ኡቦ

ከውክፔዲያ

ኡቦስዊድን አፈ ታሪክማጎግ 3ኛው ልጅ፣ የስዊድን 2ኛው ንጉሥ፣ እና የኡፕሳላ ከተማ መሥራች ነበረ።

1546 ዓ.ም. በኡፕሳላ ኤጲስ ቆጶስዮሓንስ ማግኑስ በታተመው የስዊድን ታሪክ መጽሐፍ እንደሚለው፣ ኡቦ ከባቢሎን ግንብ ውድቀት 115 ዓመታት በኋላ የስዊዶች ንጉሥ ሆኖ ሥፍራውን ለራሱ ስም «ኡፕሳላ» (የኡቦ አዳራሽ) ሰየመው። ከወንድሙ ስዌኖ መሞት ጀምሮ ለ101 ዓመታት (ምናልባት 2312-2211 ዓክልበ.) እንደ ነገሠ ይባላል። ከማግኑስ መጽሐፍ በቀር ምንም ማስረጃ ባለመኖሩ ግን የአሁኑ ታሪክ ሊቃውንት ይህን እንደ እውነት አይቀበሉም።