ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ኅዳር 16
Appearance

- ፲፱፻፶፮ ዓ.ም. በዳላስ፣ ቴክሳስ ላይ በሰው እጅ የተገደሉት ሠላሣ አምሥተኛው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ በአርሊንግተን ብሔራዊ መቃብር በታላቅ ሥነ ስርዐት ተቀበሩ። በዚሁም የቀብር ስርዐት ለመሳተፍ ከዓለም ዙሪያ ብዙ መሪዎች መጥተው ነበር። ከነዚህም መሃል የፈረንሳይ ፕሬዚደንት ሻርል ደ ጎል፤ የአየርላንድ ፕሬዚደንት ደ ቫሌራ፤ የምዕራብ ጀርመን ቻንስለር ኤርሃርድና የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ይገኙበት ነበር።
- ፲፱፻፸፯ ዓ.ም. በኢትዮጵያ ውስጥ ለተከሰተው ታላቁ ድርቅና ረሐብ እርዳታ እንዲሆን በብሪታንያ ሠላሣ ስድስት የሙዚቃ ባለሙያዎች “ባንድ ኤይድ” በሚል ስም ተሰባስበው፤ “የክርስቶስ ልደት መሆኑን ያውቁታል ወይ?” (Do They Know It's Christmas) የተባለውን ዘፈን ቀረጹ።