ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ታኅሣሥ 12

ከውክፔዲያ

ታኅሣሥ ፲፪

  • ፲፰፻፲ ዓ/ም - በዘመነ መሳፍንት ፮ ጊዜ ከንጉሥነት ሥልጣናቸው የተሻሩት እና የነገሡት ዓፄ ተክለ ጊዮርጊስ በዚህ ዕለት በትግሬው መሥፍን በራስ ወልደ ሥላሴ ዘመን አርፈው፣ አክሱም ጨለቆት ሥላሴ ተቀበሩ።
  • ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - የጎጃሙ ራስ ኃይሉ ተክለ ሃይማኖት አማቻቸው የነበሩትን ደጃዝማች አበራ ካሣን እና ወንድማቸውን ደጃዝማች አስፋ ወሰን ካሣን ‘አይዟችሁ አትነኩም’ ብለው አታለው ካስገቡ በኋላ አሳልፈው ለፋሺስት ኢጣልያ ኃይሎች አስረከቧቸው። የጣልያኖቹም ጄኔራል ትራኪያ ወንድማማቾቹን ፍቼ ላይ በዚህ ዕለት አስረሽኖ አንገታቸውን አስቆርጦ ገደላቸው።
  • ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የደርግ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት "የኢትዮጵያ ኅብረተ ሰብአዊነት"ን (የኢትዮጵያ ሶሻሊዝም) በይፋ ካወጀ በኋላ፣ ቀዳሚ ተግባሩ ያደረገው "ብሔራዊ የዕድገት በኅብረት የዕውቀትና የሥራ ዘመቻ" የተሰኘ ፷ ሺ የሁለተኛ ደረጃ፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና አስተማሪዎችን በመላ አገሪቱ አሰማራ። የጊዘውም መፈክር ፣"በዕድገት በኅብረት - እንዝመት፣ ወንድና ሴት ሳንል ባንድነት" የሚል ነበር