አባል:Sualih astatke

ከውክፔዲያ

title           = ሃያሉ ንጉስ=

|image            = 200بك

| caption         = ምናባዊ የሶላሁዲን ስእል

ሶላሑዲን አል አዩቢይ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የታሪኩ ፀሃፊዎችና የዘመን ጓዶቹ በሚግባቡበት የዓረብኛ ቋንቋ ሲያሞካሹት አሸናፊው ንጉስ፣ አባ ድሉ፣ አባ ጀብዱ፣ ትንግርተኛው መሪ፣ ሽንፈት የማያውቀው ጦረኛ፣ ጉምቱ ፈረሰኛ፣ ሊቀ ጠበብት ይሉታል። ታሪኩን በኩርዱ ቋንቋ የፃፉት የታሪክ ልሒቃን ደግሞ ከዚህም በላይ የሙገሳ ቃላት ይገባዋልና ያዥጎደጉዱለታል።

ለ262 ተከታታይ ዓመታት የቆየውን የፋጢሚያ ስረወ መንግስት ገርስሶ በዓባስያ ስረወ መንግስት ጥላ ስር ግብፅን፣ ሶሪያን፣ ጆርዳንን፣ ፍልስጤምን፣ ሊባኖስን፣ ቱሃማንና የመንን በአንድ ግዛት ስር ያዋለውን የአዩቢያ ስረዎ መንግስት አቋቁሟል።

በመስቀል ጦረኞች ቁጥጥር ስር ውለው የነበሩትን የተባረኩ ሃገራት የቁድስን ከተማ ጨምሮ በሃይልና በዲፕሎማሲ ወደ ኢስላማዊ አስተዳደር መልሷል።

እ.ኤ.አ በአስራ ሁለተኛው ክፍለ ዘመን ገናና ከነበሩት የአውሮጳ ፈረንጅ አምባ ገነን መንግስታትና የመስቀል ጦረኞች ጋር በርካታ ታላላቅ ጦርነቶችን አድርጎ አሰቃቂ በሚባል ደረጃ ድል ነስቷል።

በፈረንሳያውያንና እንግሊዛውያን ሙስሊም ያልሆኑ የታሪክ ሊቃውንትና ደራሲያን ባዘጋጇቸውና በመላው አውሮጳ በተሰራጩት ብሎም ወደተለያየ ቋንቋ በተተረጎሙት መፅሃፍቶች ላይ ምንም ቢጠሉት እንኳ ስለ ብልሃቱና ጀግንነቱ አውርተው አይጠግቡም።

ትልቁ ባላንጣው የሆነው የእንግሊዙ ንጉስ ቀዳማዊ ሪቻርድ እንኳን ቢያገኘው በጥርሱ ሊዘለዝለው እያማረው ጀግንነቱ ሲነሳ ግን "የአንበሳ ልብ ያለው መሪ ነው" ሲል ያሞካሸውና ይመሰክርለት ነበር።

በኢስላማዊ አስተሳሰቡ ሱፍይ ሲሆን የዓቂዳ መዝሃቡ አሽዓርያ እንደሆነ፣ ለዚህ መዝሃብም ከፍተኛ ፍቅር የነበረው እንደነበር ሙስሊም የታሪኩ ፀሃፊዎች በአንድነት ይስማሙበታል። ለማንኛውም የሃሳብ እገዛም ከማንም በፊት የሱፍይ ሊቃውንትን ያስቀድም እነደነበርና ልሒቃኑ ከጎኑ እንዲጠፉ የማይፈልግ መሆኑም እንዲሁ በፀሃፊዎቹ ተደጋግሞ ተፅፏል።

በ533ኛው ዓ.ሂ ላይ አባቱን ነጅሙዲን አዩብን ለመዘየር በድንገት የተገኙት ታላቁ የሱፍዮች መሪና የጦሪቃ ባለቤት ገውሱ ዓብዱል ቃዲር አል ጀይላኒ አይተዉት ዱዓ በማድረግ ባርከውታል። ከዛ በኃላም ለጠላቱ የእግር እሳት ሆኖ ኖሯል።

በጊዜው ስሙ ብቻ የፈረንጆችን ልብ የማስሸበር አቅም ነበረው። እይታውም ያርዳቸው ከፊል የማይባሉትንም ያስሸናቸው ነበር። ግርማ ሞገሱ ለአትኩሮት የሚገድ፣ ፈረስ ግልቢያው ልዩ መስህብ የተላበሰ ነበር

ውልደት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ፈረሰኛው ሶላሑዲን የተወለዱት ዒራቅ ውስጥ በምትገኝ ቲክሪት በተባለች ከተማ ነው። ይህቺ ከተማ የቅርብ ጊዜው ዓለም አቀፍ ተፅዕኖ ፈጣሪ ተጋፋጭና ጀግና ፕሬዘዳንት ሶዳም ሑሴን የተወለደባትና ያደገባት ከተማ ናት። ፈረሰኛው ሶላሑዲን የተወለዱበት አመት ደግሞ በሂጅራ አቆጣጠር በ532 ዓሂ በኤሮፓውያን አቆጣጠር ደግሞ በ1138 ዓል ነበር።

የፈረሰኛው አባት ነጅሙዲን አዩብ ቲክሪት ውስጥ የሚገኝ ምሽግ ውስጥ የሚኖሩ አስተዳዳሪ ነበሩ። ታድያ ያንን ምሽግ ለቀው በዕለበክን ለማስተዳደር ወደ በዕለበክ እንዲጓዙ ታዘው ለጉዞ በመረጡትና በተነሱበት ቀን ነበር ሚስታቸው ድንገተኛ ትልቅ ሰው ሊገላገሉ ምጥ ያጣደፋቸው። እናም ፈረሰኛው በዚያች የአጣብቂኝ እለት ተወልደው የመጀመርያውን ህይወት የዘሩበት ቅፅበት በጉዞ ጀመሩ።

የፈረሰኛው የዘር ግንድ በታሪክ ሊቃውንት ዘንድ የተለያየ አስተያየት የተሰጠበት ሲሆን ከፊሎቹ ዘራቸው የኩርድ ነው ሲሉ ከፊሎቹ ደግሞ ሶላሁዲን የዓረብ ዝርያ ያለባቸው ሹም ናቸው ይላሉ።

የፈረሰኛው አባት ነጅሙዲን የበዕለበክ አስተዳዳሪ በመሆን ሰባት አመታትን ካሳለፉ በኃላ ጉዟቸውን ወደ ደማስቆ አዞሩ። ፈረሰኛው ሶላሑዲን የልጅነት እድሜያቸውን ያሳለፉትም በዝህችው በደማስቆ ነው። ፈረሰኛው በደማስቆ ያሳለፉት ህይወት የተመሳቀለ ቢሆንም ክፉ ደግ ያዩባትና የተማሩባት ብሎም ትዝታዎቻቸው የተዋቀሩባት ከተማ ናትና ለደማስቆ ዘለቅ ያለ ፍቅር እንደነበራቸው ይነገራል።

ፈረሰኛው በደማስቆ እጅግ በርካታ የትምህርት ዘርፎችን ተምረዋል። በየዘርፉ ያላቸውን እውቀት የተነተኑት የታሪክ ፀሃፊያን ሱልጣኑ በሆነ የእውቀት ዘርፍ ትንተና ሲሰጡ እድሜያቸውን በዚህ ዘርፍ የፈጁና ከዚህ ዘርፍ ውጪ ያልተማሩ ይመስላሉ ሲሉ ያሞካሿቸወል። በሇላ ለጠላቶቻቸው አይበገሬ እንዲሆኑ ያደረጋቸውም ይኸው የበዛ ዓለማዊና ዲናዊ መሆኑ እሙን ነው።

ፈረሰኛው በደማስቆ ቆይታቸው በደማስቆው አሚር መወደዳቸው እውቀትን ያለ ገደብ የመማር እድል እንደፈጠረላቸው ይታመናል። በገቡበት የዕውቀት ፈን ሁሉም በከፍተኛ ውጤት የሚያጠናቅቁ ሰው ነበሩ።

በዚህም መሰረት በሸሪዓዊ እውቀት በኩል ብዙ ፈኖችን እንዳጠኑና ሊቅ የሚያስብል ደረጃን ያለፉ በልጅነታቸው በረካ የተደረገላቸው ዓሊም እንደሆኑ ፀሃፍያን በአንድ ብዕር ከትበዋል።

ከዲናዊ እውቀት ባሻገር ፈረሰኛው የምህንድስና፣ የውትድርና፣ በታሪክና ዝርያ ጥናት፣ በሒሳብ ስሌት፣ በስነ ሰውነት ግንባታ፣ በስፓርት፣ በብረት ስራና በስነ ፈለክ አንቱ የተባሉ ሊቅ እንደነበሩ ወዳጆቻቸው ሳይሆኑ ጠላት የሆኑት የፈረንሳይና የእንግሊዝ ፀሃፊያንም ምስክርነት የሰጡበት ጉዳይ ነው።