ከፋ
[1]የካፊቾ ብሔረሰብ ታሪክ ካፋ የሚለዉ ስያሜ በደቡብ ኢትዮጵያ ከነበሩት የቀድሞ የቦንጋ ግዛት የሚካተቱ ሰፊ ህዝቦች ናቸዉ። የጎንጋ ህዝቦች የሚባሉት የእናሪያ፣ የቦሾ ወይም ጋሮ ፣ካፋ ፤ ሽናሻ ወይም ቦሮ ሽናሻ እና አኒፊሎ ወይም ቡሽሽ ናቸዉ።የካፋ ህዝቦች አመጣጥ ከግብፅ ነዉ የሚሉ ያሉ ሲሆን ሌሎች የጎንጋ ማህበረሰቦች ቀደምት ግዛቶች አመጣጥ ትግረ እንዲሁም ከእስራኤልና የመን እንደሆነ ይገልፃሉ።በሁለተኛው ሀሳብ የሚስማሙ ምሁራን እስራኤሎች በግብጹ ንጉስ ፈርዖን ቅኝ አገዛዝ ዘመን በነበረዉ ረሀብና ድርቅ ተሰደዉ የአባይን ወንዝ ተከትለዉ ለእርሻ ተስማሚ ወደ ሆነ ለም መሬት እንደተጓዙ ይህም ጉዞ ካፋ እንደተባለ ያብራራሉ።ካፋ ማለት ከሞት ወደ ህይወት ጉዞ እንደማለት ነዉ!። የቀድሞና ያሁኑ የታሪክ ተመራማሪዎች እንደሚገልጹት የከፋ ግዛተ መንግስት የተቋቋመው በመካከለኛው ክፍለ ዘመን 500-1500 ከክርስቶስ ልደት በፊት ነው፡፡ ለረዥም ጊዜ የከፋ ግዛት የራሱ የሆነ የአስተዳደር ስርአት ባለቤት ሆኖ በሶስት ስርወ መንግስታት ማለትም ማንጆ፤ማቱ እና ሚንጁ በሚባሉ የሚመራ እንደነበር ተመራማሪዎች ይገልጻሉ፡፡እነዚህም ከ13ኛ እስከ 19ኛመቶ ክፍለ ዘመን ድረስ ጠንካራ እና እራሳቸውን የቻሉ ስርወ መንግስታት ነበሩ፡፡በዚህ መካከል ከ20 በላይ ነገስታት በከፋ ግዛት ተፈራርቀዋል፡፡የመጨረሻው የከፋ ስርወ መንግስት ሚንጆ ሲሆን ይህም ማዕከላዊ መንግስትና ታቶ በተባሉ መንፈሳዊ ንጉስ የሚመራ አምባገነን ስርአት እንደነበር ይነገራል፡፡ በ እ.
ኤ.አ 1897 የመጨረሻው የከፋ ግዛት ንጉስ የነበሩት ታቶ ጋኪ ሽራቾ ተይዘው ስርአቱ እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡ከከፋ ግዛት ጋር አዋሳኛ የነበሩት አርባ ነገስታት ለከፋ ንጉስ ግብር ይገብሩ እንደነበር ይነገራል፡፡በ19ኛ ክፍለ ዘመን ከፋ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ከተቀላቀለች በኋላ እስከ 1991 ድረስ የአውራጃ ስያሜ ተሰጥቶ ጅማ ዋና ከተማ ነበረች፡፡ በአሁኑ ወቅት ከፋ ከደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች መንግስት አንዱ ዞን ሆኖ በአስር ወረዳዎች የተከፋፈለ ነው፡፡በከፋ የሚኖሩ ሶስት ነባር ብሄረሰቦች ያሉ ሲሆን እነሱም ከፊቾ 80% ሌሎች ናኦ እና ጫራ ናቸው፡፡ የከፊቾ ቋንቋ ከፊኖ በመባል ይታወቃል፡፡ 1.2 የከፋ ዞን ስነ-ምህዳር
የከፋ ዞን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በ60' 24' እስከ 70'7ዐ• ሰሜን እና 35'69. እስከ 36'78• ምስራቅ ላይ ይገኛል፡፡የከፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ከአዲስ አበባ 460 ኪ.ሜ
ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ከፋ ከደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች መንግስት 13 ዞኖችና ስምንት ልዩ ወረዳዎች አንዱ ነው፡፡ የዞኑ የመሬት ስፋት ጠቅላላ 10,602.7 ኪ.ሜ ስኩዌር ሲሆን ከክልሉ 7.06% ስፋት ይሸፍናል፡፡ዞኑ በሰሜን ከኦሮሚያ እና ከሰሜን ምዕራበ በኮንታ ልዩ ወረዳ በምስራቅ በደቡብ ከደቡበ ኦሞ ጋር በቤንችማጅ ዞን በምዕራብ ከደቡብ ምዕራብ ከሸካ ዞን ጋር ይዋሰናል፡፡
