ውክፔዲያ:Reference desk

ከውክፔዲያ

ምክር በእርግዝና ወክት

መርዕድ ምን ማለት ነው[ኮድ አርም]

«መርዕድ የሚለው ቃል ትርጉም ምንማለት ነው» የሚል ጥያቄ ላቀረበው 197.156.67.82፦ ትክክለኛው ቃል 'መርድ' እንጂ መርዕድ እንዳልሆነ አለቃ ደስታ ተክለ ወልድ በ "ዐዲስ፡ያማርኛ፡መዝገበ፡ቃላት።" ላይ ይገልጻሉ። ግድፈቱም «ካ፲፱፻፴፫ ዓ/ም ወዲህ አንዳንድ ሰዎች መርድ በማለት ፈንታ መርዕድ አዝማች እያሉ በደብዳቤና በጋዜጣ ይጽፋሉ፤ በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን ጻፎችና ሠዓሊዎች ሞአን ሞዓ አንበሳ በማለት ስሕተት እንዳደረጉት ይኸም እንደዚያ ነው።» (ገጽ ፰፻፭) በማለት አብራርተውታል። መርድ ማለት ገሥግሥ፣ ፍጠን፣ ውረር፣ ዝረፍ ማለት ነው። የሺዋ መሳፍንትም 'መርድ አዝማች' በሚል የማዕርግ ስም ይጠሩ ነበር። ይኽም ማለት የወራሪ አዝማች ማለት ነው።--Bulgew1 (talk) 12:25, 18 ፌብሩዌሪ 2013 (UTC)[reply]

መርድ አዝማች 196.191.61.204 17:38, 19 ኤፕሪል 2023 (UTC)[reply]