ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ሰኔ 23
Appearance
- ፲፭፻፶፭ ዓ/ም የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ዓፄ ገላውዴዎስ በዘመኑ የካቶሊክ ዕምነት ተከታዮች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን <<ኦሪታዊ’ ናት>> እያሉ ስም የማጥፋት ዘመቻቸውን በመከላከል፣ ዳሞት ላይ የተጻፈ የሃይማኖቱን እውነትነት የሚገልጽ ውሳኔ ፈረመ።
- ፲፱፻፳፰ ዓ/ም - የፋሺስታዊ ኢጣልያ ሠራዊት ኢትዮጵያን በግፍ ወሮ ማስተዳደር ከጀመረ በኋላ እና ንጉሠ ነገሥቷ ከተሰደዱ በኋላ፤ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዠኔቭ በሚገኘው የዓለም መንግሥታት ማኅበር ላይ ተገኝተው የኢጣልያን ግፈኝነትና የኢትዮጵያን አቤቱታ አሰሙ።