የከፋ ዞን በአስር ወረዳዎች የተከፋፈለ ሲሆን እነዚህም አዲዮ፣ቢታ፣ጨና፣ጨታ፣ዴቻ፣ገዋታ፣ጌሻ፣ጊምቦ፣ሳይለም፣ ጠሎ እና ቦንጋ ከተማ አስተዳደር ናቸው፡፡
የከፋ ዞን የአረቢካ ቡና ዋና መገኛ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ቡና ምንጩና መገኛዉ በዴቻ ወረዳ ማኪራ በተባለ ቦታ እንደተገኘ ይነገራል፡፡በከፋ ዞን የሚገኘዉ የጥቅጥቅ ደን
በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ጥቂት የቡና ደኖች ዉስጥ አንዱ ነው፡፡ ካፋ የኢትዮጵያ የቡና ዝርያ ምንጭ ሆኖ
ይጠቀሳል፡፡ከፋ ሶስት የአየር ንብረት ዞኖች የሉት ሲሆን እነሱም ደጋ 2500-3000 ሜትር በላይ ወይና ደጋ 1500-2500 ሜትር እና ቆላ 500-1500 ሜትር ከፍታ ያለው ነው፡፡የከፋ ዞን ከ500 እስከ 3500ሜትር ከፍታ መካከል ይገኛል፡፡
የአካባቢው የሙቀት መጠን 17-20 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ የሚደርስ ሲሆን የካቲት፣መጋቢት እና ሚያዚያ ሞቃታማ ወራት ናቸው፡፡የከፋ ተራራማ መሬቶች፣የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የዝናብ ሰጭ አካባቢዎች ናቸው፡፡ይህም በመሆኑ ከዓመት ዓመት አረንጓዴ ደኖች እና ዛፎች የተከበበች ዞን እንድትሆን አድርጓታል፡፡የቦንጋና አካባቢው የዝናብ መጠን 1300-2000ሚ.ሜ ይደርሳል፡፡ ከፍተኛው የዝናብ መጠን በአካባቢው በግንቦትና መስከረም ቢሆንም በሁሉም ወራት መጠነኛ ዝናብ ይኖራሉ፡፡
በ1999 በስታቲስቲክ ባለስልጣን በወጣው ሪፖርት የከፋ ህዝብ ብዛት 880,251 ሲሆን ከዚህ ውስጥ 812,387 ወይም 92.3 ፐርሰንት በገጠር የሚኖሩ ሲሆን 67,864 ወይም 7.3 ፐርሰንት በከተማ የሚኖሩ ናቸው፡፡ ከዞኑ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት መረጃ እንደተገኘው በዞኑ ከ20 በላይ የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች የሚኖሩ ሲሆን ከፊቾ ብሄረሰብ 71.8% ሸካ ብሄረሰብ 6.36% ቤንች 5.23% እና አማራ 6.86% ይገኛሉ፡፡ የቀረው ድርሻ ያላቸው የአካባቢው ነዋሪዎች የጫራ፣የዳውሮ፣ናኦ እና መአኒት እና ሌሎችም ብሄረሰቦች ናቸው፡፡በከፋ ዞን ካሉት ማህበረሰቦች ውስጥ ሚንጆ ማህበረሰብ ዝቅተኛ ማህበራዊ ደረጃ የተሰጣቸውና በልማድ የተገለሉ ናቸው፡፡ ሚንጆ ማህበረሰብ በተፈጥሮ ደን አካባቢ የሚኖሩና በአደን፣በከሰል፣እንጨትና ሌሎች የባህላዊ ዕደጥበብ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ናቸው፡፡የማንጆ ማህበረሰብ መገለል እንደ ማህበረሰቡ ልማዳዊ ዕይታ በማንጆ የአመጋገብ ስርአታቸው የሞቱና የዱር እንስሳትን የሚመገቡ በመሆኑ እንደሆነ ተገልጾል፡፡
በአሁኑ ወቅት ግን የመገለሉ ሁኔታ እየቀነሰ መምጣቱ እና የአመጋገብ ስርአታቸውም እየተሻሻለ መምጣቱ ይናገራሉ፡፡ የከፋ ዞን ማህበረሰብ በአብዛኛው በእርሻ ስራ ላይ የተሰማሩ ሲሆን በደን አካባቢ አነስተኛ የእርሻ ማሳ ይጠቀማሉ::
