ዋናው ገጽ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search
መቅድም
enllaç=
        ውክፔዲያ ዓለም-ዓቀፍ የዕውቀት ማከማቻ ድረ-ገጽ ነው። ውክፔዲያ የጋራ ነው። ሁሉም ሰው በመዝገበ ዕውቀቱ እንዲሳተፍ ተፈቅዷል። አዳዲስ ተሳታፊዎች፣ የጀማሪዎች ማያያዣን በመጫን በፍጥነት ስለ ድረ-ገጹ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

        አዲስ ጽሑፍ ለመጻፍ ወይንም ነባር ጽሑፍ ለማስተካከል ደፍሮ መሞከር ጥሩ ልምድ ነው። ከሌሎች ውክፔዲያዎች የተተረጎሙ ጽሑፎች እንዲያቀርቡ ይበረታታሉ። ለዚህ ተግባር እነዚህን መዝገበ ቃላት ማማከር ይችላሉ ። የሚያቀርቡት ጽሑፍ ያልተሟላ ወይንም ያልተጠናቀቀ ቢሆንም እንኳ መጨነቅ አያስፈልግም። ጅምር ጽሑፍ በተፈለገ ጊዜ ሊሻሻል ይችላልና።
የመደቦች ዝርዝር
Wikibar.png
ለዕለቱ የተመረጠ ጽሑፍ
enllaç=

ጆን ኔፐር

John Napier.jpg


ጆን ኔፐር

ጆን ኔፐር (1542– 1610) – ስኮትላንዳዊ ሓሳቢ (ሒሳብ ተማሪ)፣ የተፈጥሮ ህግጋት ጥናት ተመራማሪ፣ ሥነ ፈለክ አጥኚ እና ኮኮብ ቆጣሪ ነበር።

ከሁሉ ስራው በታሪክ ቀደምት ስሙ እሚነሳው ሎጋሪዝምን በመፈልስፉ ነበር። ይህን የሂሳብ መሳሪያ የፈለስፈበት ዋና ምክንያት ከኮምፒውተር እና ካልኩሌተር ርቆ በሚገኘው ዘመን ቁጥሮችን ማባዛት፣ ጊዜ የሚወስድ፣ ለስህተትም የተጋለጠ መሆኑ ነበር። ሎጋሪዝም ማባዛትን ወደ መደመር በመቀየር አስቸጋሪውንና አሰልቺውን የማባዛት ስራ ለማቃለል ይረዳል።

ክፍልፋይ ቁጥርን ለማሳየት የምትጠቅመው ነጥብ በአውሮጳ ታዋቂ እንድትሆን ያደረገ ኔፐር ነበር። ከዚህ በተረፈ ኔፐር በሥነ መለኮትሥነ አልኬሚ ይጠቀሳል። በዘመኑ ደግሞ በጥንቆላ ና በማሟረት ስራ ይታማ ነበር።

ኔፐር በጥንቆላ ስለመታማቱ

ኔፐር በነበረበት ዘመን ጥቁር ሸረሪት በትንሽ ሳጥን ደብቆ ይዞር ነበር ይባላል፤ ደግሞም ለመኖሪያው ቤቱ አድባር እንዲሆነው ጥቁር አውራ ዶሮ ያረባ እንደነበር ይጠቀሳል።

የቤቱ ሰራተኞች ዕቃ ሲሰርቁ ይሄው አውራዶሮ የትኛው አገልጋዩ እንደሰረቀው ለማወቅ ይረዳው ነበር ይባላል። ለምሳሌ ዕቃ ከቤቱ ሲጠፋ፣ አገልጋዮቹን አንድ ባንድ ከዶሮው ጋር እቤቱ ውስጥ እየቆለፈ ዶሮውን እንዲነኩ ከውጭ ሆኖ ያዛቸው ነበር። ጥቁር አውራዶሮውን ከተጠርጣሪዎቹ ጋር ከመቆለፉ በፊት ጥላሸት ይለቀልቀው ነበር። ጥፋተኛ የሆኑት አገልጋዮች ዶሮው ይናገርብናል ብለው ስለሚፈሩ ዶሮውን አይነኩም፣ ጥፋት የሌለባቸው ባንጻሩ ይነኩታል። በኋላ ላይ ኔፐር እጃቸውን አንድ ባንድ ሲመረምር፣ እጃቸው ንጹህ የሆኑት ጥፋተኛ እንደሆኑ ያውቃል ማለት ነው።

