ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ሚያዝያ 3
Appearance
- ፲፰፻፷ ዓ/ም - የስቅለት ዓርብ ዕለት በ ሎርድ ናፒዬር የሚመራው የእንግሊዝ ሠራዊት እና የዓፄ ቴዎድሮስ ሠራዊት በመቅደላ ተራራ ሥር በምትገኘው እሮጌ በምትባል ሥፍራ ላይ ጦርነት ገጥመው የዓፄ ቴዎድሮስ የጦር አዛዥ የነበሩት ፊታውራሪ ገብርዬ ሞቱ።
- ፲፱፻፫ ዓ/ም - የልጅ ኢያሱ ሞግዚት የነበሩትራስ ቢትወደድ ተሰማ ናደው አልፈው በደብረ ሊባኖስ ተቀበሩ።
- ፲፱፻፵፬ ዓ/ም - የአዲስ አበባው ሊሴ ገብረ ማርያም ትምሕርት ቤት ተመረቀ፡፡
- ፲፱፻፷ ዓ/ም - የአሜሪካ ፕሬዚደንት ሊንደን ጆንሰን ጥቁር አሜሪካውያን ላይ የነበረውን የመኖሪያ ቤት ጭቆና ሕገ-ወጥ የሚያደርግ የሰብዓዊ መብት ሕግ አጽድቀው ፈረሙ።