በ1999 የስታትስቲክሰ ባለ ስልጣን መረጃ 92.29 ፐርሰንት የህዝቡ ቁጥር በገጠር የመኖር እና በእርሻ ስራ ላይ የሚተዳደር ነው፡፡በከፋ ዞን ካለው የመሬት አቀማመጥ 56 ፐርሰንት ለእርሻ ምቹ የሆነ ፣29 ፐርሰንት ደን እና ጫካ እንዲሁም 14 ፐርሰንት ህዝብ የሰፈረበት እና ለተለያዮ አገልግሎቶች የሚውል ነው፡፡
በከፋ ዞን ከሚመረቱት ዋና ዋና ምርቶች ዉስጥ በቆሎ፣ማሽላ፣እንሰት፣ገብስ፣እና ስንዴ ይገኝበታል፡፡ በከፋ ዞን ቡና እና ጤፍ ዋናዎቹ የገቢ ምንጮች ናቸው፡፡ከአንስሳት ከብት፣በግ፣ፍየል፣ዶሮ፣አህያ፣ፈረስ እና በቅሎ ወናዎቹ የዞኑ ሃብቶች ናቸው፡፡
የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ አስተዋጽኦ ከሚያበረክቱ የኤክስፖርት ምርቶች መካከል በዋናነት ቡና በስፋት የሚመረትባት፣ውሽውሽ ሻይ ልማት፣ማር ምርት፣ቅመማ ቅመም ወዘተ በከፍተኛ ደረጃ ስለሚመረት ሀገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ዞኑ አስተዋጽኦ እያደረገ ነው፡፡
ቋንቋ:-ካፊ-ኖኖ(kafi noonoo)
3,000,000
የከፋ ዞን የደን ሽፋን እና የብዝሃ ህይወት ጥብቅ ደን ገፅታ የካፋ ዞን የደን ሽፋን
ከጠቅላላው የከፋ 10,602.7 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ውስጥ የተፈጥሮ የደን ሽፋን ከፍተኛውን የመሬት ሽፋን ይይዛል፡፡ደን እና የተፈጥሮ ጨካ የከፍቾ ብሄረሰብ ኑሮ እና ማህበራዊ ህይወት አንድ አካል ነው፡፡በቅርብ ጊዜ እየወጡ ያሉት የምርምር ውጤቶች እንደሚያስረዱት በከፋ ምድር ውስጥ ባሉት ጫካዎች በአብዛኛው የጫካ የተፈጥሮ ቡና ይበቅላል፡፡ከዚህም በመነሳት በከፋ ጫካዎች ዉስጥ የበቀሉና ተራብተው የሚገኙ ከ5 ሺ በላይ የቡና ዝርያዎች ይገኛሉ፡፡ደን ለከፊቾ ህዝብ ሁሉም ነገሩ ነው ማር፤ኮረሪማ፤ጥምዝ የተለያዩ የተፈጥሮ ፍራፍሬዎች፣ቶጆ፣ጋሮ ስራስሮች ወይም አኖ በከፋ ደን ውስጥ የሚገኙ ናቸው፡፡ እነዚህ የከፋ የተፈጥሮ ደኖችና ጫካዎች በከፊቾ ብሄረሰብ ባህል ከአባት ወደ ልጅ ሲወራረሹ የመጡ እያንዳንዱ ዛፍ ከትዉልድ ወደ ትውልድ ሺተላለፍ የመጣ እና ባለቤት ያለው ነው፡፡የዚህ የባለቤትነት ባህላዊ የደን እንክብካቤና አጠባበቅ የኮቦ ስርአት ተብሎ
ይጠራል፡፡ተፈጥሮ ሀብቱንና ደኑን ለመጠበቅ አስተዋጽኦ ካደረጉት ሀገር በቀል ዕዉቀቶች አንዱ የኮቦ ስርአት ነው፡፡ 1.3.2.የከፋ የብዝሃ ህይወት ጥብቅ ቦታ ወይም ባዮስፌር ገጽታ
በደቡብ ክልል በከፋ ዞን ከ760 ሄክታር በላይ የሚሸፍነው የባዮስፌር ጥብቅ ቦታ በሰኔ 2010.እ.ኤ.አ በዩኔስኮ በአለም የብዝሀ ህይወት ጥብቅ ቦታ ተብሎ ተመዝግቧል፡፡በዚሁ የብዘሀ ህይወት ጥብቅ ቦታ ጥቅጥቅ ደኖች፣የጫካ ቡና፣ረግረጋማ ቦታ፤የግጦሽ መሬት፤የቀርከሃ ደን እና ሌሎችም የሚገኙበት ነው፡፡ከፋ በአለም በብዝሃ ህይወት ከሚታወቁ 34 ቦታዎችአንዱ ነው፡፡ በከፋ ጥብቅ ደን ከ250 በላይ የእፅዋት ዝርያዎች፣የጫካ ቡና የአፍሪካ ቀይ እንጨት፣ቀርከሃ ስድስት መቶ የሚሆን የእንስሳት ዝርያ፣ዝንጀሮ፣ጉማሬ አንበሳ እና የተለያዩ የወፍ ዝርያዎች ይገኛሉ:: የባዮስፌር ጥብቅ ቦታዎች መርህ ብዝሃ ህይወቱን በመጠበቅ የአካባቢ
ማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያጎለብት የዘላቂ ልማት ስትራቴጅ ነዉ። የሰውና የባዮስፌር ፕሮግራም ሀገራችን በሁለተኛ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን አቅድ ዉስጥ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት የሰጠችው ልዩ ትኩረት በቀጥታ የሚደገፍ በተጨማሪም በተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ያፀደቀችዉን አለም አቀፍ ዘላቂ ልማት ግቦች ወደ ተግባር የማሸጋገሪያ ድጋፍ ሰጭ ፕሮግራም ነው የባዮስፌር ጥብቅ ቦታዎች በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያገኙ ሲሆን የሀገራት መንግስታት በቂ የህግ ሽፋን ስጥተዉ የሚጠበቁ ናቸው።የባዮስፌር ጥብቅ ቦታዎች ህይወት ያላቸው ላብራቶሪዎች ሲሆኑ በተለይም የመሬት የውሃ እና የብዝሃ ህይወት ቅንጅታዊ አስተዳደር ውጤታማነት የሚፈተሽበት የምርምር ቦታ ነው።
በአለም ደረጃ የባዮሰፈር ጥብቅ ቦታዎች ሰፊ ትስስር እና ኔት ዎርክ የፈጠሩ ሲሆን በዩኔስኮ መረጃ መሰረት በአለም ላይ የባዮስፌር ኔትዎርክ ውስጥ ስድስት መቶ ሃምሳ የባዮስፌር ጥብቅ ቦታዎች ከ 120 በላይ ሀገራት ውስጥ እንደሚገኙ ተብራርቷል፡፡ በባዮስፈር መርህ መሰረት ጥብቅ ቦታዎቹ ለሶስት ዋና ዋና ዓላማዎች የሚዉሉ ሲሆን የተፈጥሮና የባህል ብዝሃነትን ለመጠበቅ በዚህም የብዝሀ ህይወት ዝርየዎች፣ስነ-ምህዳሩና የተለያዩ የእፅዋትና የእንስሳት ዘሮች እነዲጠበቁ ይረዳል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ በጥብቅ ቦታዎቹ አካባቢ ኢኮኖሚያዊና ማህበረሰባዊ ልማት በማምጣት ለዘላቂ ልማት፣ለአካባቢ ጥበቃ እና ለባህል እሴቶች መጠበቅ አስተዋጽኦ ማድረግ ሲሆን ሶስተኛ የባዮስፌር ጥብቅ ቦታዎቹ ለተለያዩ የጥናትና ምርምር ስራዎች ግብአት የሚሰጡ የፕሮጀክት፣የትምህርትና ስልጠና እንዲሁም ልምድ ልውውጥ ለማድረግ በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ የጥበቃና ልማት መረጃዎችን ለመለዋወጥ ይጠቅማሉ፡፡ በአጠቃላይ መልኩ ባዮስፌር ሪዘርቭ ማለት መሬትን፣ደንን፣እርሻ፣ግጦሽናረግረጋማ ቦታዎችን፣የባህር ዳርቻ፣የውሃ አካልና በውስጡ የሚኖሩ ህይወት ያላቸው እፅዋትና እንስሳትን እንዲሁም ሰውንና ባህሉን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ ጥናት በዩኔስኮ አስተባባሪ ካውንስል ወይንም ዩኔስኮ ያስቀመጠውን መስፈርት አሟልቶ የተመዘገበ ቦታ ነው፡፡ የባዮስፌር ጥብቅ ቦታዎች በሦስት ደረጃ ተከፍለው የተቀመጡ ሲሆን እነሱም ጥብቅ፣ዳርቻ እና መሸጋገሪያ (core, buffer and transit) አካባቢ ተብለው ተመድበዋል፡፡ መረጃ ትንተና እና የጥናቱ ግኝቶች ለባዮስፌር ጥብቅ ቦታ ዘላቂነት አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ሀገር በቀል ዕውቀቶች እንደሚታወቀው ሀገር በቀል እውቀት ብዙ ዘርፎች ያሉትና በአንድ ማህበረሰብ ባህል ውስጥ የሚገኝ የእውቀት፣የጥበብና የአስተሳሰብ ሀብት ነው፡፡ይህ ሃብት ብዙ ዘርፎች