ኔፐር ጠንቋይ እንደሆነ በአገሩ የተማበት ሌላ ምክንያትም አለ። አንድ ቀን ኔፐር ያሰጣውን ጥራጥሬ የጎረቤቱ እርግቦች እየለቀሙበት ይደርሳል። በዚህ የተናደደው ኔፐር ጎረቤቱን ጠርቶ እርግቦቹ እኔፐር ግቢ ሁለተኛ ከመጡ የእርሱ ንብረት እንደሚያደርጋቸው ያስጠነቅቀዋል። በሚቀጥለው ቀን እርግቦቹ ኔፐር ግቢ ውስጥ ታዩ፣ ሆኖም ግን በሚያስፈራ መልኩ ከቆይታ በኋላ ሁሉም ተዝለፍልፈው ወድቀው በኔፐር እየተለቀሙ አዘጋጀላቸው አቅማዳ ውስጥ ሲታጨቁ ታዩ። ኔፐር ሆየ ባለፈው ቀን ጥራጥሬውን የሚያሰክር ብራንዲ ውስጥ ከዘፈዘፈ በኋላ ነበር ለስጦሽ የዘረጋው። ጠዋት ላይ እርግቦቹ አተሩን ሲለቅሙ እየተሳከሩ መብረር አቅቷቸው መሬት ላይ እየተንደፋደፉ ተፈነገሉ።

ታሪክ በዛሬው ዕለት
enllaç=

የካቲት ፲፭

RasDesta.jpg
  • ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ግብጽ እና ሶርያ የአረብ ሪፑብሊ ኅብረትን (United Arab Republic) መሠረቱ። ይሄ የሁለቱ አገሮች ኅብረት ከሦስት ዓመታት በኋላ ቢፈርስም የግብጽ መጠሪያ ስሟ ሆኖ ለብዙ ዓመታት ቆይቷል።.
  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያአብዮት ፍንዳታ የተፋፋመውን ሽብር ለመቆጣጠር በተወሰደው እርምጃ፣ የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ወታደሮችን በአዲስ አበባ ከተማ ቀበሌዎችና ‘ቁልፍ’ ቦታዎች ለጥበቃ አሰማራ።
ሕገ ወጥ የአውሮፕላን ጠለፋ.jpg
  • ፲፱፻፸፩ ዓ/ም - ኢትዮጵያ ሕገ ወጥ የአውሮፕላን ጠለፋ ለመከላከል በዓለም ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት የጸደቀውን ስምምነት ፈረመች።
Jonas Savimbi.jpg
  • ፲፱፻፺፬ ዓ/ም አንጎላዊው የፖለቲካ እና የነጻነት ትግል መሪ የነበሩት ጆናስ ሳቪምቢ በወታደራዊ የደፈጣ ስልት ተገደሉ።
የሥራ ዕህቶች
enllaç=

ነጻ መጽሐፈ ዕውቀት የሆነው የውክፔዲያ አስተናጋጅ Wikimedia Foundation ነው።
ይህ ለትርፍ-ያልሆነ ድርጅት አያሌ ልዩ ልዩ ባለ ብዙ ቋንቋ እና የጋራ ጥቅም ሥራ እቅዶች ያካሂዳል፦

ለዕለቱ የተመረጠ ምስል
Wikibar.png

Dülmen, Börnste, Waldweg -- 2015 -- 4649.jpg