ውክፔዲያ:ቀላል መማርያ/ገጽ 3

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search
Nuvola apps cache.png

ሌላውን ጽሑፍ ስለ ማያያዝ:

  • መያያዣ ለሌሎች መጣጥፎች በቀላል ሊፈጥሩ ይቻላል። ለምሳሌ በመጣጥፍዎ ውስጥ «ግሥላ» የሚልን አንድን ቃል ቢኖር ስለ ግሥላዎች ወደሆነው ጽሁፍ ለማያያዝ፣ ዝም ብለው ሁለት ባለ-ማእዘን ቅንፍ ([[ ]]) ይጨመራሉ። ስለዚህ [[ግሥላ]] በመጻፍ መያያዣውም እንዲህ ግሥላ ይመስል ነበር።
  • ከዚህ በላይ በመያያዣው ውስጥ የሚታዩትን ቃላት ለመቀየር ይቻላል። እንዲህ ለማድረግ የፒፓ ምልክት ( | ) ከመያያዣው አርዕስት ቀጥሎ ጨምረው ለመታየት የሚፈልጉትን ይጻፉ።
  • የውጭ ድረ ገጾችን ማያያዝ ደግሞ ይቻላል። ለምሳሌ [http://www.google.com ጉግል] (ያለ ፒፓ ምልክት) እንዲህ ይታያል፦ ጉግል