አባል:Amil aliff

ከውክፔዲያ

የነብያት ታሪክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አደም[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አደምአ.ሰ

አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ አደምን ዐ ሰ ለመፍጠር በፈለገ ግዜ ጂብሪልን ወደ መሬት ወርዶ አፈር ዘግኖ እንዲያመጣ ላከው።

ጅብሪልም ወደ መሬት ከወረደ በኋላ ከመሬት አፈር ሊዘግን ሲል መሬትም፦"እንዳትቀንሰኝ በአላህ እጠበቃለሁ" አለችው። ጅብሪልም በአላህ እጠበቃለሁ ስትለው ምንም ሳይነካት ትቶ ተመለሰ። አላህም ዘንድ መጣ'ና ፦"ጌታዬ ምድር ባንተ እጠበቃለሁ ስትለኝ ተመለስኩ" አለው።

ከዚያም አላህ ሚካኢልን ላከው።ሚካኢልም ትእዛዙን ሊፈፅም ወደ ምድር ሲወርድ መሬትም፦" እንዳትቀንሰኝ በአላህ እጠበቃለሁ" አለችው። ሚካኢልም በአላህ እጠበቃለሁ ስትለው ምንም ሳይነካት ትቶ ተመለሰ።

አላህም ዘንድ መጣ'ና ፦"ጌታዬ ምድር ባንተ እጠበቃለሁ ስትለኝ ተመለስኩ" አለው።

በመጨረሻም አላህ አዝራኢልን ላከው አዝራኢልም ተልዕኮውን ሊፈፅም ምድር ላይ ወረደ'ና አፈር ሊዘግን ሲል ምድር፦" እንዳትቀንሰኝ በአላህ እጠበቃለሁ" አለችው። አዝራኢልም፦"እኔ እራሴ የአላህን ትዕዛዝ ሳልፈፅም ከመመለስ በአላህ እጠበቃለሁ" ብሏት አፈር ከተለያየ ቦታ መዘጋገን ጀመረ። ከጥቁሩም፣ከነጩም፣ከቀዩም...ዘገነ።ለዛ ነው የሰው ልጆች መልክም የተለያየው።ከዚያም አፈሩን ይዞ አላህ ዘንድ ሲቀርብ አላህም፦"አፈሩን አንተ እንዳመጣህ ሁላ ነፍሳቸውንም እንድታወጣ አንተን ወክዬሀሁ" አለው።

ከዚያም ከምድር የመጣው አፈር ረጥቦ ጭቃ ሲሆን ግዜ አላህ ለመላዕክቶቹ፦"እኔ ከጭቃ ሰውን ልፈጥር ነው። ፍጥረቱንም ባስተካከልኩና ከመንፈሴ በነፋሁበት ጊዜ ለእርሱ ሰጋጆች ኾናችሁ ውደቁ።" ብሎ መልዕክት አስተላለፈላቸው።

ከዚያም አላህም ኢብሊስ እንዳይኩራራ አደምን በእጁ ፈጠረው።ከዚያም ለ40 አመት ያህል ጭቃው ቅርፅ ብቻ ሆኖ ከረመ።እና መላዕክት በዛ በኩል ሲያልፉ አደምን ሲያዩት በጣም ይፈሩ ነበረ...ነፍስም አልገባለትም ነበር።

ከሁሉም በላይ እሚፈራው ኢብሊስ ነበር።ኢብሊስ ሁሌ ከአደም ጭቃ አጠገብ ሲያልፍ መታ አድርጎት ነበር ሚያልፈው።ያን ግዜ ሸክላ ሲመታ እሚወጣው ድምፅ ይሰማ ነበር።

ከዚያም ኢብሊስ ከአደም ጭቃ ጎን ላይ ቆሞ፦"አንተማ ለሆነ ነገር ነው የተፈጠርከው" እያለ በአፉ እየገባ በመቀመጫው ይወጣ ጀመር...ለመላዕክትም፦"እኔ በዚህ ላይ ከተሾምኩ አጠፋዋለሁ" በማለት ይዝት ጀመር።

አላህም በአደም ገላ ላይ ነፍስ መንፋት በፈለገ ግዜ መላዕክትን፦"ልክ ሩሁን/ነፍሱን እንደነፋሁለት ሰጋጆች ሆናችሁ አጎብድዱ" ብሎ አዘዛቸው። መላዕክትም ዝግጁ ሁነው መጠባበቅ ሲጀምሩ አላህ በአደም ሩሁን/ነፍሱን መንፋት ሲጀምር ገና ነፍሱ በአደም ጭንቅላት በኩል ስትገባ አደም አስነጠሰው። መላዕክትም፦"አልሀምዱሊላህ በል" አሉት። አደምም፦"አልሀምዱሊላህ" ሲል... አላህ ደግሞ፦"ጌታህ ይማርህ" ብሎ መለሰለት።

