ውርዴ ወይም ፈንጣጣ

ከውክፔዲያ

ውርዴግብረ-ስጋ የሚተላለፍ የባክቴሪያ በሽታ ነው። ውርዴ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው የውርዴውን ቁስል በቀጥታ ከነኩት ነው። ውርዴ ብዙ ምልክቶች ሲኖሩት፣ የሌላ በሽታ ምልክቶች ሊመስሉና ሊያታልሉም ይችላሉ። ውርዴ ሦስት ደረጃ ኣሉት።

  1. 1ኛ ደረጃ፦

በተጋባ ከ10 እስከ 90 ቀናት ባሉት ውስጥ የበሽታው የመጀመሪያ ምልክቶች ይታያሉ። የውርዴ ቁስል ይወጣል፣ ካልታከመም የውርዴው ቁስል እየባሰ ይሄዳል።

  1. 2ኛ ደረጃ፦

በማንኛውም ቦታ ከቆዳ ላይ ቀይና ፍም የመሰለ ነገር ይወጣል። ግን ምንም የማሳከክ ስሜት የለበትም። ካልታከመ በሽታው እየባሰ ይሄዳል።

  1. 3ኛና የመጨረሻው ደረጃ፦

ከውጭ ያሉት ምልክቶች ሁሉም ይጠፋሉ። የበሽተኛው ገላ ስሜት መጥፋት ይጀምራል፣ ከኣእምሮ ድክመትም ይደርሳል፣ የኣካላት ማንቀሳቀስም ሊያቅት ይጀምራል። ሕክምና ካላገኘ ውርዴ ሞትን ያስከትላል።

በመጀመሪያ ደረጃ የሚገኝ ውርዴ በቀላሉ ሊታከምና ሊድን ይችላል። ግን በሓኪም ትእዛዝ እንጂ ከፋርማሲ ማንም ሰው የሚገዛቸው መድሓኒቶች ባክተሪያውን ሊያጠፉት ኣይችሉም። ሓኪም የሚያዝዘው መድሓኒት ውርዴውን ቢያጠፋውም እንኳን በኣካል ላይ ለደረሰውጉዳትና ጠባሳ ለማከም ኣይቻል ይሆናል።

  • መከላከያው፦

ውርዴን መከላከል ይቻላል። እንደ ሌሎች የግብረ- ስጋ (ኤስቲዲ) በሽታዎች ውርዴም ከግብረ-ስጋ ፈጽሞ በመገለል፣ ወይም ሕመሙ ከሌለበት ሰው ብቻ ግብረ-ስጋን በመፈጸም ለመከላከል ይቻላል። ኮንዶምን በመጠቀም ግን ሕመሙን ለመከላከል ኣይቻልም።