ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ኅዳር 19

ከውክፔዲያ

ኅዳር ፲፱

  • ፲፰፻፵፭ ዓ.ም. - የደጅ አዝማች ካሣ (በኋላ ዓፄ ቴዎድሮስ)ሠራዊትና የጎጃሙ የደጅ አዝማች ጎሹ ተከታዮች ጉራምባ ላይ ተዋግተው ድሉ የደጅ አዝማች ካሣ ሆነ። ደጅ አዝማች ጎሹም በነፍጥ ተመተው ሞቱ።
  • ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. በብሪታንያ “ኮንሰርቫቲቭ” የቀኝ ፖለቲካዊ ቡድን መሪ የነበረችው ማርጋሬት ታቸር ከመሪነቷ ካስወገዷት በኋላ የጠቅላይ ሚኒስቴርነቱን ስልጣን ለአገሪቷ ንግሥት ዳግማዊት ኤልሳቤጥ አስረከበች። ከአሥራ አምሥት ደቂቃ በኋላ ንግሥቲቱ አዲሱን የ”ኮንሰርቫቲቭ” ቡድን መሪ ጆን ሜጀርን አቅርባ፣ አዲስ አስተዳደር በጠቅላይ ሚኒስቴርነት እንዲመራ ሾመችው።