተወለደ፡፡

🖍የጥንተ ቀመር መመላለሻው 7 ነው እሱም ከማግሰኞ እስከ ሰኞ ነው፡፡

🖍እንደ አዋጅ የምትወሰድ በቃልም መያዝ ያለበት፡፡

   🔑 አዋጅ ፩🔑

            👇

   ተካፍሎ ከመጣው ወጤት የተረፈው

🖋🖋🖋🖋🖋🖋🖋🖋🖋🖋🖋🖋

                    1 ከሆነ መግሰኞ

                     2 ከሆነ ዕረቡ

                     3 ከሆነ ሀሙስ

                     4 ከሆነ አርብ

                     5 ከሆነ ቅዳሜ

                     6 ከሆነ እሁድ

        7(0/እኩል/) ከሆነ ሰኞ🖋🖋🖋🖋🖋🖋🖋🖋🖋🖋🖋🖋🖋🖋🖋

ከ7 ከበለጠ ደግሞ በ7 ማካፈል፡፡

ይህን ካወቅን መንገድ አንድን እንይ

          📖 መንገድ አንድ📖

ይህም የምናየው ጥንተ ቀመርን መሰረት በማድረግ ነው፡፡

1⃣  ዓመተ አለምን ለአራት እናካፍላለን፡፡ከዚያ መጠነ ራብዕትን(1/4) እናገኛለን፡፡

2⃣  መጠነ ራብዕትን ከዓመተ አለም ጋር እንደምራለን፡፡ከዚያም ያን ለ7 እናካፍላለን፡፡

3⃣ከዚያ ከመጣው ውጤት የተረፈውን እንደ አዋጅ ፩ መሰረት መቁጠር ነው፡፡

ምሳሌ ፩👇👇👇

🖍7513(2013 ዓ.ም) እንውስድ

1⃣ 7513(ዓ.ዓ)÷4=1878(መጠነ ራብዕት)

2⃣ 1878+7513=9391

3⃣ 9391÷7=1341 ሁኖ 4 ይተርፋል፡፡

ስለዚህ የ2013 ዓ.ም እንቁጣጣሽ (በዓለ ዮሐንስ) የሚውልበት እለት አርብ ነው ማለት ነው፡፡ምክንያቱም ማግሰኞ አንድ ተብሎ መቆጠር ሲጀምር በአራተኛው ዕለተ አርብን እናገኛለን ማለት ነው፡፡

ምሳሌ ፪ 👇👇👇

🖍5510(10 ዓ.ም) እንውሰድ

1⃣5510÷4=1377

2⃣1377+5510=6887

3⃣6887÷7=983 ሁኖ 6 ይተርፋል፡፡

ስለዚህ የ10 ዓ.ም መስከረም የሚበብተው(የሚውለው) እሁድ ነው፡፡

ምሳሌ ፪  👇👇👇

🖍7584(2084 ዓ.ም)ን እንውሰድ

1⃣7584÷4=1896

2⃣1896+7584=9480

3⃣9480÷7=1354 ሁኖ 2 ይተርፋል ፡፡

ስለዚህ 2084 ዓ.ም መስከረም 1 በዕለት ዕረቡ ይበብታል ፡፡

ምሳሌ ፬  👇👇👇

🖍7499(1999 ዓ.ም)ን እንውሰድ

1⃣7499÷4=1874

2⃣1874+7499=9373

3⃣9373÷7=1339 ሁኖ ምንም አይተርፍም(እኩል ነው)

ስለዚህ በ1999 ዓ.ም እንቁጣጣሽ በዕለተ ሰኑይ ውሎ ነበር ማለት ነው፡፡

ሁሉም ይህን ያውቁ ዘንድ share ያድርጉ::

በቀጣይ መንገድ ሁለትን ይዠ እቀርባለሁ፡፡📜

             ወሰብሐት ለእግዚአብሔር

             ወለወላዲቱ ድንግል

              ወለመስቀሉ ክቡር

                 ይቆየን