አትክልት

ከውክፔዲያ
ቢጫ አበባ

ዕፅዋት ከሕያዋን ነገሮች አምስቱ ዋና ዘርፎች አንዱ ናቸው። ምግበለፊ ውኑክለስ ናቸው፣ ይህም ማለት የራሳቸውን ምግብ ይሰራሉ እና ውስብስብ ወይም ባለኑክለስ ህዋስ (ሴሎች) ያላቸው ናቸው። አብዛኞቹ ዕፅዋት ከስፍራ ወደ ስፍራ መዛወር እንደ እንስሶች አይችሉም። ሲበቅሉ ግን እጅግ ቀስ ብለው ይዞራሉ።

በዕፅዋት ዘርፍ ውስጥ ታዋቂ አይነቶች ዛፍዕፅቊጥቋጥሣርሐረግፈርንሽበትአረንጓዴ ዋቅላሚ ይገኛሉ። በዕፅዋት ጥናት ዘንድ፣ አሁን 350,000 ያሕል የዕፅዋት ዝርያዎች ይኖራሉ። ፈንገስ እና አረንጓዴ ያልሆነ ዋቅላሚ ግን እንደ ዕፅዋት አይቆጠሩም።

አብዛኛዎቹ ዕፅዋት በመሬት ውስጥ ይበቅላሉ፣ አገዳቸው ከላይና ሥራቸው በታች አላቸው። አንዳንድ በውኃ ላይ ሰፋፊዎች ናቸው። ውኃና ምግብ የሚያገኙ በሥሮቻቸው በኩል ነው፤ ከዚያ በአገዳ ወጥተው እስከ ቅጠሎች ድረስ ሲጓዙ ነው። በቅጠሎች ውስጥ በሚገኙት ትንንሽ ቀዳዳዎች ውኃ በፀሐይ ዋዕይ በመትነን፣ ውኃው በአገዳው መንገድ ምግብን ከታቹ ወደ ላይ ይስባል። ይህም ስበተ ቅጠላበት ይባላል።

ዕፅዋት ምግብን እንዲሠሩ፣ የሚያስፈልጉዋቸው የፀሐይ ብርሃን፣ ካርቦን ክልቶኦክሳይድ፣ የመሬት ማዕድንና ውኃ ነው። አረንጓዴው ሃመልሚል (ክሎሮፊል) የፀሐይቱን አቅም ይወስዳል።

እንደ እንሥሣት፣ ዕፅዋትም የእንስትና የተባእት የዘር ህዋስ (gamete) ያመነጫሉ። በተጨማሪ፣ ብዙ የዕፅዋት አይነቶች ወሲባዊ በማይሆን ዘዴ መስፋፋትና መባዛት ይችላሉ። ይህ እፃዊ ተዋልዶ ይባላል።

ሥነ ሕይወታዊ ክፍፍሎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሥነ ሕይወት ጥናት ዘንድ፣ ዕፅዋት አንድ የሕይወት ስፍን ሲሆን የሚከተሉ ክፍለስፍኖች ብውስጡ ይመደባሉ፦

የመሬት ሃመልማል Embryophyte ሃመልማል Viridiplantae
አረንጓዴ ዋቅላሚ
ሌላ ዋቅላሚ Biliphyta (ባብዛኛው እንደ አትክልት አይመደቡም)
ክፍለስፍን ሮማይስጥ መኖሪያ የባሕርይ ልዩነት ዝርያ ቁጥር
ዱኬ ቀንድ Anthocerotophyta[1] ዓለም አቀፍ ቀንድ ያለ ዱኬ ወለድ፣ ሸንዳ የለሽ 100-300+
ሳረንስት Bryophyta አለም አቀፍ ዘለቄታዊ ቅርንጫፍ የለሽ ዱኬ ወለድ፣ ሸንዳ የለሽ 12000 ያህል
የባሕር ድንጋይ አረንጌዴ ዋቅላሚ Charophyta ጨው አልባ ውሆች 1000 ያህል
የባሕር አረንጓዴ ዋቅላሚ Chlorophyta አለም አቀፍ 7000 ያህል
የንጉሥ አሚዶ ዘምባባ ክፍለስፍን Cycadophyta ገሞጂዎች ባዶ ዘር፣ የድርብርብ ቅጠል አናት 100-200
የብር ባሕርኮክ (ጊንኮ) Ginkgophyta ቻይና ባዶ ዘር ዛፍ 1 ብቻ
ሰማያዊ ዋቅላሚ Glaucophyta ጨው አልባ ውሆች 13
የመሊንጆ ክፍለስፍን Gnetophyta አንዳንድ አገሮች ባለዘር፣ ሸንዳማ እንጨት 70
የበትረሳረንሰት ክፍለስፍን Lycopodiophyta

Lycophyta

አለም አቀፍ ነጠላ ሸንዳ ዕጽ 1290
ክንንብ ዘር፣ አባቢ አትክልት Magnoliophyta አለም አቀፍ አበባ፣ ፍሬ፣ ሸንዳማ እፅ 300,000
ጉብ ዕጽ Marchantiophyta,[2]

Hepatophyta

አለም አቀፍ ኢዘለቄታዊ፣ ቅርንጫፍ የለሽ ዱኬ ወለድ፤ ሸንዳ የለሽ 9000 ያህል
ዘረ ቅምብብ Pinophyta

Coniferophyta

አለም አቀፍ ባለዘር ቅምብብ፣ ሸንዳማ እንጨት 629
ፈርን Monilophyta አለም አቀፍ ቀዳማይ ብቃይ ህዋስ ወለድ እፅ፣ ሸንዳማ 9000 ያህል
ቀይ ዋቅላሚ Rhodophyta ዓለም አቀፍ 7000 ያህል
ድምሩ፦ 14
  1. ^ Mauseth, James D. (2012). Botany : An Introduction to Plant Biology (5th ed.). Sudbury, MA: Jones and Bartlett Learning. ISBN 978-1-4496-6580-7.  p. 489
  2. ^ Crandall-Stotler, Barbara; Stotler, Raymond E. (2000). "Morphology and classification of the Marchantiophyta". in A. Jonathan Shaw & Bernard Goffinet (Eds.). Bryophyte Biology. Cambridge: Cambridge University Press. p. 21. ISBN 0-521-66097-1.