ያሉት የባህላዊ ክንዋኔዎችና ስርአቶች (rituals) የተፈጥሮ ሃብት አያያዝና አጠቃቀም፣የግብርና እርሻ ዘዴዎች እውቀት፣የደን እና የዱር አራዊት ጥበቃ፤ባህላዊ መድሃኒት፣ቅመማ፤የከብት ጤና አጠባበቅ ባህላዊ የግጭት አፈታትና የዳኝነት ስርአት፤እደጥበባትና ባህላዊ የስራ ፈጠራ ይገኝበታል፡፡ሀገር በቀል እውቀት ብዙ ጊዜ በቃልና በልማድ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ የባህል ሃብታችን ነዉ ፡፡ የተለያዩ ፀሃፍት ለሀገር በቀል እውቀት የተለያዩ ስያሜዎችን ይሰጣሉ፡፡ብዙዎቹ የሚነሱት አገራዊ እውቀት በአብዛኛው በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ የሚፈጠር ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚወራረስ፣የህብረተሰብ አባላት ለተለያዩ ማህበራዊ፣አኮኖሚያዊ እና አስተዳደራዊ ጉዳዮች የሚጠቀሙበት የዕዉቀት ሀብት ነው ይላሉ፡፡ በአገር በቀል እውቀት ላይ የፃፉ ምሁራን እንደሚሉት አገር በቀል እውቀት በአንድ የህብረተሰብ ባህል ውስጥ የሚገኝ ልዩ አካባቢያዊ እውቀት ነው፡፡አገር በቀል እውቀት በግብርና፣በጤና አጠባበቅ፤በምግብ ዝግጅት፣በትምህርት፣በተፈጥሮ ሃብት አያያዝ፣በእደ ጥበብና በሌሎች በርካታ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ለመስጠትና ዘላቂ ልማት ለማስፈን ጉልህ ድርሻ እንዳለው አረጋግጠዋል፡፡በመሆኑም ሀገር በቀል እውቀት ዘላቂ ለሆነ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ፤ለደን፤ለውሃ፤ለአፈር፤ለእርሻ ስራና ለአካባቢ ጥበቃ ያገለግላል፡፡በአሁኑ ወቅት የሰው ልጆች በተፈጥሮ ሃብት መሸርሸርና የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ትልቅ ተግዳሮት እየገጠማቸው ነው፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ የስነ-ምህዳር ለውጦችና ተግዳሮቶች ኢፍትሃዊ ከሆነው የሃብት አጠቃቀም ጋር ተዳምሮ የድሃውን ህብረተሰብ ደህንነት ስጋት ላይ ጥለዉታል፡፡ይህንን ስጋት ለመቀነስ የተለያዩ የተፈጥሮና የማህበራዊ ሳይንስ ተመራማሪዎች በቅንጅት የስነ-ምህዳር ጥበቃና መልሶ ማልማት ተግባራት በጥናትና ምርምር እና በፖሊሲ ታግዞ የዘላቂ ልማት ስትራቴጅ አካል እንዲሆን እየሰሩ ነው፡፡ ባህላዊ እውቀት ማህበረሰብ፤ ለችግሮቹ ወይም አኗኗር ተግዳሮቶቹ የሚሰጠው መፍትሄ እራሱን የሚያስተዳድርበት ስልት፣ግጭቶችን የሚፈታበት ዘዴ፣ በሽታን የመከላከል ስልት፣የውሳኔ አሰጣጥ ዘዴዎች እራሱን የሚገልጽበት ጥበቦች፣ተፈጥሮ ሃብትና አካባቢውን የሚጠብቅበት እውቀት ነው፡፡ የከፋ ባዮስፌር ጥብቅ አካባቢ የህብረተሰቡን ዕውቀት ማዕከል ያደረገ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ፣ልማትና እንክብካቤ ይደረግለታል፡፡ ከዳሰሳ ጥናቱ የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመዉ በከፋ ብሄረሰብ አራት ዋና ዋና የሀገር በቀል ዕውቀቶች ለተፈጥሮ ሃብት ጥበቃና እንክብካቤ አስተዋጽኦ እያደረጉ ነው፡፡
ካፋ የኢትዮጵያ ብሔር ነው።
- ^ ካፋ(ከፋ)