እንዳለጌታ ከበደ

ከውክፔዲያ

የኢትዮጵያ ደራስያን ማህበር ዋና ፀሐፊ የሆነው ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ (ዶክተር) ሰባተኛ መፅሐፉን “ጽላሎት” በሚል ርዕስ ባለፈው ረቡዕ ለንባብ አበቃ፡፡ 11 ታሪኮችን የያዘው የአጫጭር ታሪኮች መድበል በ30 ብር እየተሸጠ ነው፡፡ በቅርቡ የማስተርስ ዲግሪውን በፎክሎር የትምህረት ዘርፍ ያገኘው እንዳለጌታ ከበደ፤ ከአሁን ቀደም

- እምቢታ


- ደርሶ መልስ


- ዛጎል


- የመኝታ ቤቶች ምስጢሮች


- ኬር ሻዶ


-- ከጥቁር ሰማይ ሥር


- በዓሉ ግርማ ሕይዎቱና ሥራዎቹ


- ምሳሌ


- ጽላሎት


- መክሊት


- ያልተቀበልናቸው


- ማዕቀብ


- ደቦ


- የካሳ ፈረሶች (ታሪካዊ ተውኔት) የተሰኙ መፃሕፍትን ለንባብ ያበቃ ሲሆን በሌሎች መድበሎችም ሥራዎቹ ታትመውለታል፡፡

እንዳለጌታ (ዶክተር) መጽሐፍትን ሰብስቦ ለማረሚያ ቤቶችና ትምህርት ቤቶች ማሰራጨት የሚታወቅበት ተግባሩ ነው።

"ልዩነቱ ይሄ [የመጽሐፍት ባንኩ] የተደራጀ የተቀናጀ ቋሚ ቢሮ፣ ቋሚ ሠራተኛ ያለው ወጪ የሚጠይቅ ጉልበት የሚጠይቅ መሆኑ ነው። .... ያነበቡ እንዴት እንደሚፈወሱ አይቻለሁ። ያነበቡ የሚያደርጉትን ያውቃሉ። የሚያደርጉትን ካወቁ ደግሞ ኃላፊነት ይሰማቸዋል። ኃላፊነት የሚሰማው ደግሞ ለራሱም ለአገሩም መድኃኒት ለመሆን እንጂ ችግር ውስጥ ለመክተት የሚተጋ አይሆንም " ሲል ለዛጎል የመጽሐፍት ባንክ መመስረት ምክንያት የሆነውን ጉዳይ አስረድቷል።


ዛጎል የመጽሐፍት ባንክ ከምስረታው ጀምሮ ባሉት ስድስት ወራት በአገሪቱ ለሚገኙ 40 ቤተ መጽሐፍት ለእያንዳንዳቸው ከ200 እስከ 300 የሚሆኑ የመጽሐፍት ድጋፍ የማድረግ ውጥን አለው። እስከ ነሐሴ ወር የመጀመሪያ ሳምንት ባንኩ ለ32 ቤተ መጽሐፍት የመጽሐፍ ስጦታ እንደተደረገ እንዳለጌታ (ዶ/ር) ጠቅሷል።

መላኩ ዳንኤል (MelDan) ሲያማእ