ከዚያም ነፍሱ አይኑ ጋ ስትደርስ የጀነት ውስጥ ፍራፍሬዎችን ተመለከተ አንገቱ ላይ ስትደርስ ደግሞ ፍራፍሬዎችን መብላት አሰኘው'ና ገና ነፍሱ እግሩ ላይ ሳትደርስ ሄዶ ለመብላት ተጣደፈ።

ነፍሱ መላ ሰውነቱ ላይ ስትሰራጭ ከመላዕክት ሁሉ ቀድሞ ሱጁድ ያደረገለት ኢስራፊል ነበር። ከዚያም አላህ ለአደም፦"ሂድ እነዛን ሰላም በላቸው'ና ምን ብለው እንደሚመልሱልህ አድምጥ" ብሎ ላከው። ሄዶ ሰላም ሲላቸውም መላዕክትም፦"ወዐለይኩሙሰ ላም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ" ብለው መለሱለት። አላህም ለአደም፦"አደም ሆይ! ካሁን በኋላ ይህ ያንተ እና የዝርዮችህ ሰላምታ ሆኖ ይዘልቃል" አለው።

አደምም፦"ጌታዬ ዝርዮቼ እነ ማን ናቸው?" ብሎ ጠየቀው። አላህም፦"ከሁለቱ እጆቼ ምርጥ" አለው። አደምም፦"ቀኝህን መርጫለሁ ሁለቱም እጆችህ ቀኝ ናቸው" ብሎ ሲል...

አላህም እጁን ሲከፍትለት አደም እስከቂያማ ድረስ ያሉ ልጆቹን ሁሉ ተመለከተ።በዚያም መሀል አንድ ብርሀናማ ሰው ተመለከተ'ና፦"ያ አላህ ይህ ማን ነው?" ሲል ጠየቀ።

አላህም፦"እሱ ልጅህ ዳዉድ ነው"ብሎ መለሰለት። አደምም፦"ጌታዬ ለዚህ ልጄ እድሜውን ስንት ነው ያደረግክለት?" ብሎ ሲጠይቅ... አላህም፦"60 ነው" አለው።

አደምም፦"ጌታዬ ከኔ እድሜ 40 ቀንስ'ና ለሱ ጨምረህ መቶ ሙላለት" አለው።(ለአደም የተመደበለት እድሜ 1000 ነበር) አላህም እሺ ብሎ ሞላለት'ና ምስካሪ መላዕክቶችንም አደረገ።

ከዝያም አላህ ዳግም ለአደም ልጆቹን ሁሉ ሲያሳየው አንዱ ጤነኛ ነው፣አንዱ እግር የለውም፣አንዱ መስማት የተሳነው ነው፣አንዱማየት የተሳነው ነው....በቃ ይህን ሁሉ ሲመለከት፦"ምንው ጌታዬ ሁሉን እኩል ብትፈጥር ምን አለበት" ሲለው አላህም፦"አንተ አደም እኔ እንድመሰገን እፈልጋለሁ" ብሎ መለሰለት...ምስጋና ይገባህ ውዱ ጌታዬ... ከዚያም አላህ የአደምን ጀርባውን አንድ ግዜ አብሶ የሰው ልጆችን ሁሉ አወጣ።

ከዚያም ሰበሰባቸው'ና፦"ጌታችሁ አይደለሁምን?" ብሎ ሲጠይቃቸው፦"አዎ ጌታችን ነህ እንመሰክራለን" ይላሉ።

ከዚያም አላህም፦"እኔ ሰባት ሰማያትን እና ሰባት ምድርን፣መላዕክቶችንም፣አባታችሁ አደምንም እናንተ ላይ ምስክር አድርጊያለሁ። የቂያማ ቀን ስጠይቃችሁ አላወቅንም ነበር ብላችሁ እንዳትክዱ አሁንም እወቁ!!! ከኔ ሌላ አምላክ የለም ከኔ ሌላም ጌታ የለም።በኔም ምንንም አካል እንዳታጋሩ። እኔ ወደ እናንተ መልዕክተኞቼን/ነቢያቶችን ቃል ክዳኔን እና ዛቻዬን የሚነግሯችሁ ሲሆኑ እልክላችኋላሁ። መፅሀፎቼንም አወርድላችኋለሁ" አላቸው።

