እዩሱስ ክርስቶስ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search
የናዝሬቱ እየሱስ ክርስቶስ
እየሱስ ክርስቶስ የመንግሥተ ሰማይ ባለቤትዋ የመንገዷም መሪ
ወልድ ዋህድ
የተወለደው በ፩ኛው ዓ.ም. በቤተልሔም
ዓመተ ምሕረትም ስለሱ ተቆጠረ
የእናት ስም ማርያም
ድንግል ማርያም.jpeg
የአባት ስም እግዚአብሔር አብ (ያሳደገው ቅዱስ ዮሴፍ እንደ አባት)
በሰማይ መንፈሳዊ እናት በምድር ሥጋዊ አባት የለውም
ዓመታዊ ዋና በዐላት ፱ሲሆኑ ዋና ዋናዎቹ
ገና (ልደት)
 ስቅለት
ትንሳዔ (ፋሲካ)
ያደገበት ቦታ ናዝሬት-ገሊላ
ያረፈው በ፴፫ኛው ዓ.ም. በእየሩሳሌም እየሱስ መስዋት.jpeg
ከሙታን ተለይቶ የተነሳው ባረፈ በ፫ኛው ቀን በእየሩሳሌም
የሚመለከው በመላው የክርስትና ሃይማኖት እምነት ተከታይ ሕዝብ [1]


በ14ኛው ከፍለ ዘመን መሰራቱ የሚታመን የእየሱስና የማሪያም ምስል ፣ በተጨማሪ ይህ ስዕል እቴጌ ምንትዋብማርያምና ለልጇ እየሱስ ስትሰግድ ለራሷ ማስታወሻ ያሣለችው ስዕል ነው።

ኢየሱስ (በዕብራይስጥ: ሲጻፍ ישוע ፣ ሲነበብ፡ የሹዓ፣ ትርጉሙም፡ የሚያድን ማለት ነው) የክርስትና ሃይማኖት መሰረት ነው። ክርስቶስ ማለት በግሪክ ቋንቋ Χριστός ነው፤ ይህም መሢሕ ማለት ነው (በዕብራይስጥ ማሺያሕ ወይም 'የተቀባ' ማለት ሲሆን በተጨማሪም አማኑኤል ይባላል ትርጉሙም እግዚአብሔር ከኛ ጋር ሆነ) ማለት ነው።

እየሱሰ በክርስትና ሃይማኖት አንድ አምላክ ከሚሆኑት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንዱ ወልድ እሱ ነው ፤ ይህም ወልድ ፣ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ

የኢየሱስ ክርስቶስ ልደትና ጥምቀት

እንደ ሰው በምድር ተመላልሶ የአባቱን መንግሥት አስተምሮ ለሰው ልጅ መዳን ሲል ራሱን አሳልፎ የሰጠ በመጨረሻም ከሞት ተነስቶ መንፈስ ቅዱስ እንዲተካው አድርጎ ወደ ሰማይ አርጎ በአባቱ ቀኝ የተቀመጠ ይህን ዓለም ለመፍረድ ዳግም ምፃቱ የሚጠበቅ አምላክ እና ፈጣሪ ነው ። ስለኢየሱስ የበለጠ ለመረዳት አዲስ ኪዳንን በተለይ ወንጌል በአራቱ ሐዋርያት ፣ በቅዱስ ማርቆስቅዱስ ሉቃስቅዱስ ዮሐንስቅዱስ ማቴዎስ የተፃፈውን ያንብቡ ።


እንዲሁም አንዳንድ ሃይማኖቶች ደግሞ የእግዚአብሔር መልዕክተኛ ነው ሲሉ አንዳንዶቹ ደግሞ ነቢይ ነው ብለው ያምናሉ።

  1. ^ በፕዪው የጥናት መዐከል መሠረት : በ፳፻፲፭ ዓ.ም. በተደረገው ግምት የዓለም ክርስቲያን ሕዝብ በ፳፻፶ ዓ.ም. ወደ ፫ቢሊዮን ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል