ውክፔዲያ:How to edit a page

ከውክፔዲያ

ዊኪፔዲያ ዊኪ ነው ማለትም ማንኛውም ሰው በቀላሉ ሊጽፍና ሊያስተካክል ይችላል።

አንድ ጽሑፍ ላይ ለመጨመር ወይም ለማስተካከል በገጹ መጀመሪያ ላይ 'ይህን ገጽ ለማዘጋጀት' የሚለውን ይጫኑ። ለመሞከር ከፈለጉ መፈተኛው፡ ቦታ ይሂዱ። ማስተካከል ከጨረሱ በኃላ ከስር ባለው የማጠቃለያ ሣጥን ውስጥ ስላደረጉት ለውጥ አጭር ማጠቃለያ መጨመር ይመከራል። አሁን 'ሳይላክ ቀድሞ ይታይ ብቻ' የሚለውን ሲጫኑ ያደረጉትን ለውጥ ገና የእውነተኛው መጣጥፍ ሳይለወጥ ማየት ይችላሉ። 'ለውጦቹ እካሁን ይታዩ' የሚለውን ከተጫኑ ደግሞ ያለፈውን ዕትም እና እርስዎ ያደረጉትን ለውጥ ያነጻጽራል። በመጨረሻ 'ገጹን ለማቅረብ' ሲጫኑ እርሶ የጨመሩትን ለውጥ ያትምና ወደ አዲሱ ጽሁፍ ይወስዶታል።