ኮናይንግ ቤኬክላክ

ከውክፔዲያ

ኮናይንግ ቤኬክላክአይርላንድ አፈ ታሪክ ከ593 እስከ 572 ዓክልበ. ግድም ድረስ የአየርላንድ ከፍተኛ ነጉሥ ነበር።

የአይርላንድ ታሪኮች እንዳሉት፣ ኮናይንግና ዮኩ ፊያድሙዊኔ በመጀመርያው ከፍተኛ ንጉሥነቱን አካፈሉ፤ ኮናይንግ በስሜኑ ይገዛ ነበርና ዮኩ ደቡቡን ወሰደ። አብረው ለ፭ አመት ገዝተው በ588 ዓክልበ. ግድም ሉጋይድ ላምዴርግ ዮኩን ገድሎ የደቡቡን መንግሥት ያዘ። ከሌላ ፮ ዓመታት በኋላ (582 ዓክልበ.) ኮናይንግ ሉጋይድን ገድሎ የመላው አይርላንድ ከፍተኛ ንጉሥ ለ፲ ዓመታት ሆነ። ይህ የላውድ አቆጣጠሮች (1014 ዓም ተቀነባብ) እና የድሮ አቆጣጠር በመከተል ነው፣ በኋላ የታዩት ታሪኮች ግን ከዚያ በፊት ያደርጉታል፣ ስለ ኮናይንግም አመቶች ቁጥር ይለያያሉ።