የአደም ዝርያዎችም፦"ካንተ ሌላ ጌታ እንደሌለ እንመሰክራለን...ካንተ ሌላ አምላክ እንደሌለም እንመሰክራለን" ብለው ቃል ኪዳን ገቡ። አሁን ደግሞ ወደ ኢብሊስ ልመልሳችሁ...ምነው ደከማችሁ እንዴ ያ ጀማዓ? አይዟችሁ ውዶቼ እሽ!!! ቅድም ከመላዕክት ሁሉ ቀድሞ ለአደም ሱጁድ ያደረገው ኢስራፊል ነው ብያችሁ አልነበር!!! እስራፊልን ተከትለው ሁሉም መላዕክት ሱጁድ አድርገው ነበር ግን አቶ ኢብሊስ ሁሉም ሱጁድ ሲወርድ እሷ ዘና ብላ ቆመች።

አላህም፦" ኢብሊስ ሆይ! በሁለት እጆቼ (በኃይሌ) ለፈጠርኩት ከመስገድ ምን ከለከለህ? (አሁን) ኮራህን? ወይስ (ፊቱኑ) ከትዕቢተኞቹ ነበርክ?" ብሎ ሲለው... ኢብሊስም፦" እኔ ከእርሱ በላጭ ነኝ፡፡ ከእሳት ፈጠርከኝ፤ አደምን ደሞ ከጭቃ ፈጠርከው" አለ። አላህም፦" ከጀነት ውጣ፤ አንተ የተባረርክ ነህና... እርግማኔም እስከ ፍርዱ ቀን ድረስ ባንተ ላይ ይኹን" አለው።

ኢብሊስም፦" ጌታዬ ሆይ! እስከሚቀሰቀሱበት (የቂያማ) ቀን ድረስ አቆየኝ" አለው። አላህም ጥያቄውን ተቀብሎት እስከቂያማ ድረስ ኢብሊስን ሊያቆየው ቃል ገባለት።ከዚያም ኢብሊስ፦" በአሸናፊነትህ ይኹንብኝ፤ የአደምን ልጆች ከእነርሱ ምርጥ የኾኑት ባሮችህ ብቻ ሲቀሩ በመላ አሳስታቸዋለሁ፡፡" ሲል ዛተ።

አላህም፦"አንተን እና ከአደም ልጆች የተከተሉህን ሁሌ ጀሀነም እንደምሞላችሁ ቃል እገባለሁ" አለ። ከዚያም አላህ ኢብሊስን ከጀነት አውጥቶ አደምን ጀነት አስቀመጠው።

አደምም እማያውቀው ቦታ ላይ አንድ አጫዋች በሌለበት ቁጭ ብሎ የድብርት ስሜት ተሰማው። ከዝያም ጋደም ባለበት ድንገት እንቅልፍ ሸለብ አደረገው።

ልክ ከእንቅልፉ ሲነቃ እራስጌው ላይ አንዲት ሴት ተመለከት ከአይኖቿ ፍቅር እና እዝነት ይነበብባታል። አደም፦"ከመተኛቴ በፊት እዚህ አልነበርሽም" ሀዋ፦"አዎ" አደም፦"በተኘሁበት ነው የመጣሽው ማለት ነዋ!!!" ሀዋ፦"አዎ" አደም፦"ኬት ነው የመጣሽው" ሀዋ፦"ካንተ ውስጥ ነው የመጣሁት።አንተ በተኛህበት ነው አላህ ካንተ የፈጠረኝ። አደም፦"ለምንድነው አላህ የፈጠረሽ?" ሀዋ፦"አንተ እኔ ላይ ልትረጋ" አደም አላህን አመሰገነ'ና፦'ብቸኝነት እየተሰማኝ ነበር" አለ። ከዚያም መላዕክት መጡ'ና፦"ስሟ ማን ነው?" አሉት። አደምም፦"ሀዋ" አለ። መላዕክትም፦"ለምንድነው ሀዋ ተብላ የተሰየመችው" ብለው ሲጠይቁት አደምም፦'እሷ ከኔ ነው የተፈጠረችው እኔ ደግም ህያው ነኝ ለዛ ነው ሀዋ ያልኳት"ብሎ መለሰላቸው።

ከዚያም አድም እና ሀዋ በጀነት ውስጥ ሳሉ አላህ አደምን እንዲህም አለው፦"አንተ አደም ጀነት ውስጥ ላንተ ሁሉ ነገር ሀላል ሲሆን ይህችን ቅጠል ላንተም ለሚስትህም ሀራም አድርጌያለሁ'ና እንዳትቀርቧት" ከዚያም ሁለቱም በጀነት እየተዝናኑ ሳለ ኢብሊስ መጣ'ና አጠገባቸው ማልቀስ ጀመረ። ፦"ምን ሁነሀል?" ብለው ሲጠይቁት እንዲህ በማለት መለሰላቸው፦

"እንዲህ ስትዝናኑ በጣም ታምራላችሁ ግን በጣም እኔ ሚያሳዝነኝ ይሄ ደስታችሁ ዘለቄታ አይኖረውም።ግን ይህ ደስታችሁ ዘላለማዊ እንዲሆን ምትፈልጉ እንደሆን ይህችን ቅጠል ብሏት።ምክንያቱም አላህ ጌታችሁም መልኣኮች እንዳትኾኑ ወይም ከዘላለም ነዋሪዎች እንዳትኾኑ እንጂ ከዚህች ዛፍ አልከለከላችሁም" ብሎ በመወስወስ አሳስቶ ቅጠሏን አበላቸው።

(በነገራችን ላይ አንዳንድ ሰዎች በውድቅ ንግግሮቻቸው ሴቶችን መውቀስ ሲፈልጉ ፨ሀዋ ናት አደምን ያሳሳተችው፨ ይላሉ ይህ ከእውነት የራቀ ነው ሀዋ አይደለችም ቅጠሉን እንዲበሉ የገፋፋችው።ሁሉቱም ናቸው ተሳስተው የበሉት።) አደም በስህተት የቀመሳትን ቅጠል መብላት ሲጀምር ልቡን እያመመው መጣ...ፍርሀት እና አለመረጋጋት ነገሰበት።

ዞር ብሎ ሚስቱን ሲያይ እርቃኗን ናት። እራሱንም ሲመለከት እርቃኑን መሆኑ ታወቀው። ከዚያም ቅጠል በመበጠስ ሀፍረተ ገላዎቻቸውን መሸፈን ጀመሩ።

በፈፀሙትም ሀፅያትም ተፀፅተው እንዲህ በማለት አላህን ይማፀኑ ጀመር፦" ጌታችን ሆይ! ነፍሶቻችንን በደልን፡፡ አንተ ለእኛ ባትምር ባታዝንልንም በእርግጥ ከከሳሪዎቹ እንኾናለን"

አላህም ወደ ምድር እንዲወርዱትዕዛዙን አስተላለፈ እንዲህም አላቸው፦" ከፊላችሁ ለከፊሉ ጠላት ሲኾን ውረዱ፡፡ ለእናንተም በምድር ላይ እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ መርጊያና መጠቀሚያ አላችሁ። በእርሷ/በምድር ላይ ትኖራላችሁ፡፡ በእርሷም ላይ ትሞታላችሁ፡፡ ከእርሷም ውስጥ ትወጣላችሁ" አሁን አደም እና ሀዋም ጉዞ ወደ ምድር....

አላህ ሁለቱንም ወደ ምድር ሲያወርዳቸው አደም ትካዜ ተቆጣጠረው፣ እጅጉን ሀሳብ ገባው...ሀዋ ደሞ ማልቀስ የሌት ተቀን ተግባሯ ሆነ። ከዚያም አላህ ለሁለቱም፦"ምድር እኮ እናንተ የመጣችሁበት ምንጫችሁ ናት።ከአፈር ነው የተፈጠራችሁት ወደአፈር ነው ምትመለሱት...ከአፈርም ነው ምትቀሰቀሱት" እያለ አፅናናቸው።

ከዚያም አደም እና ሀዋ መሬት ላይ ቁጭ ብለው ሳለ ጂብሪል( ዐ ሰ ) 7 የስንዴ ፍሬዎችን ይዞለት መጣ እያንዳንዱ ፍሬ 70ሺህ ዘለላ ያበቅል ነበር።አደምም ለጅብሪል፦"ምን ላድርገው" አለው። ጂብሪልም፦"መሬት ላይ ዝራው" አለው። አደምም ዘራው'ና ጂብሪል እያሳየው አጨደ። አዚያም ፈጨው...ከዚያም አቦከው...ከዚያም ጋገረው እና ሲቀዘቅዝ ከባለቤቱ ጋር በመብላት የህይወትን ውጣ ውረድ ይላመድ ጀመር...

ሁለቱም ሚለብሱት ነገር ስላልነበራቸው በግ አረደ'ና ቆዳውን ለራሱም ለሷም ልብስ ሰርቶ ለበሱ። እንዲ እንዲ እያሉ የህይወትን ውጣ ውረዶች ለመዱት ልጆችም መውለድ ጀመሩ።ሀዋ ሁሌ ምትወልደው መንታ መንታ ነበር አንድ ወንድ እና አንድ ሴት...ልጆቻቸውን ሲያጋቡ በአንድ ላይ የተወለዱትን አያጋቡም ነበር አንድ ላይ የተወለዱት ሴቷ በሌላ ግዜ የተወለደውን ወንድ ስታገባ ወንዱም እንደዛው።

አንድ ግዜ ሀቢል እና ቃቢል የተባሉp የአደም ልጆች ሁለቱም መንትያ እህቶች አሏቸው እና ሀቢል የቃቢልን እህት(አብራው የተወለደችውን) ማግባት ፈልጎ ሲጠይቅ ቆንጆ ስለነበረች ቃቢል ለራሱ ፈልጓት ለሀቢል ከለከለው።

አደምም ቃቢል እህቱን ለሀቢል እንዲድርለት ሲጠይቅም ፍቃደኛ አልሆን አለ።ከዚያም አደምም ለሁለቱ ልጆችቁርባን እንዲያዘገጁ አዘዛቸው'ና አድም ሀጅ ሊያደርግ ወደ መካ ተነሳ(ሀጅ በኢብራሂ ግዜ የተጀመረ እንዳይመስላችሁ ድሮም ቦታዋ ትታወቃለች)

ከዚያም አደም ልጆቹን የሚያስጠብቀው አካል የለም'ና ሰማያትን ልጆቹን እንዲጠብቁ አደራ ሲል እንቢ አሉ...ምድርንም ሲጠይቃት እንቢ አለች ተራራዎችንም ሲለምን ሀላፊነት መውሰድ ሀሉም ፈሩ።ግን ልጁ ቃቢል እኔ እወስዳለሁ ብሎ የአደምን ልጆች ሀላፊነት ቃቢል ተሸከመ። አደምም ጉዞውን ቀጠለ..

አደም ከሄደ በኋላ ልጆቹ ሀቢል እና ቃቢል ልጅቷን ለማግባት ለአላህ ቁርባን አቀረቡ።ሀቢል እረኛ ነገር ስለነበር ጥሩ የሚያምር ለአይን ሚማርክ ሙኩት አቀረበ...ቃቢል ደሞ ገበሬ ነበር ግን ተራ ውዳቂ እህል ነው ያቀረበው። የሁለቱም ቁርባኖች አንድ ቦታ ሳሉ ከሰማይ እሳት ወረደች'ና የሀቢልን ቁርባን በላች(ቁርባኑ ተቀባይነት አግኝቷል ማለት ነው) የቃቢልን ግን ተወችው።(አላህ አልተቀበለውም ማለት ነው)


ያን ግዜ ቃቢልም፦"እህቴን ምታገባ እንደሆን እገድልሀለሁ" አለው ሀቢልን። ሀቢልም፦"አላህ የሚቀበለው ከጥንቁቆች(እሱን ከሚፈሩት) ነው" አለው። ያን ግዜ ቃቢልም ወንድሙን ሀቢልን በያዘው ብረት ጭንቅላቱን መቶት ጣለው።(ስለአገዳደሉ የኡለማኦች ልዩነት አለ እሱን ልዘረዝር አልፈልግም) ቃቢል ወንድሙን ከገደለው በኋላ ሬሳውን ምን እንደሚያደርግ ጠፍቶበት አንድ አመት ሙሉ በጀርባው ተሸክሞ ሲዞር ከርሟል ይባላል። በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለ አንድ ቀን የወንድሙን ሬሳ እንዴት እንደሚሸሽግ ያሳየው ዘንድ አላህ መሬትን የሚጭር ቁራ ላከለት፡፡ ቃቢልም፦«ወይ እኔ የወንድሜን ሬሳ እሸሽግ ዘንድ እንደዚህ ቁራ ብጤ መኾን አቃተኝን» አለ፡፡

ቃቢል ወንድሙን ሀቢል ከቀበረው በኋላ በመግደሉ በጣም ተፀፀተ። አደምም የልጁን ሞት ሲሰማ በከፍተኛ ሁኔታ አዘነ። የቃቢልም ቅጣቱ ከዱንያ ጀመረ ሁለቱ ታፋዎቹ ተጣበቁ።ፀሀይ ወደዞረችበት ሁሉ አላህ የቃቢል አይን እንድታፈጥ አደረገ መቃጣጫ ይሆነው ዘንድ። አደም እና ሀዋ በልጃቸው ሀቢል ሀዘን በጣሙን ስለተጎዱ አላህ ሸይስ የሚባል መልካም ልጅ ሰጥቶ ሀዘናቸውን አስረሳቸው።