Jump to content

አባል ውይይት:Abkebede

Page contents not supported in other languages.
ርዕስ ጨምር
ከውክፔዲያ

ስለ ግራቪቲ ሞገድ ግኝት

ሰሞኑን በፊዚክስ አለም ከፍተኛ አድናቆትና ያስከተለ ስራ በዜና ተሰራጭቷል -ይህ ዜና ስለግራቪቲ ሞገድ (Gravity Wave) መገኝት ነው- በመጀመርያ ዜናውን ከማብራራታችን በፊት ስለሞገድ እንነጋገር- የግራ ቪቲ ሞግድ ባህርዩ ልክ እንደ ብርሃን ሞገድ ነው፨ ሁለቱ በባህርይ አንድ ሲሆኑ አመጣጣቸው ይለያያል የብርሃን ሞግድ (Electromagnetic Wave) ምንጩ የኤሌክሮን ንዝረት (vibration) ሲሆን የግራሺቲ ሞገድ ምንጩ የክብደት(mass) ንዝረት ነው፨ በነገራችን ላይ ክብደትና ሚዛን የተለያዩ ናቸው፨ ግራቪቲን ለግዜው ተውት እናድርግና የብርሃን ሞገድ አመጣጥን እንይ- አሁን ብዙ ሰው በየቤቱ ሬድዮ ያዳምጣል ቴሌቪዥንም ያያል- እነዚህ ሁለት መሳሪያዎች እንዴት አድርገው ነው እንፎርሜሽን የሚስቡት ? ሁለት ነግሮች ያስፈልጋሉ 1) የኢንፎርሜሽን ምንጭ (transmitter) 2) የኢፎርሜሽን ተቀባይ (Receiver) ናቸው - ሁለቱም አንቴናዎች ሲሆኑ ኢፎርሜሽኑን የብርሃን ሞገድ ተሸክሞ ከምንጩ(transmitter) ወደ ተቀባዩ(Receiver) ያስተላልፋል፨ የብርሃን ሞገድ ምንጩ አንቴናው ውስጥያሉት ኤሌክትሮኖች ስለሚነዝሩ ነው፨ የሚነዝር ነገር ሁሉ ባካባቢው(Field) ሞገድ ይፈጥራል፨ የግራሺቲ ሞገድ ምንጩ የክብደት(mass) ንዝረት ነው ስንል ምን ማለታችን ነው ? ይህን ጥያቄ ለመመለስ መጀመርያ ስለ ግራቪቲ ማወቅ ያስፈልጋል- በተፈጥሮ አራት መሰረታዊ ሃይሎች (Fundamental Forces) አሉ- እነርሱም ኤሌክትሮ ማግኔቲዝም ፦ኤሌክትሮ ዊክ፦ኑክሊያር ና ግራቪቲ ናቸው- ግራቪቲ የህዋን አወቃቀር ያቀፈ ሀይል ነው- እንግዲህ መሬት ላይ ያለ ማንኛውም ነገር ሊኖር የቻለው በግራቪቲ ምክንያት ነው-የወቅቶች መቀያየር ሊኖር የቻለው መሬት በጸሃይ ዙርያ ሰለምትዞር ነው-ልትዞር የቻለችበት ምክንያት በጸሃይ ግራሺቲ ምክንያት ነው- በትልቅ ደረጃ ሲንወስደው ጸሃይና በጸሃይ ዙሪት የሚዞሩት ፕላኔቶች ስርአታቸውን የወሰነው ግራቪቲ ነው- ከፍ ብለን እንሂድ ካልን ደግሞ ጸሃይና በጸሃይ ዙሪት የሚዞሩት ፕላኔቶች ያሉበት እምሆል (Milky Way Galaxy) የተቋጨው በግራቪቲ ነው- አሁንም ከፍ ብለን እንሂድ ካልን የኛ እምሆል ያለበት ብዙ እምሆሎች ያሉበት የእምሆሎች ስብስብ (Local Group) የተቋጨው በግራቪቲ ነው- እንደዚህ እያልን ስንሄድ ፍጥረተ አለምን (Universe) በሙሉ አቀናጅቶ የያዘው ሃይል ግራቪቲ መሆኑን እንረዳለን፨ትምርት ቤት ስለግራቪቲ ስንማር ከመሬት ስበት ጋር እያያዝን ነው፨ ለምሳሌ አንደ ነገር ከከፍታ ሲወደቅ፦የተወረወረ ኳስ የተወሰነ ከፍታ ደርሶ ተመልሶ ሲወድቅ እናያለን፨አልበርት አይንስታይን (Albert Einstein) የተባለ በጣም የታወቀ የፍዚክስ ተመራማሪ ስለግራቪት አዲስ አይነት ሕሳቤ(theory) አቅርቧል፦ ሕሳቤው እንዲህ ይላል ክብደት ያለው ባካባቢው ያለውን ሕዋ (space) ያጦዘዋል(ጡዘት ወይም curvature). ይህንን ለመረዳት የሚቀጥለውን ሙከራ አድርጉ 1)አራት ሆናችሁ አንድ አንሶላ በአራት ማዕዘን ይዛችሁ ወጥሩት 2) አንድ ጓደኛችሁ ደግሞ ከማዕዘኖቹ እልፍ እልፍ አርጎ መሃል ሳይደርስ አራት ሳንቲሞች ያስቀምጥ 3) አሁን ጓደኛችሁ ከፍ ያለ ክብደት ያለው አሎሎ የተወጠረው አንሶላ መሃል ላይ ያስቀምጥ ጥያቄ፦ በየማዕዘኑ የተቀመጡት ሳንቲሞች ወዴት ይሄዳሉ ? መልስ፦ወደ አንሶላው መሀል ወደ አሎሎው ይሳባሉ ምንክያት፦ አሎሎው አንሶላውን ወይም ሕዋን (space) ስለቀየረው ነው ትልቁ ግንዛቤ እዚህ ላይ ነው፦አሁን ይህ አሎሎ የሚንቀሳቀስ ከሆነ በተለይ ደግሞ ንዝረት (vibration) ካለው አንሶላውም አብሮት ይነዝራል- ይሄ ልክ ውሃ ላይ እንደሚፈጠረው ንዝረት አይነት ነው- አሁን ለምሳሌ በሳፋ በቂ ውሃ አድርገሽ መሃሉ ላይ በጣትሽ ብትኮረኩሪው ሞገዱ ክብ እየሰራ ሲሄድ ታይዋለሽ- አልበርት አይንስታይን የግራሺቲ ሞገድ መኖሩን ሕሳቤ ያቀረበው በ1915 (1907 ዓም) ሲሆን በሙከራ (experiment) የተገኘው በ2016 (2008 ዓም) ነው ልክ የብርሃንን ሞገድ በኤሌክትሪክ አንቴናዎች ማግኘት እንደተቻለው LIGO የተባለ የተራቀቀ መሳርያ የግራቪቲን ሞገድ ሊያገኝ ችሏል- የግራቪቲ ሞገድ ሃይሉ እጅግ በጣም ትንሽ ስለሆነ የሚነዝረው ክብደት እጅግ በጣም ብዙ መሆን አለበት- በፍጥረተ ዓለም ውስጥ እጅግ ግዙፍ የሆኑ የሚንዘርዘሩ (undergo vibration) አሉ -እንደ መቀመቀቅ ማንኝውንም ነገር የብርሃን ሞገድ እንኳን ሳይቀር የሚውጡ አሉ-በከዋክብት ጥናት ጥቁር ቀዳዳዎች (Black Holes) ይባላሉ- ጥቁር የተባሉት በቀለም ሳይሆን ምንም አይነት ብርሃን ሰለማያመነጩ ወይም ስለማያንጸባርቁ ነው- እንደነዚህ አይነት ግዙፍ ጥቁር ቀዳዳዎች እየተሽከረከሩ እርስ በርሳቸው ቢዋዋጡ የግራቪቲ ሞገድ በሕዋ ውስጥ እነዲነሳ ያደርጋሉ ማለት ነው- LIGO ይህንን የግራቪቲ ሞገድ ሊያገኝ ችሏል-

Start a discussion with Abkebede

